የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮዽያዊያን የሚሳተፉበት ውድድር ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 27/2013 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ይደረጋል።በዚህ ርቀት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከ1ኛ – 4ኛ ወጥተው ባመጡት ፈጣን ሰአት እንደሆነ ይታወቃል። በአንፃሩ በ5ሺህ ሜትር በተደጋጋሚ በአጨራረስ የሚታወቀውና በርቀቱ ስመጥር የሆነውን የዓለም ድንቅ አትሌት ሞህ ፋራን ጭምር ያሸነፈው ሙክታር እንድሪስ በሀገር ውስጥ […]
አትሌቲክስ
– አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5 ሺ ሜትር ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል !
ትላንት ምሽቱን ወደ ቶኪዮ ያመራው 4ኛዙር የኢትዮዽያ ልዑካን ቡድን ቶኪዮ በሰላም መድረሱ ታውቋል። በአራተኛ ዙር ትላንት የተጓዘው የወንዶች 5000 እና 1,500 ሜትር የያዘው የኦሎምፒክ ቡድን መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ለዑካን ወስጥ የነበረው እና በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝርዝር ያልተካተተው ሙክታር እድሪስ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ጥረት ወደ 5 ሺ እንዲገባ ተደርጓል ። በዚህ መሠረት ውጤታማው ድንቅ አትሌት ሙክታር እድሪስ በ5ሺህ […]
“ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ የታላላቆቼን ምሩፅ ይፍጠር፣ሀይሌ ገብረ ስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለን ታሪክ በመድገሜ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ ” – አትሌት ሰለሞን ባረጋ
በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት ከ13 ዓመት በኃላ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያሰገኘ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል። ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አፈትልኮ በመውጣት ርቀቱን በ27:ከ43.22 በሆነ ጊዜ በአስገራሚ መልኩ ማሸነፍ ችሏል። በውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ዮጋንዳውያኑ አትሌቶች […]
– ምድብ ሁለት አትሌት ጌትነት ዋለ
አትሌት ጌትነት ዋለ በቶኪዮ በኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ ሩጫን በልጅነቱ 4 ኪ.ሜ ወደ ትምህርት ቤቱ በመሮጥ የጀመረው አሁን ላይ በኦሎምፒክ መድረክ በውጤት ከሚጠበቁ አንዱ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ በ13 ዓመቱ ወደ ሩጫው ዓለም እንደገባ ሲነገር በወቅቱ በ 1500 ሜትር እና በ 3000 ሜትር ርቀቶች በክልል ሻምፒዮና ላይ ያሳየው ውጤት አሰልጣኝ ተሾመ […]
በምድብ 1 : ተወዳዳሪ አትሌት ለሜቻ ግርማ
የዛሬ ሌሊት 3ሺ ሜትር የወንዶች መሠናክል ማጣሪያ ከሌሊቱ 9 :30 ሰዓት ይጀመራል . አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክ በዶሀ የአለም ሻንፒዮና ላይ የብር ሜዳሊያ ማግኘት የቻለ ወጣት አትሌት ነው። በቅርቡ በሞናኮ ተካሄዶ በነበረው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኬኒያዊያንን አሸንፎ የአመቱን ፈጣን ሰአት አስመዝግቦ ማሸነፉ ይታወሳል። አትሌቱ በአሁን ሰዓት በርቀቱ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው አትሌቶች አንዱ ነው። ምንም […]
– ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ቱፋ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ ዲፕሎማ አስገኘ!
በወርልድ ቴኳንዶ ድንቅ ብቃትን በማሳየት ለኦሎምፒክ ውድድሩ ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ጃፓን ያቀናው ወጣት ሰለሞን ቱፋ በኢትዮዽያ የኦሎምፒክ ታሪክ በ7ተኛ ደረጃ በመጨረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል። ሰለሞን ቱፋ ደም ደምሴ በውድድሩ ዲፕሎማ በማግኘት አዲስ ታሪክ ያስመዘገበ ቀዳሚ ሆኗል ። ወጣት ሰለሞን ቱፋ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያውን በ58 ኪ/ሎ ግራም ከጃፓኑ ሱዚኪ ሰርጂዮ ጋር ተጋጠመው በጥሩ የአጨዋወት ስልት ሶሎሞን […]
– ወደ ቶኪዮ ዛሬ ተጓዥ ከሆነው ሁለተኛ ዙር ውስጥ ሦስት ሰዎች ከኤርፖርት ተመላሽ ሆነዋል!
በቶኪዮ 2020/2021 ኦሎምፒክ ኢትዮዽያን አትሌቲክስ የሚወክሉ እና የሁለተኛ ዙር ተጓዞች ዛሬ ምሽት ወደ ጃፓን አምርተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ከሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገፁ ይፋ ካደረገው ተጓዥ ስም ዝርዝር ውስጥ ሦስት የልዑካን አባላት ኦሎምፒክ ለመሄድ ኤርፓርት ደርሰው ከኤርፓት ተመላሽ ተደርገዋል ። በፌዴሬሽን ብዙም ግልፅ ባልሆነው አሰራር አትሌት አላያም የህክምና ባለሞያ ወይም ልዑካን ወደ ቶኪዮ መሄዱን አልያም […]
ሰለሞን ቱፋ ከ ሩሲያዊው ጋር ለነሀስ ይጫወታል !
የጃፓኑን ተጋጣሚው ሰርጅዮ ሱዙኪ በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፈው ሰለሞን ቱፋ ደምሴ በቱኒዚያው ተፎካካሪው በነጥብ ልዩነት ቢሸነፍም የተሻለ ነጥብ ስላስመዘገበ ለነሀስ ሜዳሊያ ይጫወታል። ሰለሞን ቱፋ ከ ሩሲያዊው አርታሞኖቭ ሚኪሀሊ ጋር ነው የተገናኘው። ሰለሞን የሚያሸንፍ ከሆነ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ታገኛለች። @EOC Olympic
ቶኪዮ ከተጓዘው ከ100 በላይ የኦሎምፒክ ልዑካኑ ግማሹ ያህሉ ጥያቄ እያስነሳ ይገኛል!- አትሌቶች ተቀንሰው ለምን ልዑካኑ በዛ?
የ32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮሮና ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቶ ነገ በታዋቂው የጃፓን አርክቴክት ኬንጎ ኩማ በተሠራው ባለ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በፈጀው እና 68ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ያለ ተመልካች በሚደረግ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በይፋ ይጀመራል። በታሪካዊው እና ተጠባቂው የቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮዽያን ባንድራ በመከፈቻው ስነስርዓት ላይ ከፍ ለማድረግ ትላንት የተጓዘው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ከስድስት ሰአታት ቆይታ በኃላ […]
-በቶኪዮ አየር ማረፊያ ለስድስት ሰዓታት ታግዶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኮቪድ ነፃ ሆነ !
ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ ኮሮና ምክንያት ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ተዘግቦ ነበረ ፣ይሁንና አሁን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑካን ቡድን ከቶኪዮ አየር ማረፊያ ወጥቶ ወደ ተመደበለት ቦታ መግባቱን የቡድኑ መሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ገልጸዋል። ነገ በሚጀመረው 32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ […]