ኢትዮዽያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በምሽቱ የፖሪስ ዳይመንድ ሊጎ የ3000 ሜትር መሰናክል የአለምን ክብረወሰን በማሻሻል በ 7:52:12 ሪከርዱን ሰብሮ ቃሉን አሳክቷል ። የአርሲዋ ቦቆጂ የ5000 ሜትርና የ10,000 ሜ ክብረወሰን የሚያሻሽሉ ብቻ ሳይሆን ተምዘግዛጊ የ3000 ሜ መሰናክል ጀግናም ማፍራት እንደምትችል አሳይቷል።
ዜናዎች
#በዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ቤትኪንግ ሊግ ይቋረጣል !
በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከማላዊ ጋር የሚያደርጉት የጨዋታ እየተቃረበ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የምድቡ አምስተኛ መርሐ-ግብር ሲሆን፣ ጨዋታው ሰኔ 13 / 2015 (June 20) ይካሄዳል። አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራትም በቀጣይ ከሁለት ሳምንታት በኃላ ለሚያደርጉት ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ዝግጅት የጀመሩም አሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን […]
#ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 26ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎች!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 26ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ሁለቱ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 15 ጎሎች በ14 ተጫዎቾች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 13 በጨዋታ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ነው። በሳምንቱ 33 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋቾችና አንድ የቡድን አመራር ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ […]
ኢትዮዽያዊያን አትሌቶች በዳይመንድ ሊግ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል!
Rabat Diamond League 2023 From Abdu Muhammed በሞሮኮ ራባት ዳይመንድ ሊግ የ1500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያን እንስት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። በውድድሩን ጉዳፍ ፀጋዬ በ3:54.03  በቀዳሚነት ስታሸንፍ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ብሪኪ ሃይሎም እና ወርቅነሽ መሠለ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
#አልቢትር ባምላክ ተሰማ የአውሮፓን የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተጋብዟል!
ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ሰኔ 4 ቀን የግብፁ ክለብ አል አህሊ እና የሞሮኮው ክለብ ዊዳድ አትሌቲክስ ጋር የሚያደርጉትን የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ እንዲዳኝ መመረጡ ይታወሳል። በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በብቃት በመወጣት የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ ከአፍሪካ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በኃላ ወደ አውሮፓ ተጉዞ በአምሰርዳምር ከተማ […]
#የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በአፍሪካ የመጀመሪያ በሆነው ስልጠና ብቸኛ ተወካይ ሆነው ጨርሰዋል!
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በአዲሱ ኮንቬንሽን መሰረት በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የግብ ጠባቂዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና እና የአካል ብቃት ስልጠና እንዲሚጀመር በወሰነው መሰረት በአልጄሪያ የመጀመሪያውን ስልጣና ላለፉት ሶስት ሳምንታት በተሳካ መልኩ አካሄዶ ዛሬ ፍፃሜ አግኝቷል። በMay 7 ተጀምሮ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረውን የመጀሪያው የግብ ጠባቂዎች ስልጠናን 28 የአልጄሪያ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኞች የተከታሉ ሲሆን ስልጠናውን በካፍ የልማት […]
#የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ዳኛን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው በቀረበ ሪፖርት /ሃምሳ ሺህ/ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 24ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 12 ጎሎች በ10 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 10 በጨዋታ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ነው። በሳምንቱ 26 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች ቀይ ካርድ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሐሙስ ግንቦት 10 […]
” በአካዳሚያችን የሚጫወቱ ታዳጊ ተጨዋቾቻንን ወደ አውሮፓ አገራት ለማጫወት ለእኛ ይሄ ከባድ አይደለም፤ በቅርቡ የምንተገብረው ነው”የ3 Points አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ተገኝተው
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊዎች እግር ኳስ ስልጠና ከሚሰራው የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ (3 Points) ፕሮጀክት ጋር በጋራ ለመስራት በጥር ወር 2014 በይፋ የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸው ይታወሳል። እናም ከወራቶች በፊት የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ ተቋም ይፋዊና ከስምምነቱ በኋላ ቀጥታ ወደ ሥራ ገብቶ ታዳጊዎችን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን – ካፍ የልህቀት ማዕከል በማሰልጠን ከፍተኛ የሆነ ስራን […]
#የዋልያዎቹ ቀጣይ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ !
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ላይ በጊዜያዊነት እንዲመሩ የኢ/እ/ፌ ቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም እና አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን በዋና እና ረዳት አሰልጣኝነት መሾሙ የሚታወስ ሲሆን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሠረት በቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙትን እና ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድኑ ልምድ ያላቸውን አሰልጣኝ ውብሸት ደሳለኝን ሾሟል።
# አሰልጣኝ አስራት ኃይሌን የከተማው አመራሮች በቤቱ ተገኝተው ጠይቀዋል! -የ250ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ እግር ኳስን በታማኝነት ላገለገለው አንጋፋው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው) ለሕክምና ወጪ የሚውል የ250ሺ ብር ድጋፍ አድርገው በመኖርያ ቤቱ ጠይቀውታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባስተላለፉት መልዕክት በሴካፋ ያመጣው ድል በእግር ኳስ ፌድሬሽን በሰጠው አመራርነት በርካታ […]