ዜናዎች

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር በይፋ ተለያዩ !

👇
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ በይፋ መለያየታቸውን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በ2013 የተሾሙት አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል በአራት ዓመታት ቆይታቸው ቡድናችን በ2022 እና 2024 የዓለም ዋንጫ ማጣርያዎች እስከ መጨረሻው ዙር እንዲደርስ አስችለዋል፡፡
በ2022 በዩጋንዳ የተሰናዳው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ውድድር አሸናፊ እንዲሆን አስችለዋል።
ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ በተጨማሪ ከግንቦት 2014 ጀምሮ የዋናው ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) አሰልጣኝ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በቆይታቸውም የሴካፋ ሴቶች ዋንጫን በ3ኛ ደረጃ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ፍሬው በቆይታቸው ላበረከቱት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ የእግር ኳስ የሥራ ዘመናቸው መልካሙን ሁሉ መመኘቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል