አፍሪካ ዜናዎች

#አቡበከር ናስር በቋሚነት – ተሰልፎ ቡድኑም ድል ቀንቶታል !

የደቡብ አፍሪካው ማሚሎዲ ሰንዳዉስ የፊት መስመር አጥቂ ኢትዮጵያዊ ው አቡበከር ናስር ምሽቱን ቡድኑ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጋጣሚውን ኬፕታውን ስፐርስ 3 ለ 0 ባሸነፈበት ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃዎች ተሰልፎ ተጫውቷል።

አቡበከር ከወራቶች ጉዳት እና ማገገም በኃላ ባለፉት ቀናቶች ወደ ሜዳ በመመለስ የመጀመሪያ ጨዋታውን በመጨረሻዎቹ ለ 2 ደቂቃዎች ፣ ሁለተኛውን ጨዋታውን ለ26 ደቂቃዎች ተቀይሮ በመግባት መጫወቱ ይታወሳል።

በዛሬው ጨዋታ ደግሞ አቡበከር በመጀመሪያ ቋሚ 11 ተሰላፊዎች ውስጥ ለ 45 ደቂቃዎች በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ እና ለጎል የቀረቡ አጋጣሚዎች አድርጓል።

ክለቡ የአምናው ሻምፒዮን ማሚሎዲ ሰንዳዉስም በሜዳው በመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ኬፕታውን ስፐርስ በ 3 ለ0 ድል አሸንፎ ለዳግም ድል የፕሪምየር መሪነቱን አጠናክሯል።

 

 

ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)

#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን

tiktok.com/@ethiokick

#በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

#በኢንስታግራም ገጻችንን :-

https://www.instagram.com/ethio_ki

🔛ድረ ገጻችንን :-

Home page