የዋልያዎቹ አምበል እና የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሽመልስ በቀለ ከአስራ አምስት አመታት የብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን አሳውቋል።
” ጊዜው አሁን እንደሆነ ይሰማኛል ፣ ብሔራዊ ቡድኑን የምሰናበትበት ወቅት የምወደውን እና የምጓጓለትን አረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ወክዬ የምጫወትበት ጊዜ
እንዳበቃ ይሰማኛል ” ሲልም በመልዕክቱ አጋርቷል።
ሀገራችንን ለሁለት አፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ በማድረግ ደማቅ ታሪክ እና ትልቅ አሻራን ማሳረፍ የቻለው ሽመልስ በቀለ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ 83ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።
” በቀጣይም ከሀገሬ እና ብሔራዊ ቡድኑ ጎን በመሆን በስሜት እና በኩራት ዋልያዎቹን የማበረታታ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ።
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻዋ ቀን በእኔ እምነቱ ኖሯችሁ ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ” ሲልም ሽመልስ በቀለ በስንብት መልዕክቱ አጋርቷል።
ሽመልስ በቀለ አስራ አምስት አመታት ለኢትዮጵያ፣ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎትን ሲሰጥ የተመለከተው አንድ የቢጫ ካርድ ብቻ ነው።
8⃣3⃣ – የጨዋታ ብዛት
1⃣6⃣ – ጎሎች
1⃣3⃣ – ለጎል የሚሆኑ ኳሶች
1⃣ – ቢጫ ካርድ
0⃣ – ቀይ ካርድ
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
tiktok.com/@ethiokick
#በቴሌግራም :-
https://t.me/Ethio_Kickoff
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_ki
🔛ድረ ገጻችንን :-