በዓለም የማራቶን ውድድሮች ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው አንዱ የሆነው ቺካጎ ማራቶን ለ45 ኛ ጊዜ ነገ ይካሄዳል። ከ6 ዋና ዋና አለም አቀፍ ማራቶኖች መካከል አንዱ የሆነውና በ5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቺካጎ ማራቶን ላይ በሁለቱም ፆታ የዓለማችን ድንቅ አትሌቶች የሚወዳደሩ ሲሆን በውድድሩ ላይ ደግሞ ከ45 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችም ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በነገው ውድድር ከሚጠበቁ አትሌቶች በሴቶች አትሌት ገንዘቤ […]
አትሌቲክስ
#ኢትዮጵያዊው ጀግና ሪከርዱን ሰብሮ አሸንፏል
ኢትዮዽያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በምሽቱ የፖሪስ ዳይመንድ ሊጎ የ3000 ሜትር መሰናክል የአለምን ክብረወሰን በማሻሻል በ 7:52:12 ሪከርዱን ሰብሮ ቃሉን አሳክቷል ። የአርሲዋ ቦቆጂ የ5000 ሜትርና የ10,000 ሜ ክብረወሰን የሚያሻሽሉ ብቻ ሳይሆን ተምዘግዛጊ የ3000 ሜ መሰናክል ጀግናም ማፍራት እንደምትችል አሳይቷል።
ኢትዮዽያዊያን አትሌቶች በዳይመንድ ሊግ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል!
Rabat Diamond League 2023 From Abdu Muhammed በሞሮኮ ራባት ዳይመንድ ሊግ የ1500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያን እንስት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። በውድድሩን ጉዳፍ ፀጋዬ በ3:54.03  በቀዳሚነት ስታሸንፍ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ብሪኪ ሃይሎም እና ወርቅነሽ መሠለ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
#በካናዳ ኦትዋ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል!
From Abdu Muhammed በዘንድሮው ኦትዋ ኢንተርናሽናል ማራቶን በወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሎቶች አሸንፈዋል። በወንዶች ወደፊት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ይሁኝልኝ አዳነ በ 2፡08፡22 በመግባት አንደኛ ሲሆን ገብረጻዲቅ አብርሃ በ 2፡09፡13 በሁለተኝነት ፣ አብዲ አሊ ገልቹ በ 2፡10፡38 ሶስተኛ አሸንፈዋል። በሴቶቹ ቀዳሚ ሆና የገባችው ዋጋነሽ መካሻ ስትሆን ካናዳዊቷ ኤልሞር 2ኛ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ጀርመናዊ የሆነችው ሜላት […]
#በመጀመሪያው ቀን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል
From Abdu Muhammed በዛምቢያ ንዶላ በሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ የተጓዘው እና በትላንትናው እለት መጉላላት አጋጥሟቸው የነበሩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የታዳጊዎችና የወጣቶች ቡድን በመጀመሪያ ቀን ድል ቀንቶታል በውጤቱም በ3,000 ሜ ሴቶች ከ20 አመት በታች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ሜዳልያውን ጠራርገውታል። አስማረች አንለይ 1ኛ ሆና ወርቅ፣ የኔዋ ንብረት […]
#የቶኪዮ ማራቶንን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል አድርገዋል!
From Abdu Muhammed የ2023 የቶኪዮ ማራቶንን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በወንዶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት ሲያሸንፉ በተመሣሣይ በሴቶች ከ2ኛ – 4ኛ ደረጃን በመያዝ አሸንፈዋል። የወንዶች ውጤት 1ኛ -ጫሉ ዲሶ (2:05:22) 2ኛ- ኢሳ መሀመድ(2:05:22) 3ኛ-ፀጋዯ ከበደ (2:05:25) የሴቶች ውጤት 2ኛ -ፀሀይ ገመቹ( 2:16:56) 3ኛ- እሸቴ በክሪ (2:19:11) 4ኛ- ወርቅነሽ ኦዴሳ(2:19:11) […]
ኢትዮዽያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በፈረሳይ በተካሄደው የቤትውስጥ 3000ሜትር ውድድር የአለምን ሪከርድ 7:23;81 ሰብሮታል !
From Abdu Muhammed ኢትዮጵያዊው ላሜቻ ግርማ አርማንድ ሞንዶ ዱፕላንቲስ በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ያስመዘገበውን የአለም የ3,000ሜ የቤት ውስጥ ክብረ ወሰን በሊቨን ውድድር ከአንድ ሰከንድ በላይ ሰበረ። ኢትዮዽያዊው አትሌት ላሜቻ ግርማ 7 ደቂቃ ከ23.81 ሰከንድ በመግባት በኬንያዊው ዳንኤል ኮመን በቡዳፔስት የካቲት 1998 ባስመዘገበው የ 7 ደቂቃ ከ24.90 ሰከንድ የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል። ኢትዮጵያዊው በመዝጊያ አራት ዙር ብቻውን በመሮጥ […]
#የ44ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ አሸኛኘት ተደረገለት!
በአውስትራሊያ – ባትረስ ከተማ እ.አ.አ ፌብሪዋሪ 18/2023 በሚካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎች በ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተመልምለው ሆቴል ገብተው ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሸኛኘቱ ዛሬ በተከናወነ መርኃ ግብር በስዊስ ኢን ኔክሰስ ሆቴል በድምቀት ተካሂዷል። አትሌቶች የኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነውን ሰንደቅ አላማ በአደራ ተረክበዋል።
#ኢትዮዽያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል!
በፈረንሳይ ደ ሞንዴቪል ዛሬ በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 1500ሜትር የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉዋል። በውድድሩ አያል ዳኛቸው 4:11:00 በመሮጥ ቀዳሚ ስትሆን ፣ትግስት ከተማ ሁለተኛ ሲንቦ 3ኛ እንዲሁም ትዕግስ 4ኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል። በተመሳሳይ በፖላንድ ኦርለን ኮፐርኒከስ ዋንጫ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር በ3000ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ተከታትለው […]
# ከዕድሜ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከ250 በላይ አትሌቶችን ማገዱን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ
#ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ ፌዴሬሽኑ መጠየቅ ይኖርበታል! 👇 ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከዕድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ መሠረት ከውድድር ውጭ መሆናቸውን የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል። […]