ከ14ኛው ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታዎች አንዱ የነበረውና ዛሬ የተደረገው የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ሲሆን በጨዋታው የመጠናቀቂያና የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል የለወጠው ያሬድ ባዬ ከጨዋታው በኃላ ከኢትዮኪክ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።በቅድሚያ ለያሬድ ጎሏን በማስቆጠሩ የተሰማውን ደስታ እንደገልፅልን ለጠየቅነው ” በጣም ትልቅ የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ። ከጨዋታው ትልቅ ግምት መሠጠትና የቅዱስ […]
Author: Ethokick
ዓፄዎቹ መሪነታቸውን ተቀዳጅተዋል !
የ14ኛወ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ቀን ዛሬ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች አምስት ጎሎች ተቆጥረዋል።በረፈድ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ በ2 ለ2 የአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ ከሰአት የተካሄደው ጨዋታ የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በጭማሪ ደቂቃዎች ባገኙት ፍፁም ቅጣት ምት ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፈው ወጥተዋል።
የቤትኪንግ ሊግ – የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ – የሁለተኛ ዙር14ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል .የመጀመሪያው አጋማሽ አራት ግቦችን አሰተናግድዋል ። ሰበታ ከተማ በፍፁም ገብረማርያም በ10ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳሚውን ጎል አስቆጥሮል ። ድሬዎችም በ23ኛው ደቂቃ ላይ በጁኒያስ ናንጄቦ አቻ ሆነዋል ። ፍፁም በ38ኛው ደቂቃ ላይ ሰበታን መሪ ቢያደረግም ድሬዎች 41ኛው ደቂቃ በሄኖክ ኢሳያስ አቻ ሆነው ጨዋታው ተጠናቋል […]
በስዊድን ሊግ የሚጫወተው ቢኒያም በላይ በግል ጉዳይ ኢትዮዽያ ይገኛል !
ለስዊዲኑ ኡሚያ ኤፍ ሲ ክለብ የመስመር ተጨዋች የነበረው ኢትዮዽያዊው ቢኒያም በላይ በግል ጉዳይ በአሁን ሰአት በኢትዮጵያ እንደሚገኝ መረጃዎች አመልክተዋል። በስዊዲን Superettan የክለቦች ውድድር ላይ ለክለቡ ኡሚያ ኤፍ ሲ ከኮሮና እረፍት መልስ ሊጉ ሲጀመር በተደጋጋሚ የጨዋታው ኮከብ በሚል ሽልማት ያገኘውና በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ የነበረው ቢኒያም በላይ በአሁኑ ሰአት በአገር ቤት እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል። የኡሚያ የመስመር […]
የዝውውር ➖መረጃዎች
ወልቂጤ ከተማ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በ17 ጎሎች እየመራ የሚገኘውና የኢትዮዽያ ቡናው የአቡበክር ናስር እንዲሁም የኢትዮዽያ ቡናው ተከላካይ የሬድዋን ናስር ወንድም የሆነው የአማካይ ተጨዋችጅብሪል ናስርን ከሰበታ ከተማ ወጀ ወልቂጤ ከተማን ተቀላቅለዋል። የፊታችን ማክሰኞ ጅብሪል ለአዲሱ ክለቡ የሚሰለፍ ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮዽያ ቡና የሚካሄደው ጨዋታ ሶስስቱን ወንድማማቾች በአንድ የጨዋታ መስክ ይታዮም ሆናል ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅዱስ ጊዮርጊስ […]
ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች በዋልያዎቹ ለመካተት ጥያቄዎችን ማቅረብ ቀጥለዋል
በእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ ከተሳካለቸው ተጨዋቾች ተርታ የሚመደበው እና በጎንደር ቋራ የተወለደው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ሳልልህ ከእስራኤል ይልቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆንኑ ለኢትዮ-ኪክ በተደጋገሚ ገልጿል። ተጨዋቹ በቀጣይ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን የመካተት ፍላጎቱን በከፍተኛ ተስፋ አስምሮበታል።አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሶስት ወር በኃላ ከማዳጋስጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የአገር ውስጥ ሊግ ቀጣይ ከተማ በሚካሄድት […]
ኢትዮዽያዊው ዛሬም ጎል አሰቆጥሮ በግብፅ ሊግ መሪነቱን አጠናክሯል !
በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ለቡድኑ ወሳኝ እና ብቸኛ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገው ኢትዮዽያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ዛሬም ጎል በማሰቆጥር ቡድኑ ምስር ኤል ማካሳ ከታላቁ ዛማሊክ ቀጥሎ በሁለተኝነት ሊጉን እንዲከተል የበኩሉን አድርጓል። በ14ኛ ሳምንት የዛሬው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ የሽመልስ ምስር ኤል ማካሳ ተጋጣሚውን ዋዲ ዳግልን በ3 ለ1 እንዲያሸንፍ ኢትዮዽያዊው ሽመልስ በቀለ በ23ኛው ደቂቃ […]
ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-2 አዳማ ከተማ
የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ የሊጉን የጎል ድርቀት የከፈተ ሲሆን በአጠቃላይ በጨዋታው ስድስት ጎሎች ተቆጠረዋል። እስካሁን በባህርዳር ስታዲየም ከተደረጉት አራት ጨዋታዎች ከተቆጠሩት 8 ጎሎች ስድስቱ በዚህ ጨዋታ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 4 ለ 2 ባሸነፈበትጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጎል የሚሆኑ አጋጣሚዎች እና በቡድኖቹ እንቅስቃሴም ክስተቶችም ተስተውለዋል። […]
ወላይታ ድቻ 0 – 0 ባህርዳር ከተማ
የ12ኛው ሳምንት የመጀመራያው ጨዋታ ተጠናቋል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ በጭማሪ ሰአት ባህርዳር የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ ባዬ ገዛኸህ ወደጎል ሳይለውጠው ቀርቶ ጨዋታው ያለ ጎል ተጠናቋል። ከወላይታ ድቻ በኩል በረከት ወልዴ በቀይ ካርድ ከሜዳው ወጥቷል።
የአትሌት ለምለም ኃይሉ ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ፀደቀ !
በፈረንሳይ ሌቪን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የቤትውሰጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አትሌት ለምለም ያስመዘገበችው የ 4 01.57 ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ ከ 20 ዓመት በታች የቤት ውስጥ የ 1500 ሜትር የዓለም ሪኮርድ ሆኖ ማፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ በድህረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።