አፍሪካ ዜናዎች

#የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የጋና ቆይታቸውን በምስጋና አጠናቀዋል!

👇
በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት በተደጋጋሚ የካፍ የአሰልጣኞች የፍቃድ ማሻሻያ፣የማጠናከሪያ ስልጠናዎች በመስጠትና የስልጠናዎቹ ሂደት በመቆጣጠር በካፍ የሚታወቁት ኢትዮጵያዊው ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በጋና የአምስት ቀናት ቆይታቸውን በምስጋና አጠናቀዋል።
ከጋና እግርኳስ ፌዴሬሽን በተገኘ መረጃ መሠረት ከስደስት ዓመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ ባለው እና ለሦስት ወራት የሚቆየውን የአሰልጣኞች የ B ላይሰንስ የመጀመሪያው የ10 ቀናት ስልጠና ተጠናቋል።
በዚህ መሠረት የካፍ ቢ ላይሰንስ ስልጠና ከመጠናቀቁ በፊት በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ መገኘታቸውን መረጃው ገልጿል።
እንደ መረጃው ከሆነ የስልጠናው ሂደት ምን እንደሚመስል ለማየት እና ስልጠናው በተገቢው መልኩ መካሄዱን ለአምስት ቀናት ለማረጋጥ በስፍራው የተገኙት።
ኢንስትራክተር አብርሃም በተሳካ መልኩ ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁ ከኮርሱ ተካፋዮች እና ስልጠናውን ሲሰጡ ከነበሩ ኢንስትራክተሮች ፊርማቸውን ያኖሩበት ኳስና የጋና ብሔራዊ ቡድን መለያን በስጦታ መልክ ለኢንስትራክተር አብረሃም መብራቱ አበርክተዋል።
በዚህ ስልጠና ላይ 25 አሰልጣኞች የተካፈሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል የቀድሞ የጋና ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በፉልሃም ዌስትሃም ጨምሮ በእስራኤል ሊግ እና በተለያዩ ክለቦች የተጫወተው ተከላካዮ ጆን ፔይንትሲል ፣ የቀድሞ አሳንቴ ኮቶኮ እና ቲፒ ማዜምቤ አማካኝ ዳንኤል ናይ አድጄ የካፍ ፍቃድ ቢ የኮርሱ አካል ናቸው። በተጨማሪም ከተሳተፉት 25 ቱ መካከል ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ የቀድሞ የጋና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች አኒታ አንዷ ናት።