ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ቀጣይ አስተናጋጅ ድሬዳዋ እንግዶቿን በድምቀት መቀበሏን ቀጥላለች !

የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያ በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል። በቀጣይ ሳምንት ከ17ኛ ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት የምታስተናግደው አራተኛዋ የቤት ኪንግ  ፕሪምየር ሊግ አስተናጋጅ የድሬዳዋ ከተማ ትሆናለች ። ድሬዳዋ  የቤት ኪንግ  ፕሪምየር ሊግ  ለመጀመሪያ ጊዜም  በምሽት ጨዋታዎቹን ለማስተናገድ የስታድየም መብራቶች እና የስታዲየም እድሳቶችን በማድረግ አዘጋጇ ከተማ ዝግጅቷን አጠናቃለች ።   አሁን  ላይ ደግሞ […]

ዜናዎች

ለዋልያዎቹ የተዘጋጀው ደማቅ አቀባበል እና ሽልማት ነገ ረፋድ ይቀጥላል !– የዛሬውን አዳር ጁፒተር ሆቴል ያሳልፋሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫን ከስምንት ዓመታት በኃላ ዳግም እንዲቀላቀል ያስቸለው ልዑካን ቡድን ከአቢጃን ኮትዲቯር በኢትዮዽያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላ አየር ተንስቶ ከአምስት ሰአት ተኩል በረራ በኃላ ምሽቱን ቦሌ የአየር ማረፊያ ደርሷል። ከአርባ በላይ የብሔራዊ ቡድኑ ልዑካን ቡድን የያዘው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ምሽቱን ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስ ዶ/ር ሂሩት ካሳ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር፣ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ […]

አፍሪካ ዜናዎች

ጋናዊው የመሀል ዳኛ ቻርለስ ቡሉ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ !

በአቢጃን ትላንት የተደረገውን የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ አቻቸው ያደረጉትን የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩት የጋናዊው ዳኛ ቻርለስ ቡሉ በ81ኛው ደቂቃ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ይታወሳል።የትላንቱ የኮትዲቯር እና የኢትዮጵያ ጨዋታ ሊጀመር 3 ሰዓት ሲቀረው የእለቱ ዋና ዳኛ ጋናዊው ዳንኤል በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ የጨዋታው ኮሚሽነር ከካፍ ጋር በመነጋገር 4ኛ ዳኛው ጨዋታውን የመምራት ሚና […]

ዜናዎች

” በአፍሪካ ዋንጫ በማለፋችን በጣም ነው የተደሰትነው ፣ደስታው ለእኛ ለኢትዮዽያዊያን ከኳስም በላይ ነውና” ➖ያሬድ ባዬ

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ 2ኛ በመሆን ለ33ኛው የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ከሱዳንን ጋር ማለፏን አረጋግጧል። ዛሬ በአቢጃን ላይ ከኮትዲቯር አቻቸው ጋር የተጫወቱት ዋልያዎቹ 3ለ1 በሆነ ውጤት እስከ 83ኛው ደቂቃ ተመርተው የነበረ ቢሆንም በመሀል ዳኛው ድንገተኛ የጤንነት ችግር ጨዋታው በመቋረጡ እና በውጤቱ መሠረት ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል።በዛሬው ጨዋታው በዋልያዎቹ በኩል የመጀመሪያው ጎል የተቆጠረው ከጥንቃቄ ጉድለት […]

ዜናዎች

የዋልያዎቹን የዛሬ ጨዋታ ለመደገፍ 11 ኢትዮጵያዊያን ጉዞ ወደ አቢጃን ጀመሩ ! – ቴዲ አፍሮ ደጋፊዎቹ ወደ አቢጃን እንዲሄዱም ረድቷል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሁለተኛ ሆኖ ለማለፍ ዛሬ የመጨረሻውን እና ወሳኙን ፍልሚያ አቢጂያን ከኮትዲዮቫር አቻው ጋር በ10 :00 ሰዓት ያደርጋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ጉዞ ለማለፍ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አልያም አቻ መውጣት እና አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘት ለማለፍ በቂው ነው።በአንፃሩ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲዮቫር ከተሸነፈደግሞ በምድቡ በመጨረሻ ደረጃ የምትገኘው እና መውደቋን […]

ዜናዎች

“ከስምንት ዓመት በፊት የአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ፕሮጀክት ኦኜ ነበር በቴሌቪዥን ስመለከት የነበረው ዘንድሮ በተራዬ በዋልያዎቹ እገኛለሁ” ➖ሱሊማን ሀሚድ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዋናው የዋልያዎቹ ስብስብ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተካተተው እና ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻው 90 ደቂቃዎች ፍልሚያ አቢጂያን የሚገኘው ወጣቱ የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋች ሱሊማን ሀሚድ አንዱ ነው። የዋልያዎቹ የአሁኑ የኃላ መሥመር ደጀን ሱሊማን ሀሚድ ከዛሬ ስምንት አመት በፊት ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ የዋንጫን ከሶሰት አሰርት አመታት በኋላ ሲቀላቀል እሱ ያኔ የ15 አመት ታዳጊ እና […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ዲ.ኤስ.ቲቪ ቀጣይ ስርጭቱን የሚካሄድባት ድሬ ደርሷል!

የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ አዘጋጅ ከተማ ድሬዳዋ ዝግጅቷን የጨረሰች ይመስላል። ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግን  ጨዋታዎቹ በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈው የሱፐር ስፖርት ተንቀሳቃሽ መኪናዎች ከባህርዳር ከተማ ወደ ድሬ  ገብተዋል።  ተንቀሳቃሽ የቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮ እና የካሜራ ባለሙያዎች ቡድን የመጀመሪያው ልዑካኑ ድሬዳዋ ገብቷል። የፊታችን እሑድ መጋቢት 27 ጀምሮ በድሬዳዋ የቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ በቀጣይ ቀናት ቀሪ የዲ ኤስ […]

Derartu Tulu
አትሌቲክስ ዜናዎች

ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ዛሬ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ! – ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና መርሀ ግብር ዛሬ መጋቢት 19/2013 ከቀኑ 10 : 00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብሩን ምክንያት አስመልክቶ ከቀናት በፊት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተጠቆመው ጀግናዋ አትሌት በስፖርቱ አለም ላበረከተችው በርካታ ተግባራት አስተዋፅ እና እውቅና በመስጠት መጪውን ትውልድ ማነቃቃት መሆኑን የኮሚቴው አባል የሆኑት አትሌት ገዛህኝ አበራ […]

አፍሪካ ዜናዎች

የቀድሞ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ የጋናው አሳንቴ ኮቶኮ አዲስ አሰልጣኝ ሆነዋል !

ፖርቱጋላዊው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የጋና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ማሪያኖ ባራቶን የጋናው አሣንቴ ኮቶኮ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ  ሆነዋል።የጋናው ክለብ ከወራቶች በፊት ማክስዌል ኮናዱን ካሰናበተ በኃላ ፖርቱጋላዊውን ማሪያኖ ባራቶ በቦታው መተካቱ ሲሰማ አሰልጣኙም ወደ ጋና መድረሳቸው ታውቋል ፡፡ፖርቱጋላዊው ማርያኖ ባሬቶ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የዋና የአሰልጣኝነት ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት በረዳት አሰልጣኝነት ዳይናሞ ሞስኮ ፣ […]

ዜናዎች

የአይቮሪኮስት አና የኢትዮጵያን ጨዋታ ጋናዊው የመሀል ዳኛ ይኖሩታል !

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከአይቮሪኮስት አቻቸው ጋር የመጨረሻውን የማጣሪያ ጨዋታው የፊታችን ማክሰኞ ያካሂዳል። ይህንን ጨዋታ ጋናዊው ኢንተርሽናል አርቢትር ዳንኤል አዬ ላሪያ ይመሩታል። የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂውን ጨዋታውም 60,000 ተመልካች የመያዝ አቅም ባለውና እግር ኳስ ፣ ራግቢ እና አትሌቲክስ በሚያስተናግደው በስታድ ዲ ኤቢምፔ ሁለገብ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታውን ክጋናዊው ኢንተርሽናል በዋና ዳኝነት ዳንኤል […]