ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ የጨዋታ ሪፖርት

የሁለተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

👇
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 5 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ስድስቱ በመሸናነፍ ሁለቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ 14 ጎሎች ተመዝግበዋል። 28 ቢጫ ካርድ እና አንድ ቀይ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ተሰጥቷል።
በተጫዋቾች ሙሉቀን አዲሱ(ሲዳማ ቡና) ቅዳሜ ጥቅምት 3 2016 ዓ.ም. ክለቡ ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር ባደረገው የ2ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።