Kenenisa Bekele
አትሌቲክስ ዜናዎች

” ቀነኒሳ በቀለ በኦሎፒክ ይሳተፋል ፣ ምንም ሳይረበሽ ልምምዱን ጠንክሮ ይሰራ”- ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቶኪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ኢትዮዽያን የሚወክሉ አትሌቶችን  ለመምረጥ ከቀናት በፊት በሰበታ የ35 ኪ.ሜ ውድድር አዘጋጅቶ በሁለቱም ፆታ መምረጡ ይታወሳል።በአንፃሩ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያለው የአለም ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በውድድሩ ባለመሳተፉ በኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግልጽ ባልሆነ የውድድር መሥፈርት ከቶኪዮ ኦሎምፒክ የተገለለ መሥሎ የነበረ ቢመስልም ዛሬ ቀነኒሳ በቀለ በቶኪዮ ኦሎምፒክ እንደሚሳተፉ ታውቋል። የአኖካ አዲሱ ፕሬደዛንት […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

አትሌት ቀነኒሳ ያልተገኘበት ለቶኪዮ የማራቶን ምርጫ ውድድር ተካሄደ !

ለቶኪዮ 2020 በማራቶን ሀገራችንን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የማጣሪያ ውድድር ዛሬ ማለዳ በሰበታ ጎዳናዎች ተካሄዶ በሴቶትች አትሌት ትዕግስት ግርማ በወንዶች አትሌት ሹራ ቂጣታ ቀዳሚ ሆነው አሸንፈዋል። ውጤቶቹ :- በሴቶች 1ኛ ትዕግስት ግርማ 1:59:23 2ኛ ብርሀኔ ዲባባ 1:59:45 3ኛ ሮዛ ደረጄ 2:00:16 4ኛ ዘይነባ ይመር 2:03:41 5ኛ ሩቲ አጋ 2:04:28 በወንዶች 1ኛ ሹራ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሌጎስ ማራቶን በማሸንፍ ከፍተኛውን ሽልማት አግኝተዋል !

በምዕረብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ለስድስተኛ ዛሬ ረፋድ በተካሄደው እና DSTVን  ጨምሮ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አግኝቶ በነበረው ” Access Bank Lagos City Marathon 2021 ” የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን  ከፍተኛውን ሽልማት በማግኘት ውድድሩን አጠናቀዋል። በሴቶች የ 42 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮዽያዊቷ መሰረት ዲንቃ በ2:28.53 አሸናፊ በመሆን 30,000 ዶላር ተሸላሚ ስትሆን ኬኒያዊቷ ችሊስታይን ጄፕቺር በሁለተኝነት 20,000 ዶላር እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

የ50ኛው ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል ! – ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦለታል !

የ50ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓልን በማስመልከት የዘንድሮው ሻምፒዮናው ለየት ባለ መልኩ ዛሬ ይጀመራል። ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስጠሩ በርካታ አትሎቶች የሚታዮበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዘንድሮው በተለየ ዝግጅት  ደምቆ ዛሬ ይካሄዳል ተብሏል ። የዘንድሮው ሻምፒዮና  የአገሪቱ አብዛኞቹ ክለቦች ፣ ክልሎች እና ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን  በኮሮና ምክንያት ያለ ተመልካች የሚካሄድም እንደሆነም ተጠቁሟል ። ዘንድሮ  ለ50ኛ […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

ኑሯዋን በስዊዘርላንድ ያደረገቸው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሸነፈች !

በስዊዘርላንድ ኑሯዋን ያደረገቸው እና በረጅም እና መካከለኛ ርቀቶች የግል ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በተደጋገሚ የምታሳተፈው አትሌት ሄለን በቀለ ትላንት በጄኔቭ የሲውዝ ኦሎፒክ ኮሚቴ ባዘጋጀው የማራቶን ውድድር ላይ አሸናፊ ሆናለች። አትሌቷ የትላንቱን የማራቶን ውድድር በ2 :24.57 በመግባት ማሸነፍ ችላለች። አትሌት ሄለን በቀለ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም  ከ ኢትዮጵያ ወደ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ከገባች በኋላ ኑሯዋን  ከባለቤቷ  አትሌት […]

Athlete Derartu Tulu
አትሌቲክስ

ለክብርት ጀግና ለኮ/ር ደራርቱ ቱሉ ዕውቅ እና ሽልማት ተበርክቷል !

በዛሬው የስካይ ላይት ሆቴል ለኮ/ር ደራርቱ ቱሉ በተደረገላት የእውቅና፣ ሽልማት እንዲሁም የአክብሮቶች ልዩ ፕሮግራም ላይ የሚከተሉት ሽልማቶች ተበርክቷል! ፌደራል ማረሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1ኛ ደረጃ የተሰጠ የክብር ኒሻን ሽልማት ተበርክቶላታል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአያት የሚገኘውን ትልቁን አደባባይ በስሟ ተሰይሟል የሁለት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ከከተማ አስተዳደሩ ተበርክቶላታል ኦሮሚያ ክልል አምስት ሚሊየን እና ሱሉልታ የስፓርት አካዳሚ […]

Derartu Tulu
አትሌቲክስ ዜናዎች

ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ዛሬ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ! – ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና መርሀ ግብር ዛሬ መጋቢት 19/2013 ከቀኑ 10 : 00 ሰዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብሩን ምክንያት አስመልክቶ ከቀናት በፊት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተጠቆመው ጀግናዋ አትሌት በስፖርቱ አለም ላበረከተችው በርካታ ተግባራት አስተዋፅ እና እውቅና በመስጠት መጪውን ትውልድ ማነቃቃት መሆኑን የኮሚቴው አባል የሆኑት አትሌት ገዛህኝ አበራ […]

አትሌቲክስ

ኢትዮጵያን በቶኪዮ ፓራሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች ተረጋገጡ!

አምስት አባላት ያካተተው የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን በቱንዚያ አገር አስተናጋጅነት እ ኤ አ ከማርች 14-21/2021 እየተካሄደ በሚገኘው የ2021 የቶክዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ የሚኒማ ማሟያ ( ማጣሪያ ) የውድድር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል ። ከብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አንዱ የሆነው አትሌት ታምሩ ከፍያለው በ1500 ሜትር 03:56 በሆነ ሰዓት ውድድሩን ጨርሶ በመግባት ለቶኪዮ ፓራሊምፒክ ጨዋታ ኢትዮጵያን የሚወክል መሆኑ ታውቃል ። […]

አትሌቲክስ

የቶኪዮ ኦሎፒክ ዝግጅት እክል ገጥሞታል!

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውጥረት ተካርሮ መቀጠሉን መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል። የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ዛሬ በኔክሰስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ያረጋገጠም ሆኗል።በተለየም ፍጥጫው በፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት እና በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የኦሎምፒክ ኮሜቴ ፕሬዝዳንት መካከል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንደሚታወሰው የኦሎምፒክ ውድድሮች በመጡ ቁጥር ተመሳሳይ ውጥረቶች ከዚህ […]

አትሌቲክስ

የአትሌት ለምለም ኃይሉ ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ፀደቀ !

በፈረንሳይ ሌቪን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የቤትውሰጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አትሌት ለምለም ያስመዘገበችው የ 4 01.57 ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ ከ 20 ዓመት በታች የቤት ውስጥ የ 1500 ሜትር የዓለም ሪኮርድ ሆኖ ማፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ በድህረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።