ዜናዎች

⭕ዮሴፍ ታረቀኝ ከዴንማርኩ ክለብ AC Horsens ጋር የሙከራ ጊዜውን በስኬት ቀጥሏል!

🕳 በቀጣይ ሳምንታት ኢትዮጵያ ሀገሩ ይመለሳል!

 

👇

የዴንማርክ ክለብ ለወራት በጥብቅ ሲከታተላቸው ከነበሩ አፍሪካውያን ታዳጊ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ዮሴፍ ታረቀኝ ለሙከራ ልምምድ እንዲሁም ለፊትነስ እና የህክምና ምርመራዎች በAC Horsens ጋባዥነት ወደ ዴንማርክ ማቅናቱ ይታወቃል።

 

የአዳማ ከተማው የጎል አዳኝ ዮሴፍ ወደስፍራው ካቀና በኃላ ከAC Horsens ክለብ ጋር ልምምዱን ቀጥሎ በሆርሰን ከተማ የሚገኙ የክለቡን የተለያዩ ፋሲሊቲዎችን ጎብኝቷል። ዮሴፍ ለቡድኑ በልምምድ ጨዋታዎች 4 ጎሎችን ከመረብ ማስቆጠሩን የኢትዮኪክ ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል ።

እንደ ምንጮቻችን መረጃ ዮሴፍ በዴንማርኩ ክለብ AC Horsens የሦስት ሳምንት የሙከራ ቆይታውን በስኬት መቀጠሉ ሲታወቅ በቀጣይ ሳምንታት  ወደ ኢትዮዽያ የሚመለስ ይሆናል።
AC Horsens በአውሮፓ ከሚገኙ ወጣቶች ላይ መሰረት አድርጎ ለመስራት ጥረት እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል ሲሆን በቅርቡ የአሜሪካ ባለሃብቶች ባለቤት አድርገውቷል። ክለቡ በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ እህት ክለቦች አሉት።

ዮሴፍ ከዴንማርኩ ክለብ AC Horsens ጋር በተያያዘ መረጃዎችን በቀጣይ  ለእናንተ የምናደርስ ይሆናል።