ቀጥታ ዜናዎች

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 1ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነስርዓት ኮሚቴ ዛሬ መስከረም 24/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል። በተጫዋቾች ኤልያስ አህመድ(ድሬደዋ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

” ለንደን የመጣሁት ለማሸነፍ ነው “አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እሁድ ከሚደረገው የለንደን ማራቶን አስቀድሞ በሰጠው አስተያየት አሁንም የረጅም ርቀት ታላቁ አትሌት መሆኑን ገልጿል። የ 40ዓመቱ ታሪክ አይሽሬው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሶስት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ፣ 17 የሀገር አቋራጭ ክብሮች እንዲሁም የ 5,000 እና 10,000ሜትር ሪከርድን ለአስራ አምሰት እና አስራ ስድስት ዓመታት የግሉ አድርጎ አቆይቷል።   ” ራሴን ከኪፕ ቾጌ ጋር ማፎካከር […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ወደ ግብፅ ሊያመራ የተነገረለት አማኑኤል ከፈረሰኞቹ ጋር ውሉን አራዝሟል !

አጥቂው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር ተለያይቶ ወደ ግብፅ ሊግ ለመጫወት ከጫፍ ደርሷል ቢባልም ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያቆየውን የአንድ ዓመት ፊርማ ዛሬ አኑሯል ።

ዜናዎች

የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ የ16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለ7ኛ ጊዜ አንስተዋል!

በደማቅ ስነ ስርዓት ፍፃሜውን ባገኘው 16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስጊዮርጊስ (ፈረሰኞቹ ) በደጋፊዎች የደመቀ ህብረ ዝማሬ በመታጀብ የዋንጫ ተጋጣሚውን መቻልን በመደበኛ ጨዋታ ባስቆጠሩት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል ። የ16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የተዘጋጀለትን ልዩ ዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከአዲስ አበባ […]

ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

#ኤርትራ በኢትዮዽያ ከሚካሄደው የሴካፋ ውድድር ራሷን አግልላለች !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 9/2015 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በስምንት ሀገራት መካከል ከሚካሄደው ከ17ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ኤርትራ ሪሷን አግላለች ። ከኢትዮጵያ ጋር በአንድ ምድብ የተደለደለችው ጎረቤት ሀገር ኤርትራ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ተረጋግጧል። የታዳጊዎች ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሀገር ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላ የነበረችው ከኤርትራ […]

ቀጥታ ዜናዎች

#መቻል እና ኤልፖ ለከተማው አስተዳደር ቅሬታቸውን አቀረቡ!

በመዲናዋ አዲስ አበባ የሚገኙ ክለቦች የሚሳተፉበት እና በመካሄድ ላይ የሚገኘው የ16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች መደረጋቸው ይታወሳል። በተለይም ለረጅም ወራቶች በአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት ምክንያት በቨገር ደርቢ በአዲስ አበባ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ የሰነበቱት ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ጨዋታ በአዲስ አበባ ዋንጫ በደጋፊያቸው ፊት በአበበ ቢቂላ ለመገናኘት ችለዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከመደረጉ […]

ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

#ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን የሚያደርገው ዛሬ ረፋድ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ በነፃ እንዲመለከቱ ጋብዟል!

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከሱዳን አቻው ጋር ዛሬ(ዓርብ ) ረፋድ በ4 :00 ሰዓት እና ሰኞ(መስከረም 16) በ10፡00 ሰዓት  ያከናውናል። በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረጉት ጨዋታዎችን በነፃ በመታደም ብሔራዊ ቡድናችንን እንዲያበረታቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥሪውን ያቀርባል። መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን  :- https://www.instagram.com/ethio_kick 🔛ድረ ገጻችንን  :- https://ethio-kickoff.com

ቀጥታ አፍሪካ ዜናዎች

# ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ በስቲያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዲ.ሪ. ኮንጎ ጋር ያደርጋል!

  በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ሲጀምሩ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ሐሙስ መስከረም 12 ዲ.ሪ. ኮንጎን አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ታስተናግዳለች። ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን ለማስፋት የእግርኳስ ቤተሰቡ ድጋፍ ያስፈልገዋል። በመሆኑም በዕለቱ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በነፃ በመታደም ለብሔራዊ ቡድናችን የሞቀ ድጋፋችሁን እንድትሰጡ […]

ቀጥታ ዜናዎች

ዳዋ ሁጤሳ እና ሐብታሙ ታደሰ 500 ካ.ሜ ቦታ ፣ የወርቅ እና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተላቸው !

ዛሬ በምዕራብ ጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ከተማ ለብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዳዋ ሆጤሳ እና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የሀድያ በአሁን ሰዓት ለባህርዳር ከተማ ለፈረመው ሐብታሙ ታደሰ ከስኬታማነታቸው ባሻገር ለሀገራችን እግር ኳስ እንዲሁም ለዞኑ ወጣቶች መልካም ዓርያ በመሆናቸው አባ ገዳ እና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ ደማቅ አቀባበል እና የማበረታቻ ሽልማትለእያንዳንዳቸውም የ 500 ካ.ሜ ቦታ […]

ቀጥታ ዜናዎች

➖የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሁለት ዓመት የ6 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንደሚያገኙ ተገለጠ!

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የቀጣይ ሁለት ዓመት የውል እድሳታቸው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ውድድር ተሳትፎ ማሳካቱን አስመልክቶ ዛሬ በካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ከኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን.ዋና ጸሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ጋር መግለጫ ሰጥተው የሚከተለውን ብለዋል የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣይ ሁለት አመት በየወሩ የተጣራ 250 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ስለመሆኑ የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን.ዋና ጸሃፊ አቶ […]