የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውጥረት ተካርሮ መቀጠሉን መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ዛሬ በኔክሰስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ያረጋገጠም ሆኗል።በተለየም ፍጥጫው በፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እና በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኦሎምፒክ ኮሜቴ ፕሬዝዳንት መካከል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንደሚታወሰው የኦሎምፒክ ውድድሮች በመጡ ቁጥር ተመሳሳይ ውጥረቶች ከዚህ […]
አትሌቲክስ
የአትሌት ለምለም ኃይሉ ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ፀደቀ !
በፈረንሳይ ሌቪን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የቤትውሰጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አትሌት ለምለም ያስመዘገበችው የ 4 01.57 ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ ከ 20 ዓመት በታች የቤት ውስጥ የ 1500 ሜትር የዓለም ሪኮርድ ሆኖ ማፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ በድህረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ ክብረወሰን ሰበረች!
ኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በፈረንሳይ ሊቫን በተረደረገው የአለም የቤት ውስጥ በ1500 ሜትር ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እ.ኤ.አ. በ 2014 (በ3 55.17) ተይዞ የነበረውን አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ3 53.09 ሰዓት በመግባት አዲስ የዓለም የቤት ውስጥ ሪኮርድ ባለቤት ሆናለች
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፈረንሳይ ሌቪን ደምቀው አመሹ
በፈረንሳይ ሌቪን በተደረገው የ2021 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።በሴቶች የ1500ሜትር የአምናው የሌቫን አሸናፊ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዘንድሮ በርቀቱ 3: 53.09 ሪከርዱን ጭምር በመስበር አሸናፊ ሆናለች። ከቀናት በፊት የአለም አትሌቲክ ፌዴሬሽን ባሳወቀው መሠረት ያለፈው ከ20 አመት በታች በሌቫን ያሸነፈቸው የ1500ሜትር ውድድር አዲስ የአለም ሪከርድ ሆኖ እንዲመዘገብ የተደረገላት አትሌት ለምለም ሃይሉ በምሽቱ […]
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በቀናት ልዪነት ሌላኛውን ድል ደግማለች !
ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ላቪስ በተደረገው የ1500 ሜትር የቤትውስጥ ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት በገንዘቤ ዲባባ ለ7አመት ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ የሰበረችው ጀግናዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዛሬ ደግሞ በ 800 ሜትር በቁጥሬ ዱለቻ እ.ኤ.አ 1999 ተይዞ የነበረውን የ800ሜትር 1 :59.17 በማሻሻል 1: 57.52 አዲስ የአለም ፈጣኑን ሰአት አስመዝግባለች።