የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ዋና አሰልጣኝ የ48 ዓመቱ ሰርቢያዊ ኒኮላስ ካቫዞቪች የ5ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን ካደረጉ በኃላ ከጤና እና ከግል ጉዳያቸው ጋር በተያያዘ የዕረፍት ጊዚያቸውን በመጠቀም ወደ ሀገራቸው ሰርቢያ እንደሚሄዱ አሳውቀው ተሰናብተዋል። አሰልጣኙ ከቀናት በፊት የክለቡ አመራሮች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ እያደረጉ እንዳልሆነ የሚያሳይ ንግግር ከተናገሩ በኋላ ከአመራሮቹ ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሲታወቅ ንግግራቸውን አስመልክተው […]
ዜናዎች
ኢትዮጵያዊውያን አትሌቶች የኒውዮርክ ማራቶንን አሸነፈዋል !
Hellen Obiri and Letensebet Gidey ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ በአሜሪካ ኒውዮርክ ማራቶን 2:04:56 የቦታውን ሪከርድ በመስበር ሲያሸንፍ በሴቶች ኬኒያዊቷ ኦብሪ አንደኛ ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ሆናለች። @2023 New York marathon. Men’s 1.Tamirat Tola 2:04:58 2.Albert Korir 2:06:57 3.Shura Kitata 2:07:11 Women’s Results 1.Hellen Obiri 2:27:23 2.Letensebet Gidey 2:27:29 3.Sharon Lokedi 2:27:33
ጌታነህ ከበደ ለሁለተኛ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድኑ መጫወት እንደማይፈልግ በይፋ አሳውቆ – ከቡድኑ ተሰናብቷል!
በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በነበረ አለመግባባት ራሱን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አግልሎ የነበረው የፋሲል ከነማው ጌታነህ ከበደ በአዲሱ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ጥሪ ቢደረግለትም ብሔራዊ ቡድኑ ባረፈበት አዳማ በመገኘት ለአዲሱ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቡድኑን መቀላቀል እንደማይፈልግ በይፋ ማሳወቁ ተረጋግጧል።
⭕ዋልያዎቹ ዛሬ ዝግጅት ጀምረዋል – ጌታነህን ጨምሮ በዛሬው ልምምድ አራት ተጨዋቾች አልተገኙም!
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአፍሪካ ምድብ ‘A’ ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴራሊዮን እና ከቡርኪናፋሶ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ አዲሱ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የመረጧቸውን ተጨዋቾች ይዘው ዛሬ በአዳማ ዝግጅት ጀምረዋል። ከሁለት ቀናት በፊት የተመረጡት አዲሱ አሰልጣኝ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማደረጋቸው ሲታወቅ በአዳማ ካኖፒ ሆቴል ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ ከቀረበላቸው 30 ተጨዋቾች መካከል በዛሬው የመጀመሪያ ቀን […]
በዕድሳት ላይ የሚገኘው የድሬዳዋ ስታዲየም ዛሬ ምልከታ ተደርጓል!
ከ9ኛው ሳምንት በኃላ የሊጉን ጨዋታን ያስተናግዳል! የ10ኛውን የአፍሪካ ዋንጫና አገራዊ ያስተናገደው ታሪካዊው የድሬዳዋ ስታዲየም የፊፋን ስታንዳርድ የጠበቀ ኢንተናሽናል ስታደየም ለማድረግ የዕድሳት ስራው በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል። በተለይም ዘመናዊ በሆነ እና የፊፋ ሁሉንም መሥፈርቶችን ባሟላ ደረጃውን በጠበቀ ሳር የማልበሱ ሂደት እየተጠናቀቀ መሆኑን ባላፈው ዘገባችን ባስነበብናቹ መሠረት አሁን ላይ ሳር የማንጠፉ ስራ ወደ መጠናቀቁ ደርሷል። በየትኛውም የአየር ሁኔታ […]
⭕ አዲሱ የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል!
⭕ አዲሱ የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል! 30 ተጫዋቾች ግብ ጠባቂዎች 1)ሰዒድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ) 2)አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን) 3)ቢንያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ) ተከላካዮች 4)ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) 5) ዓለም ብርሃን ይግዛው (ፋሲል ከነማ) 6)ብርሃኑ በቀለ (ሲዳማ ቡና) 7) ያሬድ ባዬ (ባህር ዳር ከተማ) […]
-አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋሊያዎቹ ይፋዊ አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል!
“በ15 ቀን ውስጥ ተአምር መስራት አልችልም” – አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋሊያዎቹ ይፋዊ አሰልጣኝ ሆነው ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል። አሰልጣኙ በአንድ ዓመት ውል 250ሺህ፡የወር፡ደሞዝ የመድንን ክለብም ሳይለቁ ደርቦ የሚሰሩ ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]
-የኢትዮጵያ ቡና ክለብ በአራተኛው ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ አንድ መቶ ሺህ እንዲከፍል ተወስኗል !
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 18 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ 19 ጎሎች በ16 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 27 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ(በሁለተኛ […]
ኢትዮጵያዊው አትሌት ዴሬሳ ገለታ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደ ማራቶን አሸንፏል !
የቤጂንግ ማራቶን እሁድ በቻይና ዋና ከተማ ተካሂዷል። በወንዶች ኢትዮጵያዊው ዴሬሳ ገለታ 2 ሰአት ከ7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ስያታጠናቅቅ በውድድሩ በዴሬሳ በአጨራረስ ተበልጦ ሁለተኛ የወጣው የሀገሩ ልጅ ይሁንልኝ አዳነ ሲሆን የኬኒያ አትሌት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ኬንያዊቷ ሺላ ቼፕኪሩይ በሴቶች በተመሳሳይ መልኩ የሩጫ ሰዓቱን 2 ሰአት ከ21 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ዘግታ አጠናቅቃለች። 2023 BEIJING MARATHON Men […]
⭕ዋልያዎቹ ቀጣይ ሁለት ጨዋታቸውን ሞሮኮ ላይ ያደርጋሉ!
በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአፍሪካ በምድብ አንድ የተመደበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን November 15 ( ህዳር 5 ቀን ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር በሜዳው ማድረግ የሚገባውን ጨዋታ በሞሮኮ ካዛብላንካ ስታዲየም የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። ይህም ብሔራዊ ቡድኑ የፊፋን መስፈርት ሟሟላት የቻለ ስታዲየም ባለመኖሩ እና የባህር የዳር ስታዲየም በወቅታዊው ሁኔታ ማስተናገድ ባለመቻሉ የሜዳ ጨዋታን ብሔራዊ ቡድኑ እንደተለመደው ሞሮኮ ላይ ያደርጋል […]