ከ20 ዓመት በታች የኢትዮዽያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በድምር ውጤት 5 ለ 2 ኢኳቶርያል ጊኒን አሸንፏል። – ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የማሊ እና አልጄርያ አሸናፊን ትገጥማለች። የዛሬ ጨዋታ ውጤት ኢትዮጵያ 4-1 ኢኳቶርያል ጊኒ (32′ 41 ንግስት በቀለ 60′ መሳይ ተመስገን)89′ እሙሽ ዳንኤል ) [-ድምር ውጤት፡ 5-2]
አፍሪካ
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከ Nike ወደ ቻይናው ታላቅ ኩባንያ አንታ ስፖንሰሩ ዞሯል!
ኩባንያው የረጅም ርቀት ሯጮች ማሰልጠኛ በአፍሪካ እንደሚገነባ ይፋም አድርጓል! በ5000 ሜትር እና በ10,000 ሜትሮች ውድድሮች የአለም ክብረ ወሰን እና የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ባለቤትና የረጅም ርቀት ሯጩ አሁን ላይ ከዓለማችን ሦስት ፈጣን የማራቶን ሰዓት ካላቸው አንዱ የሆነው ኡትዮዽያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከስፖንሰሩ ከNike ኩባንያ ጋር ያለውን ውል ተቋጭቶ ከቻይናው ኩባኒያ አንታ ጋር መስማማቱን ተሰምቷል። እ.ኤ.አ […]
ትውልደ ኢትዮጵያዊው “The Game Changer”ማረን ኃይለሥላሴ ቺካጎ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል!
ትላንት ምሽት የሊዮን ሜስን ክለብ ላይ ድንቅ ጎሎችን በማስቆጠር ብቃቱን አሳይቷል! የአሜሪካው MLS ሊግ የዓመቱ ውድድር እየተገባደደ ይገኛል። በዛው ልክ የሊጉ ፍልሚያው “ፕለይ ኦፍ” ውስጥ ከዘጠኙ ቡድኖች አንዱ ለመሆን የሚደረገው ትግልም ቀጥሏል። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድንቅ ተጨዋች ማረን ኃይለሥላሴ የሚገኝበት ቺካጎ 12ተኛ ደረጃን ይዞ ትላንት ምሽት ከሊዮ ሜሲ ቡድን ኢንተር ሚያሚን ጋር ታላቅ ፍልሚያ አድርገው ነበር። […]
#የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከዋልያዎቹ ጋር በካይሮ የሚደርጉት ጨዋታ የክብር ጨዋታ ነው ሲሉ የግብፅ ሜዲያዎች እየዘገቡ ነው !
የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨምታውን ማለፉን ያረጋገጠውና ከኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በበርካታ ደጋፊዎቹ ፊት የሚግጠመው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ከዋልያዎቹ ጋር ነገ የሚያደረገው ጨዋታ በመጀመሪያው የማጣሪያው ጨዋታ ኢትዮጵያ ላይ ያጋጠመውን 2 ለ 0 ሽንፈት ለማካካስ የሚደረግ ታላቅ ጨዋታ እንደሆነ አል-መስሪ አል-ዩም የተባለ በድህረ ገፅ ዘግቧል። የግብፅ ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያውን የምድቡ ቀዳሚ ሆኖ በ12 ነጥብ […]
የፈረሰኞቹ ኮከብ የሞሮኮውን ክለብ ዛሬ በይፋ ተቀላቅሏል!
ቶጓዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች የነበረው እና የ2015 ከፈረሰቹ ጋር አስደናቂ ጊዜን በማሳለፍ በ25 ጎሎች በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ያጠናቀቀው እስማኤል ኦሮ አጎሮ የሞሮኮ ፋር ራባትን ዛሬ በይፋ ተቀላቅል። እንደሚታወሰው እስማኤል ኦሮ አጎሮ በኢትዮጵያ ቆይታው የውጪ ሀገር ዜጋ ሆኖ በፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በአንድ የውድድር አመት ሀያ አምስት ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ተጨዋች መሆን […]
ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚያካትተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የአሜሪካ ጉዞ !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐምሌ ወር ወደ አሜሪካ ተጉዞ ሐምሌ 26 ከጉያና ብሔራዊ ቡድን እና ሀምሌ 29 ከአትላንታ ዮናይትድ ክለብ ጋር የሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና የወዳጅነት ጨዋታውን ያዘጋጀው በፊፋ እውቅና ያለው የጨዋታ አገናኝ ሲጂኤ ኒውማን በመወከል አቶ ዳዊት አርጋው ሰፋ ያለ መግለጫን በጋራ ሰጥተዋል ። […]
# የቅዱሱ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ወደ ደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ በቀጣዪቹ ቀናት ያቀናል !
የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች እና የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ጉዳቶችን አስተናግዶ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል በቀጣዮቹ ቀናት ወደ በደቡብ አፍሪካ እንደሚጓዝ ተረጋግጧል። ከወራቶች በፊት ከደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል አሁን ላይ በምን በኩል እንደሆነ ሳይታወቅ ከደቡብ አፍሪካው የሶዌቶ ከተማ ክለብ ከሆነው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የሙክራ ጊዜ ለማድረግ ወደ ደቡብ […]
#የአቡበከር ናስር በብሔራዊ ቡድኑ ያለመካተት ጉዳይ ይፋ ሆኗል!
ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር የደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ (PSL) ሻምፒዮን ከሆነ በኃላ ለዕረፍት አቡበከር በኢትዮጵያ ይገኛል። የዋልያዎቹና የሰንዳውንስ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካ ቆይታው ለወራቶች በጉዳት የነበረ ቢሆንም በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ለቡድኑ ጠቃሚ ተጨዋች መሆኑንም አሳይቷል። ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር […]
#በዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ቤትኪንግ ሊግ ይቋረጣል !
በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ከማላዊ ጋር የሚያደርጉት የጨዋታ እየተቃረበ ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የምድቡ አምስተኛ መርሐ-ግብር ሲሆን፣ ጨዋታው ሰኔ 13 / 2015 (June 20) ይካሄዳል። አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራትም በቀጣይ ከሁለት ሳምንታት በኃላ ለሚያደርጉት ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ዝግጅት የጀመሩም አሉ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን […]
#አልቢትር ባምላክ ተሰማ የአውሮፓን የፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተጋብዟል!
ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ሰኔ 4 ቀን የግብፁ ክለብ አል አህሊ እና የሞሮኮው ክለብ ዊዳድ አትሌቲክስ ጋር የሚያደርጉትን የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ እንዲዳኝ መመረጡ ይታወሳል። በአፍሪካ ዋንጫ ወሳኝ ጨዋታዎችን እና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በብቃት በመወጣት የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ ከአፍሪካ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ የመልስ ጨዋታ በኃላ ወደ አውሮፓ ተጉዞ በአምሰርዳምር ከተማ […]