በካሜሩን አስተናጋጅነት ለ33ኛ ጊዜ በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚደረግበት ይፋ ሆኗል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን ቀደም ብሎ ቀኑን June 25 በሚል ካሳወቀ በኃላ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል። ይሁንና ካፍ የመጨረሻ ዕጣ ማውጣት ድልድል ቀኑን እሁድ ነሐሴ 9/2013 (August 15, 2021) ቀን በያውንዴ በሚገኘው ፓሌስ […]
Author: Ethokick
– ወደ ቶኪዮ ዛሬ ተጓዥ ከሆነው ሁለተኛ ዙር ውስጥ ሦስት ሰዎች ከኤርፖርት ተመላሽ ሆነዋል!
በቶኪዮ 2020/2021 ኦሎምፒክ ኢትዮዽያን አትሌቲክስ የሚወክሉ እና የሁለተኛ ዙር ተጓዞች ዛሬ ምሽት ወደ ጃፓን አምርተዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዛሬ ከሰዓታት በፊት በፌስቡክ ገፁ ይፋ ካደረገው ተጓዥ ስም ዝርዝር ውስጥ ሦስት የልዑካን አባላት ኦሎምፒክ ለመሄድ ኤርፓርት ደርሰው ከኤርፓት ተመላሽ ተደርገዋል ። በፌዴሬሽን ብዙም ግልፅ ባልሆነው አሰራር አትሌት አላያም የህክምና ባለሞያ ወይም ልዑካን ወደ ቶኪዮ መሄዱን አልያም […]
ሰለሞን ቱፋ ከ ሩሲያዊው ጋር ለነሀስ ይጫወታል !
የጃፓኑን ተጋጣሚው ሰርጅዮ ሱዙኪ በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፈው ሰለሞን ቱፋ ደምሴ በቱኒዚያው ተፎካካሪው በነጥብ ልዩነት ቢሸነፍም የተሻለ ነጥብ ስላስመዘገበ ለነሀስ ሜዳሊያ ይጫወታል። ሰለሞን ቱፋ ከ ሩሲያዊው አርታሞኖቭ ሚኪሀሊ ጋር ነው የተገናኘው። ሰለሞን የሚያሸንፍ ከሆነ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ታገኛለች። @EOC Olympic
የጣና ሞገዶች የኤርትራውን ኮከብ አሊ ሱሌይማንን አስቀርተዋል!
የኤርትራ ከ 23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ የሆነው አሊ ሱሌይማን ለ ባሕር ዳር ከነማ ለመጫወት ተስማምቶ ፊርማውን አኑሯል። በሴካፋ የመክፈቻ ጨዋታ ባሳየው እንቅስቃሴ የበርካቶችን ተኩረት ወስዶ የነበረው እና በሴካፋ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ ለ ኤርትራ ብሔራዊ ቡድን የተገኙትን ሶስቱንም ጎሎች ማስቆጠር የሴካፋ ከፍተኛ ጎል አሰቆጣሪ የሆነው ፈጣኑ አጥቂ በቀጣይ ዓመት በቤትኪንግ የሚታይ ተጨዋች ይሆናል። […]
– የሴካፋ አዘጋጅ ኢትዮጵያ ከሻምፒዮናው ውጪ ለመሆን ተቃርባለች! – የተሻለ ሁለተኛ ሆኖ ማለፉ ነገ ይታወቃል !
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 10 እስከ 25/2013 ዓ.ም ድረስ በዘጠኝ የሴካፋ አባል አገራት መካከል በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ውድድር የምድቡ ሃላፊዎች እየተወቁ ይገኛል። ወደ ቀጣይ ዙር ኃላፊ የሚሆነውን ለማወቅ አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ ባደረጉት የምድብ ” ለ” የዛሬ ጨዋታ በ1 ለ 1 በአቻ በመጠናቀቁ ተከትሎ ቡሩንዲ በ4 […]
ቶኪዮ ከተጓዘው ከ100 በላይ የኦሎምፒክ ልዑካኑ ግማሹ ያህሉ ጥያቄ እያስነሳ ይገኛል!- አትሌቶች ተቀንሰው ለምን ልዑካኑ በዛ?
የ32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮሮና ምክንያት በተደጋጋሚ ሲራዘም ቆይቶ ነገ በታዋቂው የጃፓን አርክቴክት ኬንጎ ኩማ በተሠራው ባለ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በፈጀው እና 68ሺ ተመልካች በሚይዘው ስታዲየም ያለ ተመልካች በሚደረግ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በይፋ ይጀመራል። በታሪካዊው እና ተጠባቂው የቶክዮ ኦሎምፒክ ላይ የኢትዮዽያን ባንድራ በመከፈቻው ስነስርዓት ላይ ከፍ ለማድረግ ትላንት የተጓዘው የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ልዑካን ከስድስት ሰአታት ቆይታ በኃላ […]
-በቶኪዮ አየር ማረፊያ ለስድስት ሰዓታት ታግዶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኮቪድ ነፃ ሆነ !
ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ ኮሮና ምክንያት ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ተዘግቦ ነበረ ፣ይሁንና አሁን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑካን ቡድን ከቶኪዮ አየር ማረፊያ ወጥቶ ወደ ተመደበለት ቦታ መግባቱን የቡድኑ መሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ገልጸዋል። ነገ በሚጀመረው 32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ […]
– ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የተሳተፈበት ጨዋታ በሜክሲኮ 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል !
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያ ከምትሳተፍባቸዉ የስፓርታዊ ውድድሮች በተጨማሪም በእግር ኳስ ባለሙያም ተወክላለች። በቶክዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በእግር ኳስ ዳኝነት የወከለው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ረፋዱን የተደረገውን የወንዶች እግር ኳስ የምድብ ” ሀ ” ፈረንሳይ ክ ሜክስኮ ጨዋታ በ4ኛ ዳኝነት መርቷል። ጨዋታውን በዋና ዳኝነት አውስትራሊያዊውያኑ ዋና ዳኛ ክሪስ ቤዝ እንዲሁም ፣ አንቶን ሽቼቲኒን ( 1ኛ […]
– የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና የነገው የኢትዮጵያ ጨዋታ የሰዓት ለውጥ ተደረገ !
በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ቀጣዮቹን የምድብ አላፊዎች የሚታወቁበት የቀሪዎቹ የሶስት ጨዋታዎች የጨዋታ መርሐ ግብር በኩል የሰዓት ለውጥ ተደረጓል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ መካከል የሚደረገው የነገ ጨዋታ በቅድሚያ 10:00 ሰአት እንዲደረግ መርሐ ግብር ወጥቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተሻሻለው የውድድር ሰዓት በ8:00 ሰአት የሚደረግ ይሆናል። በወድድሩ መርሐ ግብር […]
ፈረሰኞቹ የ64 ዓመቱን ስርቢያዊ አዲስ አሰልጣኝ አድርገዋል !
የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን ይፋ አድርጓል። እንደ ክለቡ መረጃ አሰልጣኙ የ64ዓመቱ ስርቢያዊ ዝላትኮ ክራምፖቲች ሲሆኑቀደም ሲል የስርቢያን ከ17 ዓመት በታች እና ከ19 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በአፍሪካ የተለያዩ ቡድኖችን በማስልጠን የካበተ ልምድ ያላቸው እንደሆኑ ክለቡ ግልዖ አሰልጣኙ ካስለጠኑባቸው ክለባች መካከልም የሩዋንዳው ዜስኮ ዩናይትድ ፣ዲሞክራቲክ ኮንጎ ቲፒ ማዜንቤ ፣የደቡብ አፍሪካው ፖሎ ኪዊን ሲቲ […]