ዜናዎች

የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋቾች የቅድመ ውድድር ጤና ምርመራ ሊጀመር ነው !

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ተመዝግበው በፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ ውድድር የሚጫወቱ ተጫዋቾች የ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት ተጫዋቾች የጤና ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ከአሁን በፊት ተጫዋቾች ከክለብ ክለብ ሲዘዋወሩም ሆነ ውል ሲያድሱ የጤና ምርመራ እንዲያደርጉ የሚያስችል አስገዳጅ ህግ ባለመኖሩ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ለችግር ሲዳረጉ ተስተውሏል፡፡ የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር […]

ዜናዎች

የባህርዳሩ የሴካፋ ዋንጫ ተካፋይ ዮጋንዳ ሁለተኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ዛሬ ያደርጋል !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሐምሌ 10/2013 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያስታወቀው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተካፋይ የሆነው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አቋማን በወዳጅነት ጨዋታ እያጠናከረ ይገኛል። በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ጠንካራ ቡድንና በተደጋጋሚ ሻምፒዮና የሆነው የዮጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት ሳውዲ አረቢያ የተጓዘ ሲሆን ባለፈው ዓርብ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ከሳውዲ አረቢያ ከ23 […]

ዜናዎች

ሀዲያ ሆሳዕናንሙሉጌታ ምህረትን አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ ! – ለሁለት ዓመት ፈርሟል

በ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር በጠንካራ ተፎካካሪነት የውድድር ዓመቱን በአራተኝነት ያጠናቀቀው ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የውል ስምምነታቸው ከማጠናቀቃቸው በፊት አሰናብቶ ዶክተር እያሱ መርሐፅድቅ አሰልጣኝ አድርጎ የውድድር ዓመቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።  ከዚህ በተጨማሪም ክለቡ ከክፍያ ጋር በተያያዘ በርካታ ተጨዋቾችን ከአሰልጣኝ አሸናፊ መሠናበት  ጋር ማጣቱም አይዘነጋም።  ሆኖም  ክለቡ የታዳጊ ቡድኑን ተጨዋቾች ወደ ዋናው በማዘዋወር  የውድድር ዓመቱን በጥሩ ተፎካካሪነት አጠናቋል። […]

ዜናዎች

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ከክለቡ መለያየቱን አስታወቀ !- ከአደጋው በኃላ የጅምናዚየም እንቅስቃሴ ጀምሯል !

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የ33 ዓመቱ ፓትሪክ ማታስ ከአንድ ወር በፊት ከደረሰበት  አሰቃቂ የመኪና አደጋ በኃላ  አገግሞ  እንደተናገረው  በቀጣይ ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር  እንደማይቀጥልና ከክለቡ መለያየቱን አስታውቋል። ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትሪክ ማታስ ከአንድ ወር በፊት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ሙሉ ቤተሰቡን መጎዳቱ ይታወሳል። ተጨዋቾቹ ከአደጋው በኋላ  የመላው  ቤተሰቡ ሕይወት መትረፉ […]

ዜናዎች

– ኢትዮጵያ ቡና ከነገ ጀምሮ አዳዲስ ተጨዋቾች ያስፈርማል ፣ የጨረሱትንም ውል ያድሳል !

የዘንድሮ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሐምሌ 1/2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቀድሞ ቢያሳውቅም ትላንት በተረጋገጠው መረጃ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ካፕ ለሚሳተፉ ክለቦች የዝውውር መሥኮቱ ከመከፈቱ በፊት ቀደም ብሎ ማካሄድ እንደሚችሉ መፈቀዱ ተዘግቧል። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከነገ ጀምሮ አዳዲስ ተጨዋቾች የሚያስፈርም እና ውል የጨረሱትንም ተጨዋቾች ውላቻውን የማደስ ሂደቶች እንደሚጀምር […]

ዜናዎች

እስራኤል አቅንቶ የነበረው ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ትላንት ተመልሷል! – ሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል !

ወደ እስራኤል አቅንቶ የነበረው  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ልዑካን ቡድን  እና ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከእስራኤል አቻቸው ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ እና አበሮ የመስራት ስምምነት አድርጎ  ትላንት ተመልሷል። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በአቶ ኢሳያስ ጅራ እና በዋና ፀሀፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን የተመራው የልዑካን ቡድን ከእስራኤል እግር ኳስ ማህበር ጋር የተሳካ ጅምር አብሮ የመስራት […]

ዜናዎች

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል!

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች የወንዶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር 11 የሴካፋ አባል ሀገራትን እና ተጋባዧ ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎን ያሳተፈ ነው። በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያን የወከለው ከ23 ዓመት በታች የተስፋ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ ሐሙስ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ባህር ዳር […]

ዜናዎች

የፌዴሬሽን ኃላፊዎች በእስራኤል :- ከትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጨዋች እና የመብት ተሟጋች ጋር ተገናኙ !

  በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ በፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንና  የፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች የታከሉበት የልዑካን ቡድን በእስራኤል የተሳካ የወዳጅነት ግንኙነት ለማድረግ ባለፈው እሁድ ቴላቪቭ መድረሳቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ እና በእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች መካከል ከረጅም ወራቶች በፊት በሀሣብ የነበረው ጅማሮ አሁን ተሳክቶ የወዳጅነት የእግርኳስ ጨዋታ እና በሁለቱ አገራት የትብብር […]

ዜናዎች

” የመጨረሻው ዕድላችንን ይሄ ብቻ ስለሆነ ያለንን ነገር ለጅማአባጅፋር ለመስጠት ዝግጁ ነን ” ወንድማገኝ ማርቆስ(ቾንቤ)

የጅማ አባጅፋሩ የቀኝ መሥመር ተጨዋች ወንድማገኝ ማርቆስ(ቾንቤ) በክለቡ ደጋፊዎች ተወዳጅ  ከሆኑ ተጨዋቾች አንዱ ነው። የወንድማገኝ ቡድን ጅማ አባጅፋር በ2013 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ያጠናቀቀው በደረጃ ግርጌ ውስጥ ከሆኑ ሶስቱ ከወራጅ ክለቦች አንዱ ሆኖ ነው። በአንፃሩ የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2014 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችን በተመለከተ ባስተላለፈው የ2ኛ አማራጭ ውሳኔ የትግራይ ክልል ሶስቱ ክለቦች ባለመሳተፋቸው የወንድማገኝ እና ጅማ […]

ዜናዎች

የ2014 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ 6 ክለቦችን ለመለየት ዛሬ ዕጣ ማውጣት ይደረጋል !-የመጀመሪያ ቡድን ባህርዳር ደርሷል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰኔ 1/2013 ዓ.ም አስተላልፎት በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ በ2ኛ አማራጭ የትግራይ ክልል ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የማይመዘገቡ ከሆነ በሚል በአማራጭ ያዘጋጀው የጥሎ ማለፍ ውድድር የፊታችን ሰኔ 18/2013 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ይጀምራል። ስድስት ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ዛሬ  ይካሄዳል። በ2013  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሊጉ […]