ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#የተራዘመው የደርቢ ጨዋታ የሚደረግበት ቀን፣ ሰዓት እና ስታዲየም መረጃ !

ቅዳሜ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል።
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረገ ውይይት የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7ተኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ቅዳሜ ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ከተማ – አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ