በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ለቡድኑ ወሳኝ እና ብቸኛ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገው ኢትዮዽያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ዛሬም ጎል በማሰቆጥር ቡድኑ ምስር ኤል ማካሳ ከታላቁ ዛማሊክ ቀጥሎ በሁለተኝነት ሊጉን እንዲከተል የበኩሉን አድርጓል። በ14ኛ ሳምንት የዛሬው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ የሽመልስ ምስር ኤል ማካሳ ተጋጣሚውን ዋዲ ዳግልን በ3 ለ1 እንዲያሸንፍ ኢትዮዽያዊው ሽመልስ በቀለ በ23ኛው ደቂቃ […]
Author: Ethokick
ቅዱስ ጊዮርጊስ 4-2 አዳማ ከተማ
የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ የሊጉን የጎል ድርቀት የከፈተ ሲሆን በአጠቃላይ በጨዋታው ስድስት ጎሎች ተቆጠረዋል። እስካሁን በባህርዳር ስታዲየም ከተደረጉት አራት ጨዋታዎች ከተቆጠሩት 8 ጎሎች ስድስቱ በዚህ ጨዋታ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 4 ለ 2 ባሸነፈበትጨዋታ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጎል የሚሆኑ አጋጣሚዎች እና በቡድኖቹ እንቅስቃሴም ክስተቶችም ተስተውለዋል። […]
ወላይታ ድቻ 0 – 0 ባህርዳር ከተማ
የ12ኛው ሳምንት የመጀመራያው ጨዋታ ተጠናቋል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ በጭማሪ ሰአት ባህርዳር የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ ባዬ ገዛኸህ ወደጎል ሳይለውጠው ቀርቶ ጨዋታው ያለ ጎል ተጠናቋል። ከወላይታ ድቻ በኩል በረከት ወልዴ በቀይ ካርድ ከሜዳው ወጥቷል።
የአትሌት ለምለም ኃይሉ ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ የዓለም ሪከርድ ሆኖ ፀደቀ !
በፈረንሳይ ሌቪን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የቤትውሰጥ የአትሌቲክስ ውድድር በ1500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማሸነፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ አትሌት ለምለም ያስመዘገበችው የ 4 01.57 ውጤት ከዓመት ቆይታ በኃላ ከ 20 ዓመት በታች የቤት ውስጥ የ 1500 ሜትር የዓለም ሪኮርድ ሆኖ ማፅደቁን የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ በድህረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ ክብረወሰን ሰበረች!
ኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በፈረንሳይ ሊቫን በተረደረገው የአለም የቤት ውስጥ በ1500 ሜትር ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እ.ኤ.አ. በ 2014 (በ3 55.17) ተይዞ የነበረውን አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ3 53.09 ሰዓት በመግባት አዲስ የዓለም የቤት ውስጥ ሪኮርድ ባለቤት ሆናለች
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፈረንሳይ ሌቪን ደምቀው አመሹ
በፈረንሳይ ሌቪን በተደረገው የ2021 የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል።በሴቶች የ1500ሜትር የአምናው የሌቫን አሸናፊ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዘንድሮ በርቀቱ 3: 53.09 ሪከርዱን ጭምር በመስበር አሸናፊ ሆናለች። ከቀናት በፊት የአለም አትሌቲክ ፌዴሬሽን ባሳወቀው መሠረት ያለፈው ከ20 አመት በታች በሌቫን ያሸነፈቸው የ1500ሜትር ውድድር አዲስ የአለም ሪከርድ ሆኖ እንዲመዘገብ የተደረገላት አትሌት ለምለም ሃይሉ በምሽቱ […]
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በቀናት ልዪነት ሌላኛውን ድል ደግማለች !
ከቀናት በፊት በፈረንሳይ ላቪስ በተደረገው የ1500 ሜትር የቤትውስጥ ውድድር በኢትዮዽያዊቷ ድንቅ አትሌት በገንዘቤ ዲባባ ለ7አመት ተይዞ የነበረውን የዓለም ሪከርድ የሰበረችው ጀግናዋ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ዛሬ ደግሞ በ 800 ሜትር በቁጥሬ ዱለቻ እ.ኤ.አ 1999 ተይዞ የነበረውን የ800ሜትር 1 :59.17 በማሻሻል 1: 57.52 አዲስ የአለም ፈጣኑን ሰአት አስመዝግባለች።
የባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም
የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሶስተኛው አስተናጋጅ ከተማ ባህርዳር ከ12ኛው እስከ 16ኛው ሳምንት ጨዋታዎች የሚካዱበት የባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም በቀጣይ ሳምንት ውድድሮችን ለማካሄድ ዝግጁነቱን እጠናቆ አሁን ገፅታው ይሄንን ይመስላል ። ቀጣይ አዘጋጅ ለውድድሩ ያመች ዘንድ ፡ 6 መለማመጃ ሜዳ 1 ደረጃውን የጠበቀ ስቴዲየም 60 ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹ ሆቴሎች አዘጋጅታለች ባህርዳር ከተማ ሰፖርት ክለብ
የብሔራዊ ቡድን የሸገር ዝግጅት ዛሬ ተጠናቋል !
የብሔራዊ ቡድን የሸገር ዝግጅት ዛሬ ተጠናቋል ! የሳምንት ዝግጅቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ይገለፃል ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባቱ እና ረዳቶቻቸው የሁለተኛው ምዕራፍ የአንድ ሳምንት ቅደመ ዝግጅታቸውን ዛሬ አጠናቀዋል። የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን አዲስ ንድፈ ሃሳብ መሠረት ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያው ምዕራፍ ለሶስት ቀናት በጅማ የትውውቅ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። በካፍ አካዳሚ መቀመጫቸውን አድርገው ለአንድ ሳምንት በዘለቀው […]
አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን
“የዲ.ኤስ ቲቪ ህይወት ነበርኩ: ምን ያደርጋል ‘አትሩጥ አንጋጠህ’ ይላሉ እናቶች ሲተርቱ : የኢትዮጵያ እግርኳስ እንደዛ ነው ” – አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የድሬደዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን በሱፐር ስፖርት ተወዳጅ እንደነበሩ ይታወሳል። አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን ከክለቡ በስምምነት መሰናበታቸውን መረጃዎች ቢወጡም ጉዳዪን አሰልጣኙ የሰሙት በማህበራዊ ሜዲያ እንደሆነ ይናገራሉ። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከኢትዮ ኪክ […]