ዜናዎች

⭕️ ኢትዮጵያ ቡናዎች ጋናዊውን የ21 ዓመት ግብጠባቂ አስፈርመዋል! 

    ትላንት የዝውውር መስኮቱን ሦስት ተጫዋቾችን በማስፈረም የጀመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች ዛሬም ጋናዊውን የ21 ዓመት ታዳጊ ግብ ጠባቂ ኢብራሂም ዳናልድ ከአሻንቲ ኮቶኮ ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል. አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ለጋና ብሄራዊ የታዲጊ ቡድን የተጫወተ ሲሆን የዋናው ቡድንም ሶስተኛ ግብ ጠባቂ እንደሆነም ታውቋል. በተመሣሣይ ቡናማዎቹ ከብሩንዲም፡አጥቂ አስፈርመዋል.   እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ህግ መሠረት አንድ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

⭕️የወላይታ ድቻ ወሳኝ ተጨዋቹ ወደ ግብጽ ሲጓዝ ዛሬ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል! 

👇   በተጠናቀቀው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው እና በዘንድሮ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ውድድር ላይ የዋንጫ ፍልሚያ ላይ የደረሰው የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ጀምሯል.   በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ወላይታ ድቻ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጎልቶ የወጣውን አጥቂ ቢንያም ፍቅሬ በግብፅ ክለቦች ተፈልጎ በአሁን ሰአት ካይሮ እንደሚገኝ ሲታወቅ ተጨዋቹ በግብፁ እስማኤሊያ አልያም የቀድሞ […]

ዜናዎች

የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ – 395 ሺህ ብር ክለቡ እንዲከፍል ፌዴሬሽኑ አስተላልፏል.

የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና ክለቦች መካከል መካሄዱ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር እና ሥነ ስርዓት ኮሚቴ በዕለቱ በተካሄደው ጨዋታ ጨዋታውን የመሩት የጨዋታ አመራሮችና የውድድር አመራር ያቀረቡትን ሪፖርት አይቶ በመርመር ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

አፍሪካ ዜናዎች

ሀዲያ ሆሳዕና የፊታችን ሀሙስ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል !

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት በጠንካራ ተፎካካሪነት በስምንተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ በቀጣይ አመት የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ እና የክለቡን የፋይናንስ አቅሙን የበለጠ ለማጠናከር ለወዳጅነት ጨዋታ እና ለገቢ ማሰባሰቢያ ወደ ፕሪቶሪያ የፊታችን ሀሙስ ያመራል። ነብሮቹ የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም በማምራት በደቡብ አፍሪካ ናሽናል ዲቪዢን ላይ ተሳታፊ ከሆነው ጂ ዲ አር ስታር ከተባለው […]

ዜናዎች

የሀምበሪቾ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በለቅሶ እና በአሳዛኝ የድረሱልኝ ጥሪ እየተማፀኑ ይገኛል !

የ2016 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ያሳለፍነው እሁድ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ውድድራቸውን በማጠናቀቅ አብዛኛዎች የሊጉ ቡድኖች ወደ መጡበት ከተማ እና ተጫዋቾች ሆነ አሰልጣኞች ወደ የቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሀምበርቾ ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም ይርጋ ጨፌ ቡና ያገለገሉበትን በውላቸው መሰረት ክፍያ ማግኘት እንዳልቻሉ እንዲሁም ችግረኛ ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ቀርቶ እየተረዱ እንደሚገኙ ተደጋጋሚ ጊዜ ትዕንግርት […]

ዜናዎች

🏆የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን የኢትዮጵያ- ቻምፒዮን ሆነዋል.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለ7ኛ ጊዜ የ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነዋል.              

ዜናዎች

ቻምፒዮኖቹ ከሐዋሳ – አዲስ አበባ

ከሀዋሳ በድል የተመለሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 ቻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከቦሌ አየር ማረፊያ በመነሳት በክፍት አውቶቡስ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ደስታውን ከደጋፊዎች ጋር ተጋርቶ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት የአሸናፊነቱን ዋንጫ በመያዝ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝቶ በዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዜናዎች

ከንቲባ አዳነች የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ ሆነው ተሹመዋል!

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሾሟቸዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ”አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋትን በተለይም የእግር ኳስ ሜዳዎችንን በማየት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰጠኝ እውቅና እንዲሁም የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሃላፊነት ስለሰጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ” […]

ዜናዎች

ራምኬል ሎክ የደቡብ ሱዳኑን ኤል ሜሪክ ክለብ ፊርማውን አኑሯል!

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያሳለፈው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመስመር ተጫዋች ራምኬል ሎክ የደቡብ ሱዳኑን ኤል ሜሪክ ቤንቲዩ እግርኳስ ክለብ ጋር ለመሠጫወት ፊርማውን አኑሯል.

ዜናዎች

የአዲስ አበባ ስታድየም ወንበር በአንድ ጨዋታ ተሰባብሯል!

እንደሚታወሰው ለዓመታት የአዲስ አበባ ስታደየም ከእድሳት ጋር በተያያዘ ጨዋታዎች ሳያስተናግድ ተዘግቶ ዛሬ የኢትዮጵያ ዋንጫ ማስተናገዱ ይታወሳል. እናም የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በተቀመጡበት በኩል የአዲስአበባ ስታዲየም ከእድሳት በኋላ በደጋፊዎች ፊት የመጀመሪያ ጨዋታ ሲደረግ ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን 2ለ1 ካሸነፈ በኋላ የድቻ ደጋፊዎች በተቀመጡበት ይህ ተከስቷል ።