ዜናዎች

ድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የዘጠኝ ጨዋታ ዕግድ ተላልፎባቸዋል!

የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በፕሪሚየር ሊጉ ወድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ የዘጠኝ ጨዋታ ዕግድ ተላልፎባቸዋል።
አሰልጣኙ ዕግዱ ሊተላለፍባቸው የቻለው ድሬደዋ ከ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በነበረው ጨዋታ ላይ የ25ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በ44ኛ ደቂቃ ላይ የዕለቱ ዳኛ ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ አፀያፊ ስድብ ሰድቦኛል በሚል በቀይ ካርድ ከሜዳ  በመሰናበታቸዉ ነው።
የፕሪሚየር ሊጉ የዉድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ ባወጣዉ ሪፖርት አሰልጣኙ ዳኛዉን ሁለት ጊዜ አፀያፊ ስድብ በመሳደባቸዉ ሪፖርት የቀረበባቸዉ ሲሆን ዋና አሰልጣኙ ቀይ ካርድ ለተመለከቱበት በኢትዮጲያ ፕሪሚርሊግ ደንብ ክፍል1 አንቀፅ 13.3 በተቁ 18 መሠረት ሶስት ጨዋታ እንዲታገዱ እና ብር 10 ሺህ ብር እንዲከፍሉ እንዲሁም በአፀያፊ ስድብ ለተሳደቡበት ጥፋት በኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 ተራ ቁጥር 1 መሠረት 6 ጨዋታ እዲታገዱ እና ብር 5000 ሺህ እንዲከፍሉ በድምሩ 9 ጨዋታ እንዲታገዱ እና ተጨማሪ 15 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *