ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ለሲዳማ ቡና በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ ፣ ቀጣይ ጨዋታዎች ከቡድኑ ጋር በድል ለማሸነፍ እነጥራለን” “➖ ፋቢየን ፋርኖል

የሲዳማ ቡና ስፓርት በቅርቡ ካስፈረማቸው የውጭ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የቤኒን ብሔራዊ ተጨዋቾች የሆነው ግብ ጠባቂ ፋቢየን ፋርኖል ይጠቀሳል። በቀድሞ በፈረንሣይ ቦርዶ የተወለደው እና በቅርቡም የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፋቢያን የመሠለፍ ዕድልም አግኝቷል። ቤኒናዊው የ36አመቱ ግብ ጠባቂ ፋቢያን በዛሬው ምሽት ጨዋታ ለሁለተኛ ጊዜ ተሰልፎም ተጫውቷል ።ቡድኑም ማሸነፍ ችሏል ። አዲሱ የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ዋንጫው ባይሳካም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውስጥ ብንገባ ደስ ይለኛል “- በረከት ወልዴ ( ወላይታ ድቻ )

ወላይታ ድቻ የ18ኛ ሳምንት ውጤቱን ድሬደዋ ከተማን 3 ለ 1 በማሸነፍ በድል አጠናቋል።በዛሬው ጨዋታ ለወላይታ ድቻ ከተቆጠሩት ጎሎች የመጨረሻዋን እና ወሳኟን ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ወጣቱ የአማካኝ ተጨዋች በረከት ወልዴ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። የዛሬውን ጨዋታ በተመለከተ “አረፍ ነበረ። ውጤቱ ስለሚያስፈልገን እና እነሱም ወደ ላይ ከፍ እንዳይሉ እና ለእኛም ውጤቱ አስፈላጊ ነበር። ስለዚህ 6 ነጥብ […]

ዜናዎች

ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር 2ኛውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ ያደርጋሉ !

የኢትዮዽያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከ ደቡብ ሱዳን የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አቻቸው ጋር ሁለተኛውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያካሄዱ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። እንደሚታወሰው ቡድኑ የኢትዮዽያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ የደቡብ ሱዳን የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን 11 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የእኔ ጊዜ ይመጣል በሚል ጠብቄ ነበር ፤ አሁን የኔ ጊዜ ነው ማለት እችላለሁ ” አቡበከር ኑሪ

የ18ኛው ሳምንት የዛሬው የምሽቱ የሃዋሳ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር  ጨዋታ  በ1ለ1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል። በጨዋታው ላይ ከታዩ የሁለቱ ቡድኖች የመሸናነፍ እንቅስቃዎች በተጨማሪ በጅማ አባጅፋር በኩል ወጣቱ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪ በርካታ ዒላማቸውን ወደ ጎል የነበሩ ኳሶችን በግሩም ብቃት ተቆጣጥሮ ጎለ ከመሆን በማዳን የጨዋታው ትኩረት ያገኘ ተጨዋች ነበር ።ከጨዋታው በኃላ አቡበከር ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“አላህ ካለ እሰብረዋለሁ ብዬ አስባለሁ” አቡበከር ናስር

በ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አቡበከር ናስር የጎል መሪነቱን 22 ያደረሰው አቡበከር ናስር በዛሬው ለኢትዮጵያ ቡና ሁለት የማሸነፊያ ጎሎችን አስቆጥሯል። ከጨዋታው በኃላ አቡበከር ናስር ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል የዛሬው ጨዋታ እና ስላ ስቆጠራቸው ሁለቱ ጎሎኖች? ” እኛ ውጤቱ ያስፈልገናል ምክንያቱም ከመሪውም በጣም እረቀናል እና ውጤት ስለራቅን ግድ ማሸነፍ ነበረብንና አላህ ብሎ አሸንፈናል። ድሬ ያበቀለችው ዮርዳኖስ […]

ዜናዎች

“ሲዳማ ቡናን በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ ፣ በቀጣይ ጨዋታዎች ሲዳማ ቡናን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ነው ፍላጎቴ” -ኦኪኪ አፎላቢ

ናይጄሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ በ2010 ዓ.ም ጅማ አባ ጅፋር የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ በ23 ጎሎች የሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪም በመሆን ይታወሳል። ተጨዋቹ በጅማ አባጅፋር ክለብ ከመጀመሪያው ስኬቱ በኃላ ወደ ግብፅ በማምራት ለግብፁ ኢስማዒልያ ኤስ ሲ ጋር ቢ ያልተሳካን ጊዜ አሳልፎ ወደ ጅማ አባጅፋር ቢመለሰም በዝውውር ሂደቱ ወቅት ለፊርማ በማስመሰል  ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 6 ወር ዕገዳና […]

ዜናዎች

ሉሲዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን በሰፋ የጎል ልዩነት አሸነፉ !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ምሽቱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው የመጀመሪያው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ተጋጣሚውን 9 ለ 0 አሸንፏል።በዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚሰለጡንት ሉሲዎቹከደቡብ ሱዳን ያደረጉት ጨዋታ ከእረፍት በፊት አምስት ጎሎች በማስቆጠር በተጋጣሚያቸው ላይ የበላይነቱን ይዘዋል። ጎሎቹን በስምንተኛው ሴናፍ ዋቁማ ፣ወዲያው በደቂቃ ልዩነት ሎዛ አበራ ፣ በ18ኛው ደቂቃ ሎዛ አበራ የግሏ ሁለተኛውን […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሌጎስ ማራቶን በማሸንፍ ከፍተኛውን ሽልማት አግኝተዋል !

በምዕረብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ለስድስተኛ ዛሬ ረፋድ በተካሄደው እና DSTVን  ጨምሮ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አግኝቶ በነበረው ” Access Bank Lagos City Marathon 2021 ” የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን  ከፍተኛውን ሽልማት በማግኘት ውድድሩን አጠናቀዋል። በሴቶች የ 42 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮዽያዊቷ መሰረት ዲንቃ በ2:28.53 አሸናፊ በመሆን 30,000 ዶላር ተሸላሚ ስትሆን ኬኒያዊቷ ችሊስታይን ጄፕቺር በሁለተኝነት 20,000 ዶላር እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የተባለው የኮቪድ ነገር ውሸት ነው ብዬ ነው የማስበው፤ ሁላችንም ላይ ትንሽ የአዕምሮ ተፅኖ ፈጥሮብናል”➖ሐብታሙ ገዛኸኝ

የሲዳማ ቡና ዛሬ ተጋጣሚውን አዳማ ከተማን 3ለ 0 አሸንፎ ወጥቷል። ከተቆጠሩት ሶስት ጎሎች ሁለተኛዋን ሀብታሙ ገዛኸኝ ነበር ያስቆጠረው ። በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ የሀብታሙ ወንድም ባዬ ገዛኸኝ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤን ሁለት ለባዶ ሲያሸነፍ አንዷን  ጎል ያስቆጠረ ተጨዋች ነበር። በተመሳሳይ ሀብታሙ ገዛኸኝ በምሽቱ ጨዋታ ጎል ቀንቶታል። ተጨዋቹ ከሱፐር ስፓርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጎ […]

ዜናዎች

“ከሁለት ቆንጆ ሴቶች አንዱን ምረጥ እንደማለት ነው ፤ ሁለቱም ውብ ናቸው“ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ

የ17ኛውን ሳምንት ጨዋታ በድል የተወጣው የባህርዳር ከተማ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ  አድርጓል። ከሁለቱ ጎሎች የትኛውን ትመርጣለህ ለሚለው “ከሁለት ቆንጆ ሴቶች አንዱን ምረጥ እንደማለት ነው ፤ ሁለቱም ውብ ናቸው። ስለዚህ ሁለቱም ቆንጆ ናቸው ።” ጨዋታውን በተመለከተ እና በቀላሉ ጨዋታውን አሸንፈናል ብሎ ታስባለህ ለሚለው ? “አልልም። የመጀመሪያው ጎል ለማስቆጠር ረጅም ደቂቃ […]