ዜናዎች

#አሳዛኝ ዜና ዕረፍት

  የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ጅማ ላይ ተሳታፊው እንጅባራ ከተማ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጨዋች ተስፋፅዮን ፋንቱ (ደሮ) ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አምና በኢትዮ ኤሌክትሪክ በትልቅ ደረጃ መጫወት የቻለው አማካዮ በዘንድሮ የውድድር ዓመት እንጅባራ ከተማን በመቀላቀል በጨዋታ ላይ እያለ ባጋጠው የጭንቅላት ግጭት አደጋ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል። ተስፋፅዮን ፋንቱ ሥርዓተ ቀብር በነገው እለት […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

  ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ከ14ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን መካሄጃ ከተማና ስታዲየም በተመለከተ የስራ አመራር ቦርዱ ዛሬ ጥር 28/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በዚህም መሰረት ውድድሩን በድሬደዋ ወይም ባህር ዳር ከተማ ለማከናወን የፊታችን ሰኞ ጥር 29/2015 ዓ.ም ሜዳዎቹን የሚገመግም ኮሚቴ(ከቦርዱ እና ውድድርና ስነስርዓት […]

ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

#የዛሬው ጨዋታ ተሰርዟል

  በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ዛሬ ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ አስታውቋል።        

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ሰለ ነገው ሸገር ደርቢ / 2015 ተጨማሪ መረጃዎች

  የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም * ትኬት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መሸጥ ይጀምራል። * የስታዲየም በሮች በተመሳሳይ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ። * የክቡር ትሪቡን በር በተዘጋጁ ልዩ ባጆች ብቻ የሚገባበት ሲሆን ጥላ ፎቅ 200 ብር ፣ ከማን አንሼ 100 […]

አትሌቲክስ ዜናዎች

# ከዕድሜ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከ250 በላይ አትሌቶችን ማገዱን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ

  #ከመነሻው ይሄ ስህተት እንዲከሰት መንገዱን የከፈተው ራሱ ፌዴሬሽኑ መጠየቅ ይኖርበታል! 👇   ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከዕድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ መሠረት ከውድድር ውጭ መሆናቸውን የኢትዮዽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል።     […]

ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

ለ45ኛ ጊዜ ሳንጃው ከ ቡንዬ የሚያደርጉት ስደተኛው ሸገር ደርቢ በቀዘቀዘ መልኩ ነገ ይካሄል !

ቀደም ባሉት አመታት ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በሚኖሩ ሳምንታቶች ብሎም ቀናቶች ጀምሮ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ደምቆ በጨዋታው ቀን ደግሞ ምሽት ለሚደረግ ጨዋታ ከሌሊት ጀምሮ ቦታ ለማግኘት ወረፋ የሚያዝለት እና የአዲስ አበባ ስታዲየም በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በተገኘው መድረክ ሲበዛ የሚደምቀው ሸገር ደርቢ ዘንድሮም በቀዘቀዘ መልኩ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ የፊታችን ቅዳሜ […]

አፍሪካ ዜናዎች

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጣይ ጊኒን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድኑ ከቻን ስህተቱ ለመማር በሚል የግምገማ መድረክ ዛሬ ተካሄዷል!

የኢትዮጵያ የቻን ብሔራዊ ቡድን በአልጄርያ አስተናጋጀነት በተከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ የልዑክ ቡድኑ አባላት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት ሐሙስ ጥር 25 በኢሊሊ ሆቴል ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ  የተባሉት ጉዳዮች የሚከተሉት ቢሆን ግምገማ  የተደረገው ሐሳብ   ከማውራት ባለፈ ለብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ  አሁን ላይ እረግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። […]

አፍሪካ ዜናዎች

#በነገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰዓት ለውጥ ተደርጎል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገውን ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል። ሆኖም በአንጋፋው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በ 5፡00 ላይ የሚከናወን በመሆኑ የሰዓት መጣበብ እንዳይኖር በማሰብ ጋዜጣዊ መግለጫው […]

ዜናዎች

#እጅግ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ዜና ዕረፍት !

እጅግ ሲበዛ በጋዜጠኝነት ስፖርት ሳይታክትና ሳያርፍ እልፍ ዘመናትን ሲሰራ አሁንም በመስራት ላይ የነበረው ታሪክ አዋቂው ወንድማችን የጋዜኛ መሸሻ ወልዴ ትላንት ማምሻውን ህይወቱ ማለፉ ተዘግቧል። ኢትዮኪክ ለቤተሰቦቹ ለስራ ባልደረቦቹ እና ለሚያውቁት ሁሉ መፅናናትን እየተመኘን ፣የምናከብረው የወንድማችን የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ነፍስ ይማር እንላለን !

አፍሪካ ዜናዎች

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የአልጄሪያ ቆይታቸው አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ በአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ላይ ያደረገትን አጭር ቆይታ እና ተሳትፎ አስመልክቶ ሰኞ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የስብሰባ አዳራሽ መግለጫ ይሰጣሉ።