Three jornalist sue EFF
ዜናዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሦስቱ ጋዜጠኞ የክስ ፍጥጫ ቀጥሏል !

➖ ጋዜጠኞቹ ለሚደርስባቸው የሞራል ብክነት ፌዴሬሽኑ  5ሚሊዮን ብር ያሲዝ በማለት ጥያቄ አቅርበዋል!

👇

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከሳምንታት በፊት በናሁ ቲቪና በትርታ ስፖርት ጋዜጠኞቹ የተዛባ እና እውነታነት  የጎደላቸው  ዘገባዎች ተላልፈውብኛል ሲል በጋዜጠኞቹ ላይ ክስ ማቅረቡ ይታወቃል።

የክሱ መዝገቡ እንደሚያሳየው  የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን በየግል በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ደግሞ እንደ ተቋም ከሳሽ ሲሆኑ ተከሳሾቹ ደግሞ አንደኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው፣  ሁለተኛ  ጋዜጠኛ ሶፎንያስ እንየው፣ ሶስተኛ ጋዜጠኛ አሸናፊ ዘለሌ፣ አራተኛ አሰልጣኝ ገዛኧኝ ታደሰ፣ አምስተኛ ናሁ ቲቪ እንዲሁም ስድስተኛው ትርታ ሬዲዮ 97.6 መሆናቸው ተጠቁሟል።

በክሱ ዙሪያ  ከተከሳሾቹ አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ግርማቸው  እንየው በጉዳዩ ላይ ከቀናት በፊት  በፋና ስፖርት ዞን  ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት ገብቶ ፌዴሬሽኑ ክስ መመስረቱንና  ስማቸን ጠፍቷል ቢሉም በየትኛው ዘገባ ስማቸው እንደጠፋ ብሎም ማንንም የመጉዳት አላማ እንደሌላቸውና ነገር ግን ያሉ ችግሮች እንዲወገዱ መስራታቸውን ገልጾ የፌዴሬሽኑ ህንጻ ባለቤትነት ወደ ፌዴሬሽኑ አለመዞሩንና የፌዴሬሽኑ መኪና ጠፍቶ አሁን ድረስ ምንም እንዳልተደረጉ  በወቅቱ  ፕሮግራም  አስረድቷል።

በአንፃሩ ባለፈው  ዓርብ  በፌዴራል የመጀመሪያ  ደረጃ  ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ፍትሃ ብሄር ተረኛ ችሎት ላይ ጋዜጠኛው ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን የለውም መጀመሪያ ብሮድካስት ሳይሄዱ በቀጥታ መክሰሳቸው ተቀባይነት የለውም፣ የፌዴሬሽኑ መኪና ጠፍቶ አሁን ድረስ ምንም አልተደረገም ፣ የፌዴሬሽኑ ህንጻ  ስም አልዞረም፣ ጠበቃው በፌዴሬሽኑ ኮሚሽነርና የተጨዋች ኤጀንት ሆነው  መስራታቸው ተገቢ ባለመሆኑ ለፊፋና ካፍ አሳውቀናል በሚል የሰጠው አስተያየት የወንጀል ህጉን የሚጻረር የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ስልጣን የሚጋፋ ሃሳቦች ለአድማጭ በማስተላለፍ  የችሎቱ አካሄድ እንዲዛባና ማህበረሰቡ የተሳሳተ ጭብጥ እንዲይዙ አድርጓል በመሆኑም የችሎቱን አሰራርና ስራ እንዲሁም ብይንና ፍርድ ከወዲሁ በመገናኛ ብዙሃን በማቅረብ ችሎቱን የደፈረ በመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር አንቀጽ  449/2 መሠረት አስተማሪ ቅጣት እንዲተላለፍ እናመለክታለን” ፌዴሬሽኑ ብሏል

ትላንት ደግሞ  በፌዴራል የመጀመሪያ  ደረጃ  ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ፍትሃ ብሄር ተረኛ ችሎት ላይ የተከሳሹ ጠበቃ የሰጠውን ምላሽ ተከትሎ  ችሎቱ  የከሳሽና ተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን  ምላሽ በማየት ብይን ለመስጠትና በሌሎቹ ክሶች ዙሪያ  ወደ መደበኛ ችሎት ክርክር ለመግባት ለጥቅምት 2/2016 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ቀጠሮ  አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ደግሞ  የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ክስ ያቀረበባቸው ሶስቱ ጋዜጠኞች (አንደኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው፣  ሁለተኛ  ጋዜጠኛ ሶፎንያስ እንየው፣ ሶስተኛ ጋዜጠኛ አሸናፊ ዘለሌ) እና  ትርት ኤፍ ኤም ለሚደርስባቸው የጊዜ የስም እና የሞራል ብክነት በምትካቸው  አምስት ሚሊዮን ብር ፌዴሬሽኑ ያሲዝ በማለት ጥያቄ ማቅረባቸውን  ዛሬ ረፋድ ስፖርት ዞን የራዲዮ ፕሮግራም አረጋግጧል።
በጉዳዩ ዙሪያ የስፖርት ዞን   የዩቲብ ቻናልን ሰብስክራብ በማድረግ  የቀጥታ ቃለመጠይቆችና  በዚሁ ጉዳይ ዙሪይ በቀጣይ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ (/https://www.youtube.com/watch?v=DKxyocQR79s )