ዜናዎች

የፋሲሉ አማኑኤል በትላንቱ ግጭት ላልተወሰነ ጊዜ ከእግርኩዋስ እንደሚርቅ አሰልጣኙ ተናግረዋል!

ትላንት የ19ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ቡና ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ የፋሲሉ ከነማው የአጥቂ መስመር ተጨዋች አማኑኤል ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል። የክለቡ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስለ አማኑኤል ገብረሚካኤል የትላንት ምሽቱን ጉዳት አስመልክተው በማህበራዊ ገፃቸው ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል ። ” ጥቃቅን የሚመስሉ ጉዳቶች የጭካኔ ታክሎች ብዙዎችን ከህልማቸው አሰናክለዋል:: ለዚህ ከባድ ጥፋት ክእግዜር ቀጥሎ […]

አትሌቲክስ

እሁድ በዓለም ሻምፒዮና የሚጠበቀው አትሌት በሪሁን አረጋዊ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ አድርጓል!

የፊታችን ቅዳሜ ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ በሚካሄደው ተጠባቂው የ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲከስ ሻምፒዮና ከሚካፈሉ እና በውጤት ከሚጠበቁ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አንዱ በሪሁን አረጋዊ ወደ ሰርቢያ ከማቅናቱ በፊት ለወገኖቹ ዕርዳታ አድርጓል። አትሌት በርሁን ዕርዳታውን ለ400 ሰወች ከ60 በላይ ኩንታል እህል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንዲደርስ አድርጓል።

ዜናዎች

የጨዋታ ማራዘም መረጃ!

በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በወጣው መርሃ ግብር መሰረት መጋቢት 21/2016 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ባህር ዳር ከተማን ከወልቂጤ ከተማ ያገናኛል። ነገር ግን የ2015 የሊጉ እጩ ኮከብ ተጫዋች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፍት ምክንያት ጨዋታው ላልተወሰን ጊዜ መራዘሙን እየገለፅን በቀጣይ የሚወሰነውን የመጫወቻ መርሃ ግብር የምንገልፅ ይሆናል። የኢትዮጵያ […]

ዜናዎች

የአለልኝ አዘነን 23 ቁጥር ማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ ክለቡ ወሰነ !

በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ አስታወቀ። የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ ስፍራው በመገኘት ገልፀዋል። በዚህም አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰው የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብሰው ሆኖ በክብር […]

ዜናዎች

አዲሱ ሙሽራ አለልኝ አዘነ ከዚህ አለም በድንገት ማለፉ – ጥልቅ ሀዘን !

ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ በአርባ ምንጭ ይፈፀማል! በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን፤ በቁርባን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ። ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

የፊታችን ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ ለሚካሄደው በ45ኛው ዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የሚካፈለው የልዑካን ቡድን ዛሬ በቤለቪው ሆቴል ተሸኘ :: በመርሀግብሩ መጀመሪያ የቡድኑ መሪና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ተስፋዬ አስግዶም ስለቡድኑ አጠቃላይ ቆይታቸው የወሰዱት የአካል እና የስነልቦና ስልጠና ለውጤታማነት እንደሚያበቃቸው በመተማመን መልካም እድል ለቡድኑ ተመኝተዋል ። አትሌቶችን በመወከል ደሞ አትሌት ለምለም […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

አረንጓዴው ጎርፍ በአክራ ሰማይ ስር ተከታለው በመግባት አሸንፈዋል !

  በጋና አክራ የ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተዋል በ5000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታለው ገብተዋል መዲና ኢሳ ብርቱካን ሞላ መልክናት ውዱ በወንዶች የ3000 ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ለሃገራችን የወርቅ ሜዳልያ በአትሌት ሳሙኤል ፍሬው ተገኝቷል ሳሙኤል ፍሬው 8:24.30 ወርቅ 4ኛ አብርሃም ስሜ 8:27.30 5ኛ ሚልኬሳ ፍቃዱ 8:27.55

አፍሪካ ዜናዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ጀምሯል!

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ለ26 ተጫዋቾች በትናንትናው ዕለት ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቾቹም በዛሬው ዕለት በመሰባሰብ ከቀትር በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመርያ ልምምዳቸውን ማከናወን ችለዋል። ኢትዮጵያ እና ሌሶቶ ሁለት ጨዋታዎችን የሚያከናወኑ ሲሆን ጨዋታዎቹም መጋቢት 12 እና መጋቢት 15/2016 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከናወኑ ይሆናል። @EFF

English አትሌቲክስ

የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ፅጌ ገ/ሰላማ ቀዳሚ ሆና በመግባት አሸንፋለች !

  Tsigie Gebreselama sets a meet record with the ninth-best performance in world history in 29:48.34 to win the women’s Paris 10,000m run at The TEN! በአሜሪካ በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ፅጌ ገ/ሰላማ ቀዳሚ ሆና በመግባት አሸንፋለች። ከፓሪስ ኦሎምፒክ ተስፋዎቻችን መካከል አንዷ የሆነችው ፅጌ ርቀቱን ለመፈፀም የፈጀባት ጊዜ (29:48.34) የውድድሩ ሪከርድ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን […]

አፍሪካ ዜናዎች

ብሔራዊ ቡድኑ ከሌሶቶ ጋር ለሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሐሙስ መጋቢት 12 እና እሁድ መጋቢት 15 ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ ለሚያደርጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እስከ ነገ 6፡00 በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል። ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች ሰዒድ ሀብታሙ – አዳማ ከተማ ፍሬው ጌታሁን […]