በኔዘርላንድ ሄንጌሎ ምሽቱን በተደረገ የ10ሺ ሜትር የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድር ላይ ከሁለት ቀናት በፊት በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊት በሆነችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ተሻሽሎ የነበረው እና ላለፉት 5 ዓመታት በአትሌት አልማዝ አያና ተያይዞ የነበረውን ሪከርድ በሁለት ቀናት ልዩነት በምሽቱ ውድድር ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል። ከቀናት በፊት አትሌት ሲፋን ሀሰን ተሻሽሎ የነበረው 29:06.82 ክብረወሰን በአትሌት ለተሰንበት ግደይ […]
Author: Ethokick
እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየታቸው ተሰማ !
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከወራት በፊት የከለቡ ዋና አሰልጣኝ አደርጎ ከሾመው እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ጋር መለያየቱ እየተዘገበ ይገኛል። ከደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት ከወራቶች በፊት የተለያየው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር እንግሊዛዊውን አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል ። በአንፃሩ ፈረንሰኞቹ ከእንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ጋር የአጭር ጊዜ ስምምነት እንደነበራቸው ሲገለፅ አሰልጣኙም […]
-ኢትዮዽያ የምትካፈልበት የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የድልድሉ ቀን ተራዘመ ! – የአፍሪካ ዋንጫ ሊራዘም ይችላል ?
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ዕጣ ማውጣት ድልድል ቀኑን ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑን አስታውቋል ፡፡ ካፍ ቀደም ብሎ የእጣ ማውጣት ቀኑን June 25 ከሶስት ሳምንት በኃላ እንደሚያካሄድ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ቀኑን ላልተወሰነ ጊዜ ያራዘመ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ካፍ አዲሱ የእጣ ማውጣት ቀኑን በቅርቡ ይፋ የሚይደርግም ይሆናል ፡፡ ዋልያዎቹ ከስምንት ዓመት […]
ለባህርዳሩ የሴካፋ ሻምፒዮና – ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ!
የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ የሚመራ ሲሆን ለ35 ተጫዋቾችም ጥሪ አድርጓል። ወደ አፍሪካ ዋንጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲያልፍ የቡድኑ አባላት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል እድሚያቸው […]
የመኪና አዳጋ ያጋጠመው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ፓትርክ ማታሲ ወቅታዊ መረጃ
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኬንያዊው ግብ ጠባቂ ፓትርክ ማታሲ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ መጠናቀቁን ተከትሎ ያሳለፍነው ቅዳሜ ረፋድ ላይ ከ አዲስ አበባ ወደ ኬንያ ወደ ቤተሰቡ ያቀናው። በአንፃሩ ትላንት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ኬኒያዊው ፓትሪክ ማታሲ በምዕራባዊው ኬኒያ ከካፕሳቤት ወደ ካካአመንጋ ከተማ ከቤተሰቡ ጋር በፍጥነት በመጓዝ ላይ ሳለ የመኪና መገልበጥ አደጋ አጋጥሞት በፍጥነት ወደ አቅራቢያ ሆስፒታል መወሰዱ መዘገቡ ይታወሳል። […]
አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካው ካይዛር ቺፍስ ክለብ እይታ ውስጥ ገብቷል!
የዘንድሮ የውድድር ዓመትን በስኬት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካው ካይዛር ቺፍ እይታ ውስጥ የገባ ይመስላል። መረጃዎች ዛሬ እንደተሠሙት ከሆነ የደቡብ አፍሪካው የካይዘር የኢትዮዽያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር በቀጣዩ የውድድር ዘመን በማስፈረም የዛምቢያውን አጥቂ ላዛሩስ ካምቦሌን ለመተካት ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል፡፡አቡበከር ናስር በ2013 የውድድር አመት 29 ግቦችን በማስቆጠር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሲሆን […]
3ቱም የትግራይ ክልል ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ እንደሚሳትፉ አሳወቁ!
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግንቦት 24ቀን 2013ዓ.ም ከ3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ጋር ስለ ቀጣይ የውድድር ዘመን ተሳትፏቸው በተመለከተ ውይይት አደረገ። በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል እና የማርኬቲንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ እና የኢ.እ.ፌ ዋና ጸሀፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን […]
“ጎል ለማስቆጠር ፈጣሪ ነው የረዳኝ ፣ፈጣሪን ጠየኩት አደረገልኝ ለዛም ደግሞ ደስ ብሎኛል ” -ተመስገን ብርሃኑ
በሀዲያ ሆሳዕና በዛሬው ጨዋታ ከተቆጠሩት ሦስት ጎሎች የመጨረሻውን እና የውድድር ዓመቱ 369 የማሳረጊያ ጎል ያስቆጠረው ተመስገን ብርሃኑ ነው። ታዳጊው ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። በቅድሚያ እንኳን ደስ ያለህ ” ያው እንኳን አብሮ ደስ አለን። ጎል ለማስቆጠር ፈጣሪ ነው የረዳኝ። ፈጣሪን ጠየኩት አደረገልኝ ለዛም ደግሞ ደስ ብሎኛል “ ጎሉን ካስቆጠርክ በኃላ ማሊያ ለማውለቅም ፈልገህ ነበር ፣ […]
“ለዋንጫ የተሰራ ቡድን ነበር የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን “-ሚካኤል ጆርጅ (ሀዲያ ሆሳዕና)
ሚካኤል ጆርጅ የሀዲያ ሆሳዕና የአማካይ ስፍራው ተጨማሪ ሃይል በመሆን ጠንካራ ሚና በሃዋሳ ቆይታው ተጫውቷል። በውድድሩ የመጨረሻው ቀን ሚካኤል ከሱፐርስፓርት ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርጓል። አራተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን በተመለከተ ? “ቡድኑ እንደመጣበት መንገድ ሁለተኛ ደረጃ ለእኛም ይገባ ነበረ ። እዚህ ሃዋሳ ላይ ስንመጣ ታዳጋዎቹ ከተወሰኑ ልምድ ካላቸው ጋር ነው አጣምሮ ለመጫወት የሞከርነው። የመጀመሪያውን ጨዋታዎች በ8 ተጨዋቾች […]
“በእግርኳስ ሆኜ ማድረግ የማሰበው ለእናትና አባቴ የተመቻቸ የሚኖሩበትን ቤት ነው፣ ኢንሽ አላህ ይሳካል ብዬ አስባለሁ “አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)
የ2013 የቤትኪንግ ኢትዮዽያን በ29ጎሎች በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ያጠናቀቀው በአቡበከር ናስር የውድድር ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል። ወላጆቹ ዛሬ በስታዲየም እንደሚታደሙ ቀድሞ ያውቅ ነበረ? ” ምንም የማውቀው ነገር የለም ማን እንዳመጣቸው፣ ይመስለኛል የሱፍ መሠለኝ።በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ። ያላሰብኩት ነገር ቤተሰቦቼ መጥተው ማየታቸው አንደኛ በጣም ደስ ብሎኛል” በእግርኳስ ተጨዋችነት ሆኖ ማድረግ አለብኝ ከሚለው ነገር ? […]