ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የዛሬው ጨዋታ በጣሞ አስፈላጊ ነበረ። ሶስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት ነበር የመጣነው ግን አልተሳካም ፣ ሃዋሳ ላይ ተሻሽለን እንቀርባለን”.- ረመዳን የሱፍ

በወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል የ10ሺህ ብር ተሸላሚ የነበረውና በዛሬው ጨዋታ ድንቅ ጎል ያስቆጠረው ረመዳን የሱፍ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። ዛሬ ስላስቆጠረው ጎል ” ቡድናችን እዚህ ከመጣን በኋላ ምንም ውጤት አልያዝንም። እዚህ ድሬዳዋ ላይ የመጨረሻ ጨዋታችን ነው ። ሶስት ነጥብ ይዘን ለመውጣት ነበር። ወሳኝ ጎል በማግባቴ በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ። ቡድንኔም ከጭንቀት […]

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሚን አስካር እስከ 2022 በኖርዌ ዋናው ሊግ ለመጫወት ውሉን አራዝሟል !

  በኖርዌ ዋናው ሊግ ለክሪስቲያሱድ እየተጫወተ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሚን አስካር   እ.ኤ.አ እሰከ ፈረንጆቹ  2022 ለመጫወት  ውሉን ማራዘሙን የኖርዌው ክለብ አስታውቋል። በኖርዌ ለዋናው ሊግ ‘Eliteserien’ ተወዳዳሪ ለነበረው  ክለብ እጅግ ሲበዛ ተወዳጅ የነበረው ትውለደ ኢትዮጵያዊው አሚን ሱሊማን አስካር የኖርዌይ ዋናው ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ክሪስቲያሱድ  ክ2019 ዓ.ም  ከተቀላቀለ በኃላ እስከ 2022  ዓ.ም ለመጫወት የሚያሰችለወን   ውሉን ማራዘሙን  ክለቡ […]

ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ አምበሉን ጨምሮ አራት ወሳኝ ተጫዋቾቹን አገደ ! – ተጫዋቾቹ አዲስ አበባ እንዲመለሱም ተወሰነ!

የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር በ2013 ዓ.ም በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው እንደሆነ ይታወቃል። ቡድኑ በትላንትናው የቤትኪንግ አቻ ውጤት ማጠናቀቁም አይዘነጋም። ክለቡ ዛሬ እንዳሳወቀው ከሆነ ቡድኑ አሁን ላይ ውጤት አርኪ የሚባል እንቅስቃሴዎችን እያደረገ አለመሆኑ አሳውቆ አልፎ አልፎ በቡድኑ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ተጫዋቾቻችን የሚያሳዩት ያልተገባ ባህሪና የስነ-ምግባር ጉድለት እጅጉን የሚያስቆጭ እንደሆነ አሳውቋል። ትናንት ቡድኑ በድሬዳዋ ስታዲየም […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“በምንፈልገው መንገድ ይህን ውጤት ከጥሩ ጨዋታ ጋር ማሸነፍ ስለቻልን በጣም ደስ ብሎኛል ” -ፍሬው ጌታሁን

የ20ኛው ሳምንት የዛሬ ምሽቱ ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ የድሬደዋ ከተማው ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን በሱፐር ስፖርት ቴክኒካል ቲም የምሽቱ ጨዋታ ኮከብ ተብሏል። ከጨዋታው በኋላ ፍሬው በሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታም አድርጓል። ስለ ዛሬው ጨዋታው ? ” በርግጥ እንበቀላለን እያልን ነበር ከልጆቹ ጋር ። እንፈልገው ነበር ይህን ውጤት በምንፈልገው መንገድ  ይህን ውጤት  ስላገኘነው እና ከጥሩ […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የአለም ፍፃሜ አይደለም ፣ ድክመቶች እና ጥንካሬዎችን እያየን ነው፣ አሁንም በጣም ጥሩ አቋም ላይ ነን ” አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል

  እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ከአዲሱ  ክለባቻው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሶስተኛ ጊዜ  ጨዋታቸውን ዛሬ አድርገው የዛሬውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ከጅማአባጅፋር ጋር አጠናቀዋል።   ከጨዋታ በኃላ ከሱፐር ስፓርት ቆይታ አድርገዋል። በጨዋታው ደስተኛ አይመስሉም ? ” ሁሌም ጨዋታ ሲኖረን ቀደም ብዬም እንደተናገሩት ጨዋታ ሲኖረን የምንገባው አሸንፈን መውጣት ነው ። እናም የአለም ፍፃሜ አይደለም ፣ ደግሞም ጨዋታው ከባድም እንደሚሆን […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ዘንድሮ እንተርፋለን፣ አንተርፍምም ለማለት ይከብዳል ፤ ኳስ ነውና ምን እንደሚፈጠር አብረን እናያለን” ➖ተመስገን ደረሰ (ጅማ አባጅፋር)

የጅማ አባጅፋሩ ተመስገን ደረሰ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ፈጣኗን ጎል አስቆጥሯል። ተመስገን በሊጉ ስድስት ጎሎችያስቆጠረ ሲሆን የዛሬዋን ጨምሮ ሁለት ጎሎች ፈጣን ጎሎች ሆነው ተመዝግበዋል። ተመስገን ከጨዋታ በኃላ ከሱፐር ስፓርት ቆይታ አድርጓል። ዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድኑን ወጥ ያልሆነ ውጤት ይታይበታል። ስለዛሬው ጨዋታ ያለው አመለካከት? ” ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እንደመጫወታችን ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር። እኛም ግምት ሰጥተን […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ትልቅ ነገር አቅደናል፣ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ለመውጣት ፣አይከብደንም ያንንም እናሳካዋለን ” ➖ወንድማገኝ ኃይሉ

በ20ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የምሽቱ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ የሃዋሳ አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉ ባስቆጠረው ብቸኛ ጎል ጨዋታው ተጠናቋል።ከጨዋታው በኋላ ወንድማገኝ ከሱፐር ስፓርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። ጎሉን ስታስቆጥር የነበረህ ስሜት ? “በጣም ደስ ብሎኛል በጣም ደስ ያለኝ ደግሞ ማሸነፊያ ጎል ሆኖ ጨዋታው ካለቀ በኃላ ውጤቱን ስናይ በጣም ነው ደስ ያለኝ […]

ዜናዎች

” ወላይታ ድቻን ከፍ ማድረግ ነው ዘንድሮ የምንፈልገው፤ ያሳደገን ቡድንም ስለሆነ ” -ቸርነት ጉግሳ

የወላይታ ድቻ በጥሩ አቋም ላይ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንዱ ቸርነት ጉግሳ ነው። ቸርነት ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ በአቻ ውጤት እንዲወጣ ሁለተኛ ጎል በ83ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል።ከጨዋታው በኋላ ቸርነት ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንዴት እየሄደ ነው እየሄደ ያለው ? “የዘንድሮው የውድድር ዓመት አጀማመሬ አሪፍ ነበር መሃል አካባቢ ትንሽ የመቀዛቀዝ ነበር ከጉዳት ጋር ነገር ግ አሁን […]

ዜናዎች

የወላይታ ድቻ ተጨዋቾቹ ከኮቪድ ነፃ ናቹ ሲባሉ አሰልጣኝ ዘላለም በዛሬው ጨዋታ አይኖርም !

በቤትኪንግ የ19ኛው ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻ አንድም ተቀያሪ ተጨዋች ሳይኖረው በ11 ተጨዋቾች ብቻ ሃዋሳ ከተማ ገጥሞ ጨዋታን በ3 ለ 2 ተሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወሳል። ከቀናት በፊት ተቀያሪ ተጨዋቾች ያልነበረው እና  በአጥቂ ቦታ ላይ ግብ ጠባቂዎቹ መክብብ እና አብነት   ያሰለፈው ወላይታ ድቻ በዛሬው የምርመራ ውጤት ደግሞ ከእዮብ አለማየሁ ውጪ ሁሉም የወላይታ ዲቻ ተጫዋቾች ከኮቪድ ነፃ ናችሁ ሲባሉ […]

አፍሪካ ዜናዎች

በልምምድ ሜዳ ህይወቱ በድንገት ያለፈው የአማካይ ቦታ ተጨዋች !

የጊኒ እግር ኳስ ዛሬ በሀዘን ውስጥ ይገኛል። ለጊኒ የዋናው ሊግ HAFIA FC ክለብ በአማካይ ቦታ ተጨዋች የነበረው ወጣት ሞሀመድ ላቲጌ ካማራ የተባለው ተጨዋች በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ አልፏል።የ24 አመቱ ተጨዋች ሞሃመድ ላቲጌ ህይወት በድንገት ያለፈው ዛሬ ረፋድ በኖንጎ ከቡድን ጓደኞቹ ጋር መደበኛ ልምምድ እየሰሩ ሳለ ድንገት ጥሩ ያልሆነ ስሜት ተሰምቶት ብዙም ሳይቆይ ራሱን ስቶ ሲወድቅ የቡድን […]