ዜናዎች

⭕️የአዲስ ስታድየም እና የተመልካቹ ናፍቆት አሁንም ቀጥሏል .

 

👇

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ27ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት ያለው መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደማደርግ

የአክሲዮን ማህበሩ ትላንት አረጋግጧል. በተለይም

የሸገር ደርቢም ሰኔ 15 እየተጠበቀ ባለበት ሰአት የዘንድሮው አመት ውድድር በሐዋሳ ከተማ እንደሚጠናቀቅ ሊግ የሊግ ካምፓኒው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል.

 

⚽️

 

⛔️የአዲስ ስታድየም እና የተመልካቹ ናፍቆት አሁንም ቀጥሏል ….

 

✍️ ……ከ Dagim Tamiru ከማኅበራዊ ሜዲያ የተወሰደ ፁህፍ እናጋራችሁ…. .Comments ላይ ከአዲስ ስታድየም ጋር በተያያዘ ሃሳቦችን አጋሩን!

.

.

.

ከትምህርት ቤት መልስ ከላይ ሰደሪያና ሸሚዝ ኣውልቆ ጨዋታ ለመታደም ስታድየም እየሮጥን የሄድንባቸው ዘመን ብዙ ነው፤የክልል ጨዋታ ውጤት ለመስማት የስታድየም ድምፅ ማጉያ በፅናት የሰማንበት ወቅት አይረሳም ፤

 

አአ ስታድየም ትዝታው ብዙ ነው ነፍስ ካወኩ ጀምሩ የሊጉን መጀመር ከሚጠብቁት መካከል ነኝ ፤ ተረባና ጨዋታ እንደየቅል ነው፤እዛው ኣግኝተኸ የካምቦሎጆ ትዝታቸው ከኑሮኣቸው ጋር አገናኝተው የሚያወጉ ሥፍር ቁጥር የላቸው ……

ግብ ግብ ተፈጥሮ እግሬ ኣውጪኙም አይረሳም ፤ረጅም ጊዜ ተመልካች ከሆንክ ኳስ ኣቀባዩቹን( ቄራዎቹን )በስም ለይተህ እየጠራ “ኳስ ቶሎ ልቀቅ” አልያም ” ወሳንሳ ( ቃሬዛ) ይዛቹ ግቡ” ማለት የተለመደ ነው።

.

.

የቀድሞ ዘመን የካምቦሎጆ ኣድባሮች ብዙ ጊዜ ትሪቩን ኣታገኛቸው ድንገት ካታንጋ ላይ ቁጭ ብለህ ወደ ላይ ስታንጋጥ ሸሚዛቸውን ግንባራቸው ላይ ኣርገው ጨዋታ ሲታደሙ ትሾፋለህ ፤ካልፈራህ ምስል አብራቸው ትታደማለህ ፀሐዩ ከራራ ከሆነ ከማን አንሼ ላይ ነፍ የሀገሬ እግር ኳስ የሚናፍቅ ሰው ኣግኝተህ ጨዋታ በጨዋታ ሆነ ትወጣለህ

.

.

እና እነዚህ ነገሮች ከሳምንቡሳና ከቆሎ ጋር ለምደኸ ይኸ ኣራት አመት ተቆጠረ በከተማው ላይ ጨዋታ ለመታደም፤ የሀገሪቱ ዋና ከተማ ህዝብም የሀገሪቱን ሊግ ስታድየም ገብቶ ለመታደም ባይተዋር ሆነ

.

.

አአ ስንት የኣፍሪካ ፣የሴካፋ እንዲሁም የኣህጉሪቱን የኣትሌቲክስ ውድድሮች በብቃት ያስተናገደች ከተማ ዛሬ የሀገሬውን ትልቁን ሊግ ለማወዳደር ኣቅም የላትም ሲባል ብዙ ቁጭት እና ናፍቆት ያስነሳል

.

.

በከተማው በስፖርት እንቅስቃሴ ለሚሳተፉ በተለያየ ዘርፍ ላለ ትውልድ ፤ትልቅ የዘመኑ ን ስፖርተኛ በቅርበት ኣለመከታትል ብዙ ነገር ያስቀርበታል

.

.

.

ስፖርቱን በቅርበት ለሚከታተል ታዳሚ ትዝታውን እና ስሜቱ በማጥፋት ተመልካቹን ከካምቦሎጆ ማራቅ ይሆናል

ምስሎቹ ፦ በተለያየ ወቅት ያነሳናቸው