በአውስትራሊያ – ባትረስ ከተማ እ.አ.አ ፌብሪዋሪ 18/2023 በሚካሄደው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ 14 ወንድና 14 ሴት አትሌቶች ከነተጠባባቂዎች በ40ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ተመልምለው ሆቴል ገብተው ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሸኛኘቱ ዛሬ በተከናወነ መርኃ ግብር በስዊስ ኢን ኔክሰስ ሆቴል በድምቀት ተካሂዷል። አትሌቶች የኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነውን ሰንደቅ አላማ በአደራ ተረክበዋል።
ዜናዎች
የሸገር ደርቢ – በአቻ ውጤት ተጠናቋል !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ 1 – 1 ኢትዮጵያ ቡና 73′ ቸርነት ጉግሳ 43′ መሐመድኑር ናስር መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን :- https://www.instagram.com/ethio_kick ድረ ገጻችንን :- https://ethio-kickoff.com
#የድሬዳዋ ከንቲባ – መልካም ተግባር
አንጋፋው ኢንተርናሽናል ዳኛና የጨዋታው ኮሚሽነር ይድነቃቸው ዘውገ(ቦቼ) በደረሰበት የጤና ችግር ሀገር ውስጥ መታከም ባለመቻሉና ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም በሐኪሞች መወሰኑ እና የስፖርት ቤተሰቡን ድጋፍ መጠየቁ ይታወሳል። በዚህ መሠረት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በዛሬው ዕለት በአንጋፋው ኢንተርናሽናል ዳኛ ይድነቃቸው ዘውገ መኖሪያ ቤቱ ተገኝተው ጠይቀውታል፡፡ በኩላሊት ህመም ላይ የሚገኝው ይድነቃቸው ዘውገ /ቦቼ / ክቡር ከንቲባው […]
#ኢትዮዽያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል!
በፈረንሳይ ደ ሞንዴቪል ዛሬ በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 1500ሜትር የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉዋል። በውድድሩ አያል ዳኛቸው 4:11:00 በመሮጥ ቀዳሚ ስትሆን ፣ትግስት ከተማ ሁለተኛ ሲንቦ 3ኛ እንዲሁም ትዕግስ 4ኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል። በተመሳሳይ በፖላንድ ኦርለን ኮፐርኒከስ ዋንጫ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር በ3000ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ተከታትለው […]
#አሳዛኝ ዜና ዕረፍት
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ጅማ ላይ ተሳታፊው እንጅባራ ከተማ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጨዋች ተስፋፅዮን ፋንቱ (ደሮ) ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አምና በኢትዮ ኤሌክትሪክ በትልቅ ደረጃ መጫወት የቻለው አማካዮ በዘንድሮ የውድድር ዓመት እንጅባራ ከተማን በመቀላቀል በጨዋታ ላይ እያለ ባጋጠው የጭንቅላት ግጭት አደጋ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል። ተስፋፅዮን ፋንቱ ሥርዓተ ቀብር በነገው እለት […]
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ከ14ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን መካሄጃ ከተማና ስታዲየም በተመለከተ የስራ አመራር ቦርዱ ዛሬ ጥር 28/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ውድድሩን በድሬደዋ ወይም ባህር ዳር ከተማ ለማከናወን የፊታችን ሰኞ ጥር 29/2015 ዓ.ም ሜዳዎቹን የሚገመግም ኮሚቴ(ከቦርዱ እና ውድድርና ስነስርዓት […]
#የዛሬው ጨዋታ ተሰርዟል
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ዛሬ ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ አስታውቋል።
#ሰለ ነገው ሸገር ደርቢ / 2015 ተጨማሪ መረጃዎች
የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም * ትኬት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መሸጥ ይጀምራል። * የስታዲየም በሮች በተመሳሳይ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ። * የክቡር ትሪቡን በር በተዘጋጁ ልዩ ባጆች ብቻ የሚገባበት ሲሆን ጥላ ፎቅ 200 ብር ፣ ከማን አንሼ 100 […]
# ከዕድሜ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከ250 በላይ አትሌቶችን ማገዱን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ
#ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ ፌዴሬሽኑ መጠየቅ ይኖርበታል! 👇 ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከዕድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ መሠረት ከውድድር ውጭ መሆናቸውን የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል። […]
ለ45ኛ ጊዜ ሳንጃው ከ ቡንዬ የሚያደርጉት ስደተኛው ሸገር ደርቢ በቀዘቀዘ መልኩ ነገ ይካሄል !
ቀደም ባሉት አመታት ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በሚኖሩ ሳምንታቶች ብሎም ቀናቶች ጀምሮ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ደምቆ በጨዋታው ቀን ደግሞ ምሽት ለሚደረግ ጨዋታ ከሌሊት ጀምሮ ቦታ ለማግኘት ወረፋ የሚያዝለት እና የአዲስ አበባ ስታዲየም በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በተገኘው መድረክ ሲበዛ የሚደምቀው ሸገር ደርቢ ዘንድሮም በቀዘቀዘ መልኩ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ የፊታችን ቅዳሜ […]