የ2016 የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ያሳለፍነው እሁድ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ውድድራቸውን በማጠናቀቅ አብዛኛዎች የሊጉ ቡድኖች ወደ መጡበት ከተማ እና ተጫዋቾች ሆነ አሰልጣኞች ወደ የቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ የሀምበርቾ ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም ይርጋ ጨፌ ቡና ያገለገሉበትን በውላቸው መሰረት ክፍያ ማግኘት እንዳልቻሉ እንዲሁም ችግረኛ ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ቀርቶ እየተረዱ እንደሚገኙ ተደጋጋሚ ጊዜ ትዕንግርት ስፖርት መዘገቡ ይታወሳል።
እንደ ትዕንግርት ስፖርት ዘገባ ነገሩ ብሶ ተባብሶ በአሁኑ ሰዓት የሀምበርቾ ቡድን ሰርቪስ በአዳማ ከተማ በበቀለ ገስት ሀውስ የሆቴል የአልጋ እና ኦሽን ምግብ ቤት ምግብ ክፍያ አለመፈፀማቸውን ተከትሎ በእዳ እንደተያዘ እና ተጫዋቾች ሀገራቸው መግቢያ ብር ስለሌላቸው እና ክፍያ ሳይፈፀምልን የትም አንሄድም ጎዳና ላይ አንወጣም ብለው ከያዙበት ሆቴል ቢቀመጡም በዛሬው ዕለት የምግብ እና የአልጋ ክፍያ ካልተፈፀመ ምንም አይነት ምግብ ማግኘት እንደማይችሉ ሆቴሉን ለቀው እንዲወጡ የበቀለ ገስት ሀውስ ሆቴሉ ባለቤቶች እንደነገሯቸው ማረጋገጥ ተችሏናል።
የሀምበርቾ ሴት ተጫዋቾች ” የህግ አካል የሆነ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በውላችን መሰረት ክለቡ እንዲከፍለን ሊያደርጉልን ስላልቻለ ሴት እህት እና እናት ያለው ይድረስልን” በማለት በማልቀስ እየተማፀኑ ይገኛሉ።
የህግ የበላይነት እንደዚህ ነው ?
ፌዴሬሽኑን እና ክለቡን አምኖ ውል የተዋዋሉት ተጫዋቾች ከዚህ በኋላ ለሚደርስባቸው ኢ-ፆታዊ ጥቃቶች ሀላፊነት ይወስዳሉ ?
የክለብ አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ይህ ነገር በእኛ ሴት ልጆች ቢሆንስ ብሎ ማሰብ እውነት አቅቷቸው ነው ?
መረጃው @Tengert Sport ትዕንግርት ስፖርት