ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

የፌዴሬሽኑ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እንዲሆን ወስነዋል!

◼🔘ፌዴሬሽኑ ለኢትዮ- መድህን ደብዳቤ አስገብቷል!
👇
የአለም ዋንጫ ማጣሪያ እና ሌሎች ጨዋታዎች የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁንም አሰልጣኝ የለውም ። አብዛኞቹ የአፍሪካና የምስራቅ አፍሪካ አገራት በቀጣዩ ወር ላይ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ እና ጠንክረው ለመታየት ስብስባቸውን ሲያሳውቁ ኢትዮጵያ እንኳን ስብስቧን አሰልጣኟን ማሳወቅ አቅቷታል ።
በአንፃሩ ኢትዮኪክ ባገኘችው መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ መሆኑ ተረጋግጧል። ፌዴሬሽኑ የቀረው ነገር ቢኖር ይፋ ማድረግ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት ቀጣዩ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ እንዲሆን ወስነዋል። አሰልጣኝ ገብረመድህን የኢትዮመድህን ጋር ኮንትራቱ ስላለው የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ለኢትዮ መድህን ደብዳቤ አስገብቷል። ደብዳቤው ለሀገራዊ ጉዳይ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ስለምንፈልገው ትብብር ስለመጠየቅ የሚል ነው።
እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለብሔራዊ ቡድኑ ሲመረጥ የሰበታ ከተማ እያለ ኮንትራቱ አላለቀም ነበረ ። በወቅቱ ፌዴሬሽኑ በፃፈው ደብዳቤ ውበቱ አባተ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ መምጣት ችሏል። ያንኑ መንገድ አሁንም ፌዴሬሽኑ ለመድን ክለብ በመፃፍ ተግባራዊ አድርገውታል። ከዚህ በተጨማሪም አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በጉዳዩ ዙሪያ ከክለቡ ኃላፊዎች ጋር እንዳወራ እና መግባባት ላይ ሳይደርሱም እንዳልቀሩ የኢትዮ ኪክ ምንጮች ጠቁመዋል
በዚህ መሠረት አሰልጣኝ ገብረመድህን በዚህ ሳምንት የዋልያዎቹ አሰልጣኝ መሆኑ በይፋ ፌዴሬሽኑ ያሳውቃል ማለት ነው።
እንደዛም ሆኖ ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ጉዳይ እና መሠል ጉዳዮች ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንቀላፍቶ ይገኛል።
ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-