በደረጃ ሰንጠረዡ በስድስተኛ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በ18ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ከባህርዳር አቻነው በ2 ለ2 አቻ ውጤት ተለያይተዋል። በወልቂጤ በኩል ጎል ካስቆጠሩት እና ድንቅ ብቃት ላይ ከሚገኙ ተጨዋች አንዱ ወጣቱ ጫላ ተሺታ ለሁለተኛ ጊዜ የጨዋታው ምርጥ ተጨዋቾች ተብሏል።ጫላ ተሺታ ከጨዋታው በኋላ አጭር ቆይታ አድርጓል። –-ስለጨዋታው ሲናገር… ” ጨዋታው ትንሸ ከበድ ይላል። እነሱ ከሽንፈት ነበር […]
Author: Ethokick
“የቅ/ጊዮርጊሱ ዘሪሁን ሸንገታ እሱ ለእኔ የአንደኛ ዙር ምርጥ አሰልጣኝ ነው” ➖ ጊልበርት ሰለቧ (የሱፐርስፖርት -ተንታኝ)
የቤትኪንግ ኢትዮዽያ ፕሪምየር ከ2013 ዓ.ም ወዲህ በዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲታወቅ አምና ኬኒያዊያኑ ኮሜንታተሮች በርናልድ ኦቴዩ እና ጊልበርት ስለቧ ዘንድሮም ከዮጋንዳዊው ጋዜጠኛ አንድሪው ካቡራ ጋር በተመሳሳይ ኬኒያዊው ጊልበርት ሰለቧ በቀጥታ ሽፋኑ ሙያዊ ትንታኔዎች እየሰጠ ይገኛል። ‘ አትዮ -ኪክ ከዚህ ቀደም እንደምናደርገው ኬኒያዊው ጊልበርት ሰለቧ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር […]
“አላዋቂ የሆኑ ለኢትዮዽያ ቡና አንደም ሳንቲም የማይጥሉ መሀይም የሆኑ የፌስቡክ አርበኞች ቦርዱ ነው እንዲህ ያደረገው ይላሉ” መቶአለቃ ፈቃደ ማሞ
የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር እና የኢትዮጵያ ቡና የቦርድ ሊቀመንበር መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ትላንት ረፋድ የብስራት-ስፖርት እንግዳ ቆይታ አድርገው ነበር፡፡መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በቆይታቸው በርካታ ሊጉን የተመለከቱ አስተዳደራዊ ጥያቄዎች እና የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጥያቄዎች ከብስራት ኤፍ ኤም ስፖርት መንሱር አብዱልቃኒ ጥያቄ ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል። ከቆይታቸው መኸል የክለባቸው እና የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ጉዳይ በተመለከተ ከተነሱት ጥያቄዎች […]
#ታዳጊዎቹ የዓለም ዋንጫን ለማሳካት ከጫፍ ደርሰዋል!
የኢትዮጵያ ከ20ዓመት በታች የሴት ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ በ2022 የኮስታሪካው የአለም ዋንጫ ለማለፍ ብዙ ርቀቶችን ተጉዘው የታንዛንያና አቻውን በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ አምስተኛ ዙር ተሸጋግረዋል። FT #FIFA U20 Women’s World Cup Costa Rica 2022 Live Ethiopia 2 – 0 Tanzania ( Agg 2 – 1 )
የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎች!
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ የሚያደርገውን የስድስት ሳምንት ጨዋታዎች ቆይታ ካሳለፍነው አርብ መጀመሩ ይታወቃል ። ከዚሁ ቀን ጀምሮም ለተከታታይ አራት ቀናት የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው በነዚህ 8 ጨዋታዎች 30 የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርዶችን ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች የተመለከቱ ሲሆን ምንም አይነት የቀይ ካርድ አልታየም ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 […]
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወጣት አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋሮጦ የሰሜን አሜሪካውን ክለብ ተቀላቅሏል !
በስዊዘርላንድ ዋናው ሱፐር ሊግ ለኤፍ ሲ ሉጋኖ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር እና ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ያለፉትን የውድድር ወራቶች አድናቆት ያተረፈው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ማረን ሀይለስላሴ ቀጣዮን የፈረንጆቹ 2023 ወደ አሜሪካ በመጓዝ በአሜሪካ Major League Soccer (MLS) ለቺካጎ ፋየር ለመጫወት መስማማቱን ክለቡ በድህረ ገፁ ትላንት ይፋ አድርጓል። በፍጥነቱ እንዲሁም በተለየ የኳስ ጥበቡ የተለየ ችሎታ ያለው የ23 ዓመቱ […]
➖የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በካሜሩኑ ውጤት የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀ !
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሩን ያሳየውን የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ፌዴሬሽኑ “ባቀድነው ልክ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ውጤታማ ባለመሆናችን የኢትዮጵያ ህዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን” የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል ። አቶ ባህሩ ቀጥለው “ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ […]
“እዚህ ትልቅ መድረክ ላይ በመመረጤ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል”-አማኑኤል ዮሐንስ
የዋልያዎቹ የመሀል ሜዳው እስትንፋስ እና የመሀል ሜዳ ሞተሩ አማኑኤል ዮሐንስ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የጨዋታው ኮከብ በመባል ከካፍ ሽልማት ማግኘቱ ይታወሳል። አማኑኤል በካፍ ቴክኒካል ኮሚቴ በምድብ ጨዋታዎች ከምርጥ 11 ተጫዋቾች ውስጥ በኢትዮጵያ በኩል በዕጩነት የቀረበ ብቸኛ ተጫዋች እንደነበር ይታወሳል። የዋልያዎቹ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመሐል ሜዳ ተጫዋች አማኑኤል ዮሃንስ ዛሬ ካፍ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በአፍሪካ […]
“የነገው የመጀመርያ ጨዋታ ነው፣እነሱ ጠንካሮች ቢሆኑም እኛም የተሻለ ነገር ለማሳየት ዝግጁ ነን” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አልጣኝ ውበቱ አባተ እና አምበሉ ጌታነህ ከበደ ነገ ምሽት 4፡00 ላይ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ከምታደርገው ጨዋታ ቀደም ብሎ ዛሬ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሀሳባቸውን በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች አካፍለዋል። ወደ ካሜሩን ለመድረስ የመጀመርያው ቡድን እንደሆንን በመግለፅ መግለጫቸውን የጀመሩት አሰልጣኝ ውበቱ ከሶስት አፍሪካ ዋንጫዎች በኋላ ወደ መድረኩ በመመለስ ጥሩ ቡድን ይዘው ለመቅረብ እና […]
የኮቪድ ወረርሽኝ ዋልያዎቹ በሚገኙበት በምድብ 1 ሀገራት ላይ ጠንክሯል ! – ከዋልያዎቹ አራት ከካሜሩን አራት በኮቪድ ተይዘዋል !
የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀመር ዘጠኝ ቀናት ብቻ ሲቀረው የውድድሩ ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖች አስመልክቶ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች ከጨዋታው መጀመር በፊት ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። በተለይም ደግሞ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በተሳታፊ ሀገራት ላይ ሊደርስ የሚችለው የኮቪድ ጫና ሌላኛው ስጋት ሊሆን እንደሚችል እየተዘገበ ነው። ከውድድሩ መጀመር በፊት ባለፈው እሁድ ከሀያ አራቱ ተሳታፊ ሀገራት ቀዳሚው ሆኗል ያውንዴ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን […]