ዜናዎች

⭕የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥር 20 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 18 ጎሎች በ16 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 41 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል ።
በሳምንቱ አራት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። አለልኝ አዘነ(ባህር ዳር ከተማ) እና ፍሬዘር ካሳ(ባህር ዳር ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ፤ በኃይሉ ግርማ(መቻል) የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች በመራገጥ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል እንዲሁም በረከት ወልደዮሀንስ /ሀዲያ ሆሳዕና-ተጫዋች/ ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር በነበረው የ12ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የእለቱን ዳኞች አጸያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበት በፈጸመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በሁለት ክለቦች ላይም የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፏል። ሀምበሪቾ እና ባህርዳር ከተማ በሳምንቱ የየክለቦቻቸው አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።