ዜናዎች

በባህርዳር ስታዲየም እገዳ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድንጋጤ ውስጥ ይገኛል!

የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን  ውድድሮች እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች በብቸኝነት ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር ብሔራዊ አለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እና የአፍሪካ የክለብ ሻንፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ በትናንትናው እለት ጥቅምት 7/2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ማሳወቁ ይታወሳል ።  በአንፀሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተጣለው እገዳው ድንጋጤ ውስጥ መሆኑ ታውቋል […]

አፍሪካ ዜናዎች

ሉሲዎቹ ወደ ዮጋንዳ ጉዞ ጀምረዋል !

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ከዩጋንዳ አቻው  የሚጫወቱት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት  በዛሬው እለት ከቀኑ 5 ሰዓት ወደ ካንፓላ የሚያመሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይገኛሉ። የፌዴሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው ሉሲዎቹ ባለፉት ቀናት በካፍ አካዳሚ ጠንካራ ልምምድ ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን ሁሉም በመልካም ጤንነት ይገኛሉ። የሉሲዎቹ አባላት ወደ ቦሌ ጉዞ ከመጀራለው በፊት ለቡድኑ የምግብ አገልግሎት ሲያቀርብ የነበረው […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

– የ2014 የውድድር ዓመቱን ባለሜዳዎቹ በድል ጀምረዋል! – ዳዊት የመጀመሪያው ቀይ ካርድ

የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 7 – ታህሳስ 15 ድረስ የመጀመሪያው ዙር ውድድር በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ ላይ የሚካሄድ ይሆናል። በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ቀናት በሚካሄደው የ2014 ውድድር የመክፈቻ ጨዋታው በሜዳው ባለቤት አሸናፊነት ተጠናቋል። በመጀመሪያውን ቀን የ2014 ቤትኪንግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ በ10 ቁጥሩ በመስፍን ታፈሰ ብቸኛ ጎል ጅማ አባ ጅፋርን 1 ለ 0 […]

Kenenisa2021
አትሌቲክስ ዜናዎች

ጀግኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶን ላይ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅቷል!!

ተጠባቂው የበርሊን ማራቶን መስከረም 16/ 2014 ይካሄዳል። የ39 አመቱ ቀነኒሳ በቀለን እእአ ከ2019 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ሀጂ አዴሎ የቀነኒሳን ብቃት ከባለፈው የበርሊን ማራቶን ጋር አነጻጽረው አሁን በጣም በተሻለ ብቃት ላይ እንደሆነና ክብረ ወሰን ለማሻሻልም የሚያስችል አቋም ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ቀነኒሳ እእአ በ2019 በተካፈለበት ማራቶን በኬኒያዊው ኢሉድ ኪፕቾጊ የተያዘዉን ክብረወሰን ለጥቂት (ለሁለት ሰከንድ) ሳይሰብረው መቅረቱ […]

ዜናዎች

ሽመልስ በቀለ ለሌላኛው የግብጽ ክለብ ፊርማውን አኖረ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አማካይና በግብፅ ሊግ የተሳካ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ከግብፁ ክለብ ምስር ኤል መቃሳ ጋር በመለያየት ለሌላኛው የግብፅ ክለብ ኤል ጎውናን ለቀጣይ ዓመት ለመጫወት ፊርማውን ብሔራዊ ቡድኑን ከመቀላቀሉ በፊት አኑሯል ። በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ አመታት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ዘንድሮ በ 11 ጎሎች አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ሽመልስ በቀለ በቀጣይም ዓመት በሌላኛው የግብፅ […]

ዜናዎች

ዋልያዎቹ አክራ ደርሰዋል- ጨዋታው የቀጥታ ሽፋን ያገኛል!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአምስት ሰዓታት በረራ በኋላ አክራ አየር ማረፊያ የደረሱ ቢሆንም ለኢንተርናሽናል በሪራ ከኢትዮጵያ የሰጡት የኮቪድ ምርመራ ውጤት አክራ ላይ ባለመቀበላቸው ቡድኑ ዳግም ምርመራ አድርጎል። በዚህም ለእያንዳንዱ ተጨዋች ከ6800 የኢትዮጵያ ብር በላይ ተከፍሎ የኮቪድ ምርመራ ማድረጋቸው ተሰምቷል። በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር ዓርብ ምሽት በ 4:00 የሚደርጉት የ2022 የዓለም ዋንጫ ቅድመ […]

ዜናዎች

የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ከጉዳት መልስ ዋልያዎቹን በቀጣይ ሳምንት ይቀላቀላል !

በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በባህርዳር በተካሄደው የሴካፋ ከ 23 አመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድር የብሄራዊ ቡድኑ ሁለተኛ አምበል የነበረው እና በዋናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ልምምድ ላይ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው ሀብታሙ ተከስተ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ማገገሙ ታውቋል።  በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባል የሆነውና ከሁለት ሳምንት በፊት በልምምድ ሜዳ ከሌላው የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋች ጋር በደረሰ ንክኪ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው […]

ዜናዎች

” ሰባት ቋሚ ተሰላፊዎቻችን በብሔራዊ ቡድን በመሆናቸው በዛሬው ጨዋታ ባይሰለፉም ጨዋታው ለቀሪ አባሎቻችንን መልካም አጋጣሚ ነው ” – አሰልጣኝ ስዩም ከበደ

ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሳምንታት በኋላ ኢትዮጵያን በመወከል የሚያደርገው የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ፋሲል ከነማ ለዝግጅቱ ይረዳው ዘንድ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ በ10:00 ሰዓት በአሰልጣኝ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን  ሚቾ ከሚሰለጥነው ዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል። የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮናው የፋሲል ከነማ ስፓርት ክለብ በቀጣይ ለሚጠብቀው ሀገራዊ እና […]

ዜናዎች

-ኢትዮዽያዊው አማካይ ሽመልስ በግብፅ ቆይታው የጎል ሪከርዱን አሻሻለ ! – የሱዳን የጎል ሪከርዱ እስካሁን አልተነካም!

በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው ኢትዮዽያዊው ሽመልስ በቀለ በዚህም ሳምንት የተለየ የሆነውን ጎል አስቆጥሯል። በግብፅ ፕሪምየር ሊግ ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች አንዱ የሆነው የአማካይ ስፍራው ሽመልስ በቀለ በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ክለቡ ምስር ለል መቃሳ በአል ሞካውሎን 3 ለ 2 ሽንፈን ቢያስተናግድም ሽመልስ በግብፅ ሊግ ቆይታው ያስቆጠረውን የጎል መጠን አሻሽሏል። ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ […]

አፍሪካ ዜናዎች

– ዓፄዎቹ አዲስ እና ነባር ተጨዋቾቹን በመያዝ ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ቀጥለዋል !

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው ፋሲል ከነማ ከሱዳኑ አሊሂላል ጋር ከጳግሜ 5 እስከ መስከረም 2/2014 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች በሜዳው ባህር ዳር አለማቀፍ ስታዲየም የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን እንደሚያደርግ የወጣው እጣ ድልድል ያመለክታል። ለዚህ ዝግጅትም ዓፄዎቹ ከቀናት በፊት አዲስ ያስፈራማቸውን እና በ2013 ሻምፒዮና የነበሩትን ነባር ተጨዋቾቹን በመያዝ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ  ዝግጅታቸውን በባህር ዳር እያደረጉ እንደሚገኝ […]