ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#የተራዘመው የደርቢ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን፣ ሰዓት እና ስታዲየም መረጃ !

ቅዳሜ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረገ ውይይት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7ተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ከተማ – አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል። […]

አፍሪካ ዜናዎች

#አቡበከር ናስር በቋሚነት – ተሰልፎ ቡድኑም ድል ቀንቶታል !

የደቡብ አፍሪካው ማሚሎዲ ሰንዳዉስ የፊት መስመር አጥቂ ኢትዮጵያዊ ው አቡበከር ናስር ምሽቱን ቡድኑ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጋጣሚውን ኬፕታውን ስፐርስ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል። አቡበከር ከወራቶች ጉዳት እና ማገገም በኃላ ባለፉት ቀናቶች ወደ ሜዳ በመመለስ የመጀመሪያ ጨዋታውን በመጨረሻዎቹ ለ 2 ደቂቃዎች ፣ ሁለተኛውን ጨዋታውን ለ26 ደቂቃዎች ተቀይሮ በመግባት መጫወቱ ይታወሳል። በዛሬው […]

English አትሌቲክስ ዜናዎች

⭕#ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ የአመቱ ምርጥ አትሌት በመሆን ታላቅ ክብር ተቀዳጅታለች!#World Athlete of the Year –

  በ2023 የሴቶች ማራቶን ክብረወሰንን 2:11:53 በመግባት የበርሊን ማራቶንን በማሸነፍ አዲስ ክብረወሰን በእጇ ያስገባቸው ኢትዮዽያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በጎዳና ላይ ውድድሮች ባሳየችው ድንቅ ብቃት ምሽቱን የአለም አትሌቲክስ የአመቱ ምርጥ አትሌት በማለት ታላቁን ክብር ለትግስት አልብሷታል ። በወንዶች በተመሳሳይ የማራቶን ክብረወሰንን በእጁ ያስገባው ኬኒያዊዉ ኬልቨን ኪፕቱ ይህንኑ ክብር አሸንፏል:: World Athlete of the Year – Women’s […]

አፍሪካ ዜናዎች

አቡበከር ናስር – በዛሬው ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት ወደ ሜዳ ተመልሷል !

በጉዳት ከሜዳ ርቆ የነበረው ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አጥቂ አቡበከር ናስር ከበርካታ ወራቶች ጉዳት በኃላ በማገገም ላይ የነበረ ሲሆን የዋሊያዎቹ አጥቂ አቡበከር ናስር ክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዛሬ ከግብፁ ፒራሚድ ጋር በሜዳው ባደረገው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት ለ26 ደቂቃዎች ተጫውቷል። ከወራቶች ጉዳት እና ማገገም በኃላ አቡበከር የመጫወት አቅሙን አሳይቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 0 ለ […]

English አትሌቲክስ ዜናዎች

#Fair Play Award #ለተሰንበት ግደይ የአመቱ የስፖርታዊ ጨዋነት አሸንፋለች!

Letesenbet Gidey #Fair Play Award አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሽልማቱን ያገኘችው በቡዳፔስቱ የአለም ሻምፒዮና በ10ሺህ ሜትር ውድድር በመጨረሻው ቅፅበት አትሌት ሲፋን ሃሰን ስትወድቅ ለመርዳት መሞከሯን ተከትሎ Fair Play Award መልካም ተግባር ተሸላሚ ሆናለች። ’s world 10,000m silver medallist Letesenbet Gidey has been named winner of the International Fair Play Award #AthleticsAwards

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

⭕ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮዽያ ቡና እና አዳማ ክለቦች የዲሲፕሊን ቅጣት ተላለፈባቸው!

  👇 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ህዳር 24 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ ሁለቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 16 ጎሎች በ15 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 34 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾች ሲሰጥ አራት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል […]

ዜናዎች

የአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያውን ለማጠር – የማስነሳቱ ሂደት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል!

– የመኪና አከራዮች ተነስተዋል! በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የሚሰሩ የመኪና አከራዮች የተለያዩ ሱቆች በ15 ቀናት እንዲለቁ እና ዙሪያውም ሊታጠር መሆኑን ከቀናት በፊት ባስነበብናቹ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። በአዲስ አዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ በተለምዶ ትንሿ ስታዲየም መኪና አለማማጆች ዛሬ መነሳታቸው እና ባህልና ስፖርት ለኢትዮጵያ እግርኳስና ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ተዕዛዞች በቀጣይም ተግባራዊ መሆናቸውን የሚቀጥሉ መሆኑ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

.ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በቫሌንሽያ ማራቶን ታላቅ ድልን ተቀዳጅተዋል!

  በወንዶች አትሌት ሲሳይ የቦታውን ክብረወሰን ሰብሯል! ከወሊድ መልስ አትሌት ወርቅነሽ ዳግም ወርቁን አጥልቃለች ! በ2023 የአለም የማራቶን ውድድር አንዱ የሆነው የቫሌንሺያ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት ተጠናቋል። ኢትዮጵያዊው ሲሳይ ለማ በወንዶች ገና ከጅምሩ ጠንከር ያለ ፍጥነት በመሮጥ ከሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዳዊት ወልዴ እና ኬኒያዊው ኪቢወት ካንዲ ጋር መሪነቱን ቢቀላቀልም ከ35ኛው ኪሎ ሜትር በመምጣት ውድድሩን በ 2፡01 48.በሆነ […]

ዜናዎች

በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ -ሱቆችና የመኪና አከራዮች በ15 ቀናት ውስጥ ሊነሱ ሲሆን- ዙሪያውም ሊታጠር ነው !

  🕳 የስታዲየሙ ዕድሳት አራት ዓመታት ሊያስቆጥር ተቃርቧል! 👇 በቀድሞ መጠሪያዉ ቀኃሥ ስታድየም በአሁኑ ስያሜዉ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ ለማጠናቀቅ ቀሪ ሥራዎች ከሦስት ወራት በላይ እንደማይፈጅ በባሕል እና ስፖርት ሚንስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ከዶይቸ ቬለ (DW) ጋር ከቀናት በፊት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሲናገያያለ በአንፃሩ የአዲስ አበባ ስታዲየም […]

ቀጥታ ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጥታ ስርጭት ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል !

የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስት ሳምንታት ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዶ በብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል። ከ6ተኛው ሳምንት ጀምሮ ያሉ የሊጉ ጨዋታዎች ከነገ ህዳር 20/2016 ጀምሮ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መካሄዱ የሚቀጥል ሲሆን የሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭተም ይጀምራል። በስምምነቱ መሰረት በ2016 ዓ.ም በቀጥታ ስርጭት ከሚተላለፉ አንድ መቶ ሰማንያ(180) ጨዋታዎች […]