ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ሰለ ነገው ሸገር ደርቢ / 2015 ተጨማሪ መረጃዎች

  የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም * ትኬት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መሸጥ ይጀምራል። * የስታዲየም በሮች በተመሳሳይ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ። * የክቡር ትሪቡን በር በተዘጋጁ ልዩ ባጆች ብቻ የሚገባበት ሲሆን ጥላ ፎቅ 200 ብር ፣ ከማን አንሼ 100 […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

# ከዕድሜ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከ250 በላይ አትሌቶችን ማገዱን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ

  #ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ ፌዴሬሽኑ መጠየቅ ይኖርበታል! 👇   ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከዕድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ መሠረት ከውድድር ውጭ መሆናቸውን የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል።     […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

ለ45ኛ ጊዜ ሳንጃው ከ ቡንዬ የሚያደርጉት ስደተኛው ሸገር ደርቢ በቀዘቀዘ መልኩ ነገ ይካሄል !

ቀደም ባሉት አመታት ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በሚኖሩ ሳምንታቶች ብሎም ቀናቶች ጀምሮ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ደምቆ በጨዋታው ቀን ደግሞ ምሽት ለሚደረግ ጨዋታ ከሌሊት ጀምሮ ቦታ ለማግኘት ወረፋ የሚያዝለት እና የአዲስ አበባ ስታዲየም በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በተገኘው መድረክ ሲበዛ የሚደምቀው ሸገር ደርቢ ዘንድሮም በቀዘቀዘ መልኩ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ የፊታችን ቅዳሜ […]

አፍሪካ ዜናዎች

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጣይ ጊኒን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድኑ ከቻን ስህተቱ ለመማር በሚል የግምገማ መድረክ ዛሬ ተካሄዷል!

የኢትዮጵያ የቻን ብሔራዊ ቡድን በአልጄርያ አስተናጋጀነት በተከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ የልዑክ ቡድኑ አባላት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት ሐሙስ ጥር 25 በኢሊሊ ሆቴል ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ  የተባሉት ጉዳዮች የሚከተሉት ቢሆን ግምገማ  የተደረገው ሐሳብ   ከማውራት ባለፈ ለብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ  አሁን ላይ እረግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። […]

አፍሪካ ዜናዎች

#በነገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጎል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል። ሆኖም በአንጋፋው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በ 5፡00 ላይ የሚከናወን በመሆኑ የሰዓት መጣበብ እንዳይኖር በማሰብ ጋዜጣዊ መግለጫው […]

ዜናዎች

#እጅግ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ዜና ዕረፍት !

እጅግ ሲበዛ በጋዜጠኝነት ስፖርት ሳይታክትና ሳያርፍ እልፍ ዘመናትን ሲሰራ አሁንም በመስራት ላይ የነበረው ታሪክ አዋቂው ወንድማችን የጋዜኛ መሸሻ ወልዴ ትላንት ማምሻውን ህይወቱ ማለፉ ተዘግቧል። ኢትዮኪክ ለቤተሰቦቹ ለስራ ባልደረቦቹ እና ለሚያውቁት ሁሉ መፅናናትን እየተመኘን ፣የምናከብረው የወንድማችን የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ነፍስ ይማር እንላለን !

አፍሪካ ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የአልጄሪያ ቆይታቸው አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገትን አጭር ቆይታ እና ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ ይሰጣሉ።

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ፈረሰኞቹ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልምምድ ስፍራና ሆስቴል ግንባታ መሬት ባለቤትነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተረከቡ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም በወሰነው ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የልምምድና የተጫዋቾች ማረፊያ ሆስቴል ግንባታ ቦታ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፤ በመሆኑም ክለቡ አስፈላጊውን የሊዝ ውል በመፈፀም እና ለይዞታውም በ20/05/2012 ዓ.ም. ካርታ በማግኘት ጭምር ቦታውን ለማልማት የተለያዩ ጥረቶች ያደረገ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት ቆይቷል። በተለይም በይዞታው ላይ 3 የይገባኛል ክሶች ቀረበው ከሁለት ዓመታት […]

አትሌቲክስ

ኢትዮጵያዊው የ17 ዓመት ታዳጊ አሸንፏል !

በጀርመን -ካርልስሩሄ በተካሄደው የአለም የቤት ውስጥ የ3000ሜትር የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮዽያዊው አብዲሳ ፈይዛ የተባላው የ17አመት ታዳጊ የመጀመርያውን የቤት ውስጥ ውድድር በ7፡40.35 በቀዳሚነት አሸንፏል። መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን :- https://www.instagram.com/ethio_kick ድረ ገጻችንን :- https://ethio-kickoff.com

አፍሪካ ዜናዎች

የመጨረሻው የልዑካን ቡድን ዛሬ ሌሊት ይገባል

17 ተጫዋቾችን ጨምሮ 24 አባላትን በመያዝ ከአልጄርያ የተነሳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑክ በግብፅ ትራንዚት አድርጎ ከአራት ሰዓታት በረራ በኋላ ሌሊት አዲስ አበባ ገብቷል። በትናንትናው ዕለት 12 የብሔራዊ ቡድን አባላት ሀገር ቤት መድረሳቸው ይታወሳል። የመጨረሻው የልዑካን ቡድን ዛሬ ሌሊት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል     መረጃ በቴሌግራም :- https://t.me/Ethio_Kickoff በኢንስታግራም ገጻችንን :- https://www.instagram.com/ethio_kick ድረ ገጻችንን :- https://ethio-kickoff.com