አትሌቲክስ

ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሊና ሜየር በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ በመሆን አዲስ አበባ ትገባለች!

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህዳር ዘጠኝ በሚከናወነው 23ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10ኪሜ ኢንተርናሽናል ውድድር የ1992ቱ ባርሴሎና ኦሊምፒክ የ10,000ሜ የብር ሜዳሊያ አሸናፊዋ ኤሊና ሜየር በክብር እንግድነት እንደምትገኝ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት በተለይም በውድድሩ የመጨረሻ ዙሮች ከኢትዮጵያዊቷ የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ ጋር ባደረገችው ጠንካራ ፉክክር እና ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ ከደራርቱ ጋር ደስታቸውን በህብረት በገለጹበት አይረሴ ክስተት ትታወሳለች።
◼🔘
👇