ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች በዋልያዎቹ ለመካተት ጥያቄዎችን ማቅረብ ቀጥለዋል

በእስራኤል ፕሪሚየር ሊግ ከተሳካለቸው ተጨዋቾች ተርታ የሚመደበው እና በጎንደር ቋራ የተወለደው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ሳልልህ ከእስራኤል ይልቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆንኑ ለኢትዮ-ኪክ በተደጋገሚ ገልጿል። ተጨዋቹ በቀጣይ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን የመካተት ፍላጎቱን በከፍተኛ ተስፋ አስምሮበታል።አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሶስት ወር በኃላ ከማዳጋስጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የአገር ውስጥ ሊግ ቀጣይ ከተማ በሚካሄድት ጅማ የብሔራዊ ቡድኑን ቅድመ ዝግጅት እዛው ሊጉ በሚካሄድበት ከተማ ለማድረግ ወስነዋል። አሰልጣኙ በቀጣይ ሳምንት መጀመሪያ ተጨዋቶቻቸውን ይፋ እንደሚያደሩጉ ቢታወቅም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች በተመለከተ አሰልጣኙም ሆነ በፌዴሬሽኑ በኩል ምንም የታሰበ ወይም የተጀመረ ቅድም ዝግጅት የለም።