በእሁዱ የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ሆን ብለው ውጤት ለቅቀዋል በሚል የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን አወዛጋቢ አጨራረስን በተመለከተ በኢትዮጵዮኑ አትሌቶች ላይ ምርመራ መጀመሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ በውድድሩ ላይ ኬኒያዊያኑ ሮበርት ኬተር እና ዊሊ ምናንጋት እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ኃይሉ ወደ መጨረሻው መስመር ሲደርሱ ፍጥነታቸውን መቀነሳቸውን እንዲሁም ቻይናዊው አትሌት ቀድሞ እንዲገባ ሲጠቁሙ የሚያሳየውን ምስል ተመልከቱ…
Author: Ethokick
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንት ድሬዳዋ ስታዲዮምን ጎበኙ !
በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ የገቡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የማስፋፊያ ግንባታ እና መጫወቻ ሜዳውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፊራንኦል ቡልቻ የፌዴሬሽኑ ኘሬዝዳንት የተቀብሏቸው ሲሆን የስታዲየሙ ያለበትን ደረጃ ገለፃ አድርገውላቸዋል። በጎብኝታቸው የስታዲየሙን የተጫዋቾች መቀየሪያ የተገጠመውን እጅግ ዘመናዊ መቀመጫ ወንበሮቹ ተመልክተዋል። በዚህ የመስክ ምልከታ ላይ ኮሚሽነር […]
በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመው ጨዋታ ሰኞ እንደሚካሄድ የሊጉ ኮሚቴ አሳውቋል
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባህር ዳር ከተማን ከወልቂጤ ከተማ የሚያገናኘው የጨዋታ መርሃ ግብር – የ2015 የሊጉ ኮከብ ተጫዋቾች እጩ፣ የኢትዬጵያ ቡሔራዊ ቡድን እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ይታወቃል። ይህ የተራዘመው መርሃ ግብርም ሰኞ ሚያዝያ 14/2015 በ12:00 ሰዓት በድሬደዋ ስታዲየም እንደሚካሄድ […]
ኢትዮጵያ የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በሁለተኝነት አጠናቀቀች!
በቤለግሬድ 2024 የ45ኛውን የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ ኪሎ ሜትር ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣6 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡ በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን […]
#ቤልግሬድ2024- የዓለም ሻምፒዮናን ኢትዮጵያን አትሌቶች በድል ጀምረዋል!
Ethiopia dominates the women’s U20 race በሰርቢያ ቤልግሬድ ዛሬ በሚካሄድ ላይ ባለው ተጠባቂው የ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲከስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በድል ጀምረዋል። በሴቶች 6km ከ20 አመት በታች ውድድር ኢትዮጵያዊቷን ማርታ አለማዮሁ፣ አሳየች አይጨው እና ሮቢ ዲዳ – ከ1 – 3ኛ ደረጃ በመውጣት አሸንፈዋል። Ethiopia dominates the women’s U20 race 1 – 3 Marta Alemayehu- […]
የፋሲሉ አማኑኤል በትላንቱ ግጭት ላልተወሰነ ጊዜ ከእግርኩዋስ እንደሚርቅ አሰልጣኙ ተናግረዋል!
ትላንት የ19ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ የፋሲሉ ከነማው የአጥቂ መስመር ተጨዋች አማኑኤል ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል። የክለቡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስለ አማኑኤል ገብረሚካኤል የትላንት ምሽቱን ጉዳት አስመልክተው በማህበራዊ ገፃቸው ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ። ” ጥቃቅን የሚመስሉ ጉዳቶች የጭካኔ ታክሎች ብዙዎችን ከህልማቸው አሰናክለዋል:: ለዚህ ከባድ ጥፋት ክእግዜር ቀጥሎ […]
እሁድ በዓለም ሻምፒዮና የሚጠበቀው አትሌት በሪሁን አረጋዊ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ አድርጓል!
የፊታችን ቅዳሜ ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ በሚካሄደው ተጠባቂው የ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲከስ ሻምፒዮና ከሚካፈሉ እና በውጤት ከሚጠበቁ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አንዱ በሪሁን አረጋዊ ወደ ሰርቢያ ከማቅናቱ በፊት ለወገኖቹ ዕርዳታ አድርጓል። አትሌት በርሁን ዕርዳታውን ለ400 ሰወች ከ60 በላይ ኩንታል እህል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንዲደርስ አድርጓል።
የጨዋታ ማራዘም መረጃ!
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባህር ዳር ከተማን ከወልቂጤ ከተማ ያገናኛል። ነገር ግን የ2015 የሊጉ እጩ ኮከብ ተጫዋች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰን ጊዜ መራዘሙን እየገለፅን በቀጣይ የሚወሰነውን የመጫወቻ መርሃ ግብር የምንገልፅ ይሆናል። የኢትዮጵያ […]
የአለልኝ አዘነን 23 ቁጥር ማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ ክለቡ ወሰነ !
በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ አስታወቀ። የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ ስፍራው በመገኘት ገልፀዋል። በዚህም አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰው የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብሰው ሆኖ በክብር […]
አዲሱ ሙሽራ አለልኝ አዘነ ከዚህ አለም በድንገት ማለፉ – ጥልቅ ሀዘን !
ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ በአርባ ምንጭ ይፈፀማል! በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን፤ በቁርባን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ። ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት […]