የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት በጠንካራ ተፎካካሪነት በስምንተኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ በቀጣይ አመት የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ እና የክለቡን የፋይናንስ አቅሙን የበለጠ ለማጠናከር ለወዳጅነት ጨዋታ እና ለገቢ ማሰባሰቢያ ወደ ፕሪቶሪያ የፊታችን ሀሙስ ያመራል። ነብሮቹ የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም በማምራት በደቡብ አፍሪካ ናሽናል ዲቪዢን ላይ ተሳታፊ ከሆነው ጂ ዲ አር ስታር ከተባለው […]
አፍሪካ
ዋልያዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል!
በ2025 በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ጁሀንስበርግ በተደረገ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይፋ ተደርጓል። በዚህ መሠረት ዋልያዎቹ ከታንዛኒያ፣ ጊኒ እና ዲ.ሪ ኮንጎ ጋር ተደልድሏል።
በ23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አግኝታለች !
በካሜሩን ዱዋላ ዛሬ በተጀመረው 23ኛ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በውድድሩ አትሌት ፋንታዬ በላይነህ እና አትሌት ውብርስት አስቻለ ተከታትለው በመግባት ለሀገራቸው የወርቅና የብር ሜዳሊያ አምጥተዋል።
Full time # ⭕️FIFA 2026 FIFA World Cup Qualifiers # ተጠናቋል
በርካታ የጎል ማግባት እድሎችን ያልተጠቀመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጅቡቲ ጋር አንድ ለአንድ ተለያይተዋል! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል። ዋልያዎቹ በምድብ A የማጣሪያ ጨዋታዎች በሶስት ነጥቦች አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ጅቡቲ 1-1 ኢትዮጵያ ጋብርኤል ዳድዚ (28′) / ምንይሉ ወንድሙ (30 FIFA 2026 […]
𝗠𝗮𝘁𝗰𝗵 𝗗𝗮𝘆! # የጨዋታ ቀን!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ጊኒ ቢሳውን በቢሳው ሴፕቴምበር 24 ስታዲየም ምሽት 1:00 ላይ ይገጥማል. በጨዋታው ኢትዮጵያ ሙሉ ቢጫ መለያ የምትጠቀም ሲሆን ተጋጣሚያችን ጊኒ ቢሳው ሙሉ ቀይ የሚጠቀሙ ይሆናል። ጨዋታውን ከቤኒን የተመደቡት ጂንዶ ልዊስ (ዋና)፣ አይማር ኤሪክ (ረዳት)፣ ጆ ኮርቴል (ረዳት)፣ ሙሐመድ ኢሳ (4ኛ) ሲመሩት ጃሜ ባካሪ […]
የጊኒ ቢሳው አሰልጣኝ ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ማምሻውን ተጫዋች ከስፔን ጨምረዋል!
ኢትዮጵያን በሜዳዋ የምታስተናግደው ጊኒ ቢሳው ከኢትዮጵያ እና ከግብፅ ጋር ለምታደርገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ቦአ ሞርቴ በብሔራዊ ቡድን ላይ ማምሻውን ለውጦችን አድርጓል። ለብሔራዊ ቡድኑ ዝርዝር ላይ የነበሩት ማውሮ ቴይሼራ እና ጃርዴል በጉዳት ምክንያት : ካርሎስ ማኔ እና ዳልሲዮ በግል ምክንያቶች ተሰናብተዋል። አሰልጣኝ ሉዊስ ሞርቴ በወጡት ተጫዋቾች ምትክ በስፔን La Liga 2, የሚጫወተው የ20 […]
🛑ዋልያዎቹ በሰላም ቢሳው ደርሰዋል! Safely arrived!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ቢሳው ጋር በመጪው ሀሙስ ለሚያደርገው ጨዋታ ዛሬ ማለዳ ወደ ስፍራው የተጓዘ ሲሆን ምሽት ላይ ቢሳው ከተማ ገብቷል። The Ethiopian national team traveled to the this morning for the World Cup qualifier against Guinea-Bissau on Thursday and safely arrived this evening in Bissau
የብሔራዊ ቡድኑ የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል!
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም ወደ መጨረሻው የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል። በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታቸውን ከኬንያ ጋር በናይሮቢ ኡሊንዚ ስፖርትስ ኮምፕሌክስ ያደረገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኬንያ 3-0 ተሸንፎ የማጣርያ ዙር ሳያልፍ ቀርቷል።
ኢትዮጵያዊቷ የላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ሆና መቀጠሯ የላይቤሪያ አሰልጣኞችን “ለማንቋሸሽ” እንዳልሆነ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል!
👇 የካፍ ኢንስትራክተር አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ታዳጊ እና ዋና ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፣ የቅ/ጊዮርጊስ የሴቶች ቡድን እና የወንዶች ተስፋ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም አሁን የላይቤሪያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዋና አሰልጣኝ መሆኗ ይታወሳል። የላይቤሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ራጂ የካፍ ኢንስትራክተር አሰልጣኝ ሠላም ዘርዓይ ሰላም የዋናው የሴት ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ […]
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ጀምሯል!
አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ለ26 ተጫዋቾች በትናንትናው ዕለት ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቾቹም በዛሬው ዕለት በመሰባሰብ ከቀትር በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ማከናወን ችለዋል። ኢትዮጵያ እና ሌሶቶ ሁለት ጨዋታዎችን የሚያከናወኑ ሲሆን ጨዋታዎቹም መጋቢት 12 እና መጋቢት 15/2016 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል። @EFF