ከሳምንታት በፊት ከደቡብ አፍሪካው የስዋቶ ከተማ ክለብ ከሆነው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የሙክራ ጊዜ ለማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች አማኑኤል ገ/ሚካኤል የሙከራ ጊዜው ቆይታ ባለመሳካቱ ወደ ሀገሩ መመለሱ ከክለቡ አካባቢ ለኢትዮኪክ የደረሱ መረጃ ያመለክታሉ። የአማኑኤል ገ/ሚካኤልን የመጓዙን መረጃ ቀድመን ካስነበብን በቀናቶች ልዩነት ወደ ደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር […]
ዜናዎች
#አቡበከር ናስር በኔዘርላንድ- አምስተርዳም ይገኛል!-የመጀመሪያ የአውሮፓ ጨዋታውን ነገ ከቤልጂየሙ KAA Gent ክለብ ጋር ያደርጋል !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋቾች አቡበከር ናስር ከክለቡ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር በኔዘርላንድ ይገኛል። የደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮ ሻምፒዮና የሆነው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ በ2023/24 የውድድር ዓመት ከዲኤስቲቪ ፕሪሚየርሺፕ እና ከካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች በተጨማሪ በ Nedbank Cup እና MTN8 ውድድሮች የበላይ ሆኖ ለመቅረብ በሀገር ውስጥ ሲያደርገው የነበረውን የቅድመ ዝግጅት በመጠናከር ከቀናት በፊት […]
#የተጨዋቾች ዝውውር እና ድርድር ገበያው ጦፏል- ለአንድ ተጨዋቾች ከ13 ሚሊዮን ብር ለመክፈል ክለቡ ዝግጁ ነኝ ይላል
በ2016 ዓ.ም ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ የተሻለ ሆነው ለመቅረብ የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች የዝውውር ሂዱቱ በይፋ ማጧጧፍ እና በተጨዋቾች ደላሎች በኩል የማግባባት ስራዎች ቀጥለዋል። በተጨዋቾች ዝውውር ሂደት ከስምምነት የደረሱት በይፋም የተሳካለቸው በተለያዩ መረጃ ምንጮ ይፋ እንደሆኑ ሁሉ ስማቸው እየተነሱ ከሚገኙ በርካታ ተጨዋቾች ጥቂቶቹን በቀጣይ ቀናት ለእናንተ እናደርሳለን። በተለይም በተጨዋቾች የድርድር ሂደት ለቀጣይ ዓመት ከፍተኛ ብር በመወጣት ለማስፈረም […]
የፈረሰኞቹ ኮከብ የሞሮኮውን ክለብ ዛሬ በይፋ ተቀላቅሏል!
ቶጓዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች የነበረው እና የ2015 ከፈረሰቹ ጋር አስደናቂ ጊዜን በማሳለፍ በ25 ጎሎች በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ያጠናቀቀው እስማኤል ኦሮ አጎሮ የሞሮኮ ፋር ራባትን ዛሬ በይፋ ተቀላቅል። እንደሚታወሰው እስማኤል ኦሮ አጎሮ በኢትዮጵያ ቆይታው የውጪ ሀገር ዜጋ ሆኖ በፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በአንድ የውድድር አመት ሀያ አምስት ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ተጨዋች መሆን […]
አርባ ምንጭ ከተማ ና ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላልፎባቸዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 29ኛ ሳምንት በአዳማ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 18 ጎሎች ተቆጥረዋል።በሳምንቱ 19 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሁለት ተጫዋቾች ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ሰኔ 26 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች […]
“በዚህ ማሊያ ይህን ክብር በማሳካቴ ደስታዬ ወደር የለውም፥ ለስኬቱ ሁላችንም አንድ መሆናችን ነው”-ቢኒያም በላይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ድንቅ ተጨዋች ቢኒያም በላይ የዘንድሮው የ2015 የውድድር ዓመቱን በስኬት ካሳለፉ ጥቂት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ነው። ቢኒያም ፈረሰኞቹን ከመቀላቀሉ በፊት በታዳጊነት ዕድሜው በአውሮፖ ክለቦች የመጫወት ዕድል አግኝቶ የእግር ኳስ ሕይወትን ተሞክሮ በሚገባ የተጠቀመበት ተጨዋችም ነበር ለማለት ይቻላል። ቢኒያም በላይ-(ቅዱስ ጊዮርጊስ) በጀርመን ቡንደስሊጋ 2 ተሳታፊ በነበረው ዳይናሞ ደረስደን ከሙከራ ጊዜ በኃላ በኃላም ቢኒያም በአልባኒያው ስኬንደርቡ […]
ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያካትተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የአሜሪካ ጉዞ !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐምሌ ወር ወደ አሜሪካ ተጉዞ ሐምሌ 26 ከጉያና ብሔራዊ ቡድን እና ሀምሌ 29 ከአትላንታ ዮናይትድ ክለብ ጋር የሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና የወዳጅነት ጨዋታውን ያዘጋጀው በፊፋ እውቅና ያለው የጨዋታ አገናኝ ሲጂኤ ኒውማን በመወከል አቶ ዳዊት አርጋው ሰፋ ያለ መግለጫን በጋራ ሰጥተዋል ። […]
# የቅዱሱ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ወደ ደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ በቀጣዪቹ ቀናት ያቀናል !
የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች እና የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ጉዳቶችን አስተናግዶ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል በቀጣዮቹ ቀናት ወደ በደቡብ አፍሪካ እንደሚጓዝ ተረጋግጧል። ከወራቶች በፊት ከደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል አሁን ላይ በምን በኩል እንደሆነ ሳይታወቅ ከደቡብ አፍሪካው የሶዌቶ ከተማ ክለብ ከሆነው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የሙክራ ጊዜ ለማድረግ ወደ ደቡብ […]
#የአቡበከር ናስር በብሔራዊ ቡድኑ ያለመካተት ጉዳይ ይፋ ሆኗል!
ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር የደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ (PSL) ሻምፒዮን ከሆነ በኃላ ለዕረፍት አቡበከር በኢትዮጵያ ይገኛል። የዋልያዎቹና የሰንዳውንስ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካ ቆይታው ለወራቶች በጉዳት የነበረ ቢሆንም በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ለቡድኑ ጠቃሚ ተጨዋች መሆኑንም አሳይቷል። ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር […]
#ጌታነህ ከበደን ዳግም ወደ ብሔራዊ ለመመለስ የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የነበረው ጌታነህ ከበደ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሚያሰለጥኑበት ወራቶች ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን ተከትሎ በውቅቱ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ነበር። በጊዜው ተጨዋቹ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በግልጽ አለመግባባቶች እንደነበሩ ከተዘገበ በኃላ በመሃከላቸው ሰላም መውረዱን አሰልጣኙ በተለያዪ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ በመናገር ነገር ግን ጉዳዩ ከተከሰተ በኋላ አሰልጣኝ ውበቱ ለጌታነህ ጥሪ ሲያቀርቡ ራሱን ከብሔራዊ […]