ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

#ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን የሚያደርገው ዛሬ ረፋድ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ በነፃ እንዲመለከቱ ጋብዟል!

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከሱዳን አቻው ጋር ዛሬ(ዓርብ ) ረፋድ በ4 :00 ሰዓት እና ሰኞ(መስከረም 16) በ10፡00 ሰዓት  ያከናውናል። በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረጉት ጨዋታዎችን በነፃ በመታደም ብሔራዊ ቡድናችንን እንዲያበረታቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥሪውን ያቀርባል። መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን  :- https://www.instagram.com/ethio_kick 🔛ድረ ገጻችንን  :- https://ethio-kickoff.com

ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

# ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ በስቲያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዲ.ሪ. ኮንጎ ጋር ያደርጋል!

  በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ሲጀምሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሐሙስ መስከረም 12 ዲ.ሪ. ኮንጎን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ታስተናግዳለች። ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን ለማስፋት የእግርኳስ ቤተሰቡ ድጋፍ ያስፈልገዋል። በመሆኑም በዕለቱ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በነፃ በመታደም ለብሔራዊ ቡድናችን የሞቀ ድጋፋችሁን እንድትሰጡ […]

ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

-ኢትዮጵያ ከሱዳን ለምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አሰሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊፋ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ወቅትን በመጠቀም ከሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር መስከረም 13 እና መስከረም 16 አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ያከናውናል። ለዚህ ጨዋታ እንዲረዳም የብሔራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 23 ተጫዋቾችን ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች በነገው ዕለት ሪፖርት በማድረግ በቦሌ ጁፒተር ሆቴል ተሰባስበው ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናል። ግብ ጠባቂዎች በረከት […]

አፍሪካ ዜናዎች

➖የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በካሜሩኑ ውጤት የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀ !

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሩን ያሳየውን የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ፌዴሬሽኑ “ባቀድነው ልክ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ውጤታማ ባለመሆናችን የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን” የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል ። አቶ ባህሩ ቀጥለው “ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ […]

አፍሪካ ዜናዎች

“የነገው የመጀመርያ ጨዋታ ነው፣እነሱ ጠንካሮች ቢሆኑም እኛም የተሻለ ነገር ለማሳየት ዝግጁ ነን” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ጌታነህ ከበደ ነገ ምሽት 4፡00 ላይ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ከምታደርገው ጨዋታ ቀደም ብሎ ዛሬ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሀሳባቸውን በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች አካፍለዋል። ወደ ካሜሩን ለመድረስ የመጀመርያው ቡድን እንደሆንን በመግለፅ መግለጫቸውን የጀመሩት አሰልጣኝ ውበቱ ከሶስት አፍሪካ ዋንጫዎች በኋላ ወደ መድረኩ በመመለስ ጥሩ ቡድን ይዘው ለመቅረብ እና […]

አፍሪካ ዜናዎች

የኮቪድ ወረርሽኝ ዋልያዎቹ በሚገኙበት በምድብ 1 ሀገራት ላይ ጠንክሯል ! – ከዋልያዎቹ አራት ከካሜሩን አራት በኮቪድ ተይዘዋል !

የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ዘጠኝ ቀናት ብቻ ሲቀረው የውድድሩ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አስመልክቶ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች ከጨዋታው መጀመር በፊት ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። በተለይም ደግሞ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በተሳታፊ ሀገራት ላይ ሊደርስ የሚችለው የኮቪድ ጫና ሌላኛው ስጋት ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ነው። ከውድድሩ መጀመር በፊት ባለፈው እሁድ ከሀያ አራቱ ተሳታፊ ሀገራት ቀዳሚው ሆኗል ያውንዴ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]

አፍሪካ ዜናዎች

ፊፋ በወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ሲልቫይን ግቦሆ ላይ የዕገዳ ውሳኔ አሳልፏል !

የፊፋ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መልዕክት ሲልቫይን ግቦሆን በጊዜያዊነት እንዳገደ አስታውቋል።ለአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን እየተጫወተ የሚገኘው ሲልቫይን ግቦሆ በአሁኑ ወቅት በወልቂጤ ከተማ ተመዝግቦ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን ኖቬምበር ላይ አይቮሪኮስት ከጋቦን ጋር ስትጫወት በእጣ የዶፒንግ ምርመራ እንዲሰራለት ወጥቶበት የሽንት ናሙና ሰጥቶ ነበር። በዚህ ናሙና ውስጥም ትራይሜታዚዲን የሚባል ከ2014 ጀምሮ አትሌቶች እንዳይጠቀሙት በዋዳ የታገደ ንጥረ […]

አፍሪካ ዜናዎች

የዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ሱዳንን 3-2 አሸንፏል! – ቀጣይ ተጋጣሚያቸው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ካሜሩን ገብቷል

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ይረዳውዘንድ የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርጎ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ሁለት ጎሎችን ሽመልስ በቀለ አንድ ጎል በአጠቃላይ 3 ለ2 አሸንፏል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቻቸው በዛሬው ጨዋታ የቡድናቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እንዲሁም የቡድኑን ቀጣይ መሻሻል ያለበትን በተወሰነ መልኩ ያዪበት አጋጣሚ ነው ተብሎ ይገመታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]

አፍሪካ ዜናዎች

#የዓለማችን 4ኛው ውድ ዋንጫ የአፍሪካ ዋንጫ ድዋላ ደርሷል !

በካሜሩን አዘጋጅነት በፈረንጆቹ ከJanuary 9 ተጀምሮ February 6 የሚጠናቀቀው የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር 10 ቀናት ቀርተዋል። አዘጋጇ ሀገር ካሜሩንም ውድድሩን ሞቅ ደመቅ ባለ መልኩ ለማካሄድ እንግዷቿን መቀበልም የጀመረች ሲሆን በካሜሩን የተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች በዓለማችን አምስተኛ ውዱ የሆነው የአፍሪካ ዋንጫም ለህዝብ በክፍት መኪና ለእይታ አየቀረበ ሲሆን አሁን ላይ ዋንጫው ከሊምቤ ወደ ሁለተኛ ዋና ከተማ ዱዋላ […]

አፍሪካ ዜናዎች

” የአፍሪካ ዋንጫውን ይዛችሁ ተመለሱ አለበለዚያ በእናንተ ላይ ወጪ ያደረግነውን ገንዘብ ትመልሳላችሁ ” -የጊኒው ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ

የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ የሁለት ሳምንት ጊዜ ቀርቶታል። እናም የውድድሩ ተሳታፊ አገራት የተለያዩ መረጃዎች መሠማትም ቀጥለዋል።ከአፍሪካ ዋንጫ መረጃዎች መሀል ዛሬ የበርካታ ሚዲያዎችን ዘገባ የሳበው የጊኒ ፕሬዝዳንት ንግግር ሲሆን ጊኒ በአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ሁለት ከዚምባብዌ፣ ሴኔጋል እና ማላዊ ጋር ትገኛለች።የጊኒው ወታደራዊ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ማማዲ ዱምቡያ ብሔራዊ ቡድናቸውን ትላንት በቤተመንግስት ጠርተው የሽኝት ፕሮግራም ሲያደርጉ የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል።”የአፍሪካ […]