የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በፕሪሚየር ሊጉ ወድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የዘጠኝ ጨዋታ ዕግድ ተላልፎባቸዋል። አሰልጣኙ ዕግዱ ሊተላለፍባቸው የቻለው ድሬደዋ ከ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በነበረው ጨዋታ ላይ የ25ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በ44ኛ ደቂቃ ላይ የዕለቱ ዳኛ ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ አፀያፊ ስድብ ሰድቦኛል በሚል በቀይ ካርድ ከሜዳ በመሰናበታቸዉ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ የዉድድር እና ስነ […]
ዜናዎች
የኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2 ውጤት
የኢትዮጵያ ዋንጫ – የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ውጤት ሲዳማ ቡና 0-0 መቻል – ሲዳማ ቡና በመለያ ምቶች 7-6 በማሸነፍ ለፍፃሜ ማለፍ ችሏል። – የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና መካከል ግንቦት 30/2017 ይከናወናል። ——— ሸገር ከተማ 0-2 ወላይታ ድቻ 39′ ዘላለም አባተ 51′ ብዙዓየሁ ሠይፈ – ወላይታ ድቻ ለተከታታይ ዓመት የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን […]
በሴቶች የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች!
በ45ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡ አትሌት ትግስት ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሠከንድ ፈጅቶባታል፡፡ በዚሁ ውድድር መርሐ-ግብር ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ የለንደን ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው ከዓለም ትላልቅ ማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ነው፡
ከንአን ማርከነህ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል ቀዷል!
በሊቢያ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው አል መዲና ትሪፖሊ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጫዋች ከንአን ማርከነህ ከክለቡ ጋር ያለውን ውሉን መቅደዱና መለያየቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢትዮ ኪክ መረጃውን ጠቁመዋል ። የከንአን ማርከነህ ክለብ አል መዲ ቱንዚያዊውን አሰልጣኝ አሰናብቶ አዲስ ግብፃዊ አሰልጣኝ መቅጠሩ ተከትሎ አዲሱ አሰልጣኝ ሦስት አፍሪካውያን ተጨዋቾች ወደ ክለቡ ማስፈረማቸው ሲሰማ አዲሱ […]
ሉሲዎቹ በየካቲት ወር አራት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ያከናውናሉ !
በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ ከዩጋንዳ ጋር የካቲት 14 እና የካቲት 19 የሚያከናውን ሲሆን ለማጣርያ ጨዋታዎቹ ዝግጅት እንዲረዳ ከጅቡቲ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በመጪው የካቲት 5 እና የካቲት 9 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ። የሴቶች ብሔራዊ ቡድናችን ለተጫዋቾች […]
“አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም። ለሁለት ሳምንታት አላየሁትም የልምምድ ቦታ ላይ መገኘት አቁሟል”አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት
ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካውን ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ከወራቶችበፊት መቀላቀሉን ይታወሳል። ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አቡበከር ናስርን ለአንድ የውድድር አመት ካስፈረመ ከወራቶች ቆይታ በኃላ የሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም በማለት በይፋ ተናግረዋል:: አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ አርብ ዕለት በፖሎክዋን ሲቲ ከተሸነፈ በኋላ ለ […]
ጋቶች ፓኖም ለኢራቅ ስታር የኒውሮዝ ስፖርት ክለብ ፈረመ
ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ከትላንት በስቲያ ወደ ኢራቅ ማቅናቱን መዘገባችን ይታወሳል:: የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና፣ ወላይታ ድቻ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መቐለ 70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እንዲሁም በራሽያ እና ግብፅ ሊግ የተጫወተው እና በዘንድሮ ዓመት በኢትዮጵያ መድን መለያ ያየነው አመለ ሸጋው ጋቶች ፓኖም የኢራቅ ስታር ሊግ የኒውሮዝ ስፖርት ክለብ የ2024-2025 በአንድ አመት ውል ፈርሟል:: ኒውሮዝ ስፖርት ክለብ […]
ጎፈሬ እና ኖቫ ኮኔክሽንስ ውላቸውን አራዘሙ !
የስፖርት ትጥቅ ብራንድ ጎፈሬ ከሀገር አልፎ በመላው ዓለም ምርቶቹን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል። ጎፈሬ በአጋርነት ከሀገር ውጪ አብሯቸው ከሚሰራቸው ታላላቅ ተቋማት መካከል በሀገረ አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፈው ግራንድ አፍሪካ ረን እንዲሁም ለሀገራቸው ታላላቅ ገድሎችን ለፈፀሙ የሀገር ባለውለታዎች እውቅና የሚሰጠው ኢምፓክት አዋርድ ዝግጅቶችን ከሚያዘጋጀው ኖቫ ኮኔክሽንስ ጋር ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት የሰራ ሲሆን አሁንም ከተቋሙ […]
ከግብፁ ክለብ ጋር የተለያየው ሄኖክ የግብፁ ክለብ ላይ ለፊፋ ክስ መስርቷል! ⭕️ሄኖክ በደቡብ አፍሪካው Cape Town Spurs እና በኢራቁ Al karkh ክለቦች ጋር አዲስ መረጃ
የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ ለግብፅ ክለብ ሃራስ ኤል ሁዶድ ከሦስት ወራቶች በፊት የሁለት ዓመት ፊርማውን በማኖር ለስድስት አመታት ከቆየበት የፈረሰኞቹ ቤት ወደ ግብጹ ክለብ ቢያቀናም ነገሮች እንደታሰቡት ሳይሆን ሄኖክ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ኢትዮጵያ መገኘቱን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል:: ኢትዮኪክ ለእናንተ ለአንባቢያን በገባንላችሁ ቃል መሠረት ሄኖክን ከክለቡ መለያቱን ተከትሎ መረጃውን የበለጠ ለማጣራት እንደምንጥር በገባነው ቃል መሠረት […]
– ስሑል ሽረ እና ቦዲቲ ከተማ ወደ ሦስተኛ ዙር የተሸጋገሩ 10ኛ እና 11ኛ ቡድኖች ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ የዛሬ ከሰአት ጨዋታ ውጤቶች :- 2ኛ ዙር 10ኛ እና 11ኛ ጨዋታ ውጤቶች ኢትዮጵያ ቡና 1-2 ስሑል ሽረ 79′ ኩንኩን ሃፊዝ 45+2′ ብሩክ ሐዱሽ 74′ ሄኖክ ተወልደ አዳማ ከተማ 1-1 ቦዲቲ ከተማ 9′ አብዱልፈታ ሰፋ / 89′ ደሳለኝ ሀሜ በመለያ ምቶች ቦዲቲ ከተማ 4-2 አሸንፏል። – ስሑል ሽረ እና ቦዲቲ ከተማ ወደ ሦስተኛ ዙር […]