ዜናዎች

” ስምምነታችን ከቃል ያለፈ የውል ስምምነት  ሳይሆን በጋራ አብሮ ለመስራት ነው”-የፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክላውድአውት  ከተባለ ኩባንያ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ማድረጉን  ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል።

በስምምነቱ ላይ የክላውድአውት ኩባንያ ስፖርት ማርኬቲንግ  እና የአለም አቀፍ ግንኙነቶች ተወካይ  አቶ ዮሐንስ ዘውዱ ( Johnny Vegas)  እና የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን  ስምምነቱን አስመልክቶ  ጋዜጣዊ መግለጫ በጋራ  ሰጥተዋል።

# ከመግጫው በኃላ  የተነሱ ጥያቄዎች   እና የተሰጡ ምላሾች በጥቂቱ……

🖋የሁለቱ ተቋማት ስምምነት  እስከ ምን ያህል ጊዜ ነው ?

🖋የጉዞ ወኪል እንደመሆኑ መጠን ከፌዴሬሽኑ ጋር ሊሰራ ያሰበው ነገር አለ?
🖋 ይህ ኩባኒያ ከዚህ በፊት ከሌሎች ፌዴሬሽኖች ጋር  የሰራው ሥራ ምን ነበረ?

🖋 ከክላውድአውት ከፌዴሬሽኑ ጋር በመስራቱ ምን ይጠበቃል?
🖋 ፌዴሬሽኑ ከኩባኒው ጋር በግልጽ ያስቀመጠው ስምምነት ቢብራራ?
🖋 በወጣቶች ላይ  በምን መልኩ ነው የምትሰሩት ?

🖋 ከሜዳ ግንባታ  ከብራንድ እና  ከሌሎች የልማት ስራዎች ጋር ድርጅቱ የመስራት ስምምነት እስከምን ድረስ ነው? 

የአቶ ዮሐንስ ዘውዱ ለጥያቄዎቹን በምላሽ ሲገልፁ :- 

የ “Kloudout” ኩባንያ ማርኬቲንግ  እና የአለም አቀፍ ግንኙነቶች ተወካይ አቶ ዮሐንስ ዘውዱ

                ————————————–

“ክላውአውት ሌከሸሪ ካምፓኒ ነው ። ስለዚህ እኔ    International Liaison ሆኜ  ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ  የምሰራው።  ክለውድአውት ደግሞ እዛ ውስጥ የሚገባ ነው። የእኔ ስራ ግንኙነቶችን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በኢንተርናሽናል ሊጎች መካከል መፍጠር ነው።  ለምሳሌ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ላሊጋ  ወይም MLS ሊጎች  ጋር ለማገናኘት   እና በዛ ውስጥ fiendlymatch ፣ አሰልጣኞች የሚሰለጥኑበት እና  ወጣቶች የሚሰለጥኑበት ሂደት ለመፍጠር ነው።  በተጨማሪም  ክላውድአውት የሚሰራው  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዞ በሚኖሩበት ጊዜ  በሆቴል የሚኖርብን ወጪዎች  እንዲቀንስ ከሆቴሎች ጋር መነጋገር በዛ ዙሪያ በቀላሉ አማራጮችን በመጠቀም ተጠቃሚ ማድረግ   ነው “

የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ስለ  አቶ ዮሐንስ ዘውዱን ሲናገሩ……

   የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን

              ————————————–

“አቶ ዮሐንስ ዘውዱ  ከዛሬ ጀምሮ  International Liaison መሆኑን ማሳወቅ ነው። ይኸ ማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የማይደርስባቸው አድማሶች አሉ። ሁሉም ቦታ እንደርሳለን ማለት አይደለም። በተጨማሪም ሁሉንም እናቃለን expert ነን ማለትም አይደለም። ስለዚህም  አቶ ዮሐንስ  በክላውድአውት የራሱ  ግንኙነቶች አሉት ። እነዚህ ካምፓኒዎችን በቀላሉ ማግኘት እጅግ ከባድ መሆኑ ይታወቃል። እናም እሱ  በቀላሉ  ግንኙነት ያደርጋል ።አቶ ዮሐንስ ዘውዱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው።  ለሀገሩ የሆነ ነገር ማድረግ ይፈልጋል። አሁን ያለበት የኑሮ ሁኔታ ከእኛ ምንም የሚፈልግ ሳይሆን ለሀገሩ  የሆነ ነገር ማድረግ ያስባል ። ጊዜውን የሚያሳልፈው በአብዛኛው ከዓለማችን Super Stars ከሆኑ ተጨዋቾች ጋር መሆኑ ይታወቃል።  እነዚህ  Superstars  እንዴት ስኬት እንደመጡ  ያውቃል ።  ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ Superstars ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። መንገዱ እንጂ የጠፋው ።  እናም እኛ  ከእሱ ግንኙነታችን ከባለፈው አመት December ጀምሮ ነበረ የጀመርነው።  ከዛም የተለያዩ በTeams  አማካኝነት communication  ስናደርግ ቆይተን ዛሬ ላይ ደርሰናል። ” ብለዋል

🖋  የፌደሬሽኑ ጥቅሞችን አቶ ባህሩ ሲቀጥሉ….

“- ብሔራዊ ቡድኑ የተለየ exposure ማግኘት የሚችልበት በሌሎች ሀገሮች  በቀላሉ Campaign ቢፈልግ  የሆነ ሀገር ላይ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል
– ወጪዎች 0 cost የሚሆንበት ወይም ወጪን ቅናሽ በሆነ ወጪ ማመቻቸት
– በወጣቶች ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ጋር  መስራት ። የክላውድአውት  በተለያዩ ሀገሮች ቅርንጫፎች አሉት አንዱ ዱባይ ነው። በዛም በእግር ኳሱም ያንን ግንኙነት  ለመፍጠር።  ሲሆን እኛ ይሄን እድል ማጣት አልፈለግንም። ለምሳሌ የአልናስር ክለብ CEO ወይም የሮማ  የቀድሞ CEO. አዲስ አበባ ነበሩ ። የመጡትም በዮሐንስ ጋባዥነት ነው።  የአልናስር ክለብ CEO ሆነው ከመሾማቸው አንድ ቀን በፊት ነው  ወደ ሳውዲ  መሄድ ሲገባቸው ወደ እዚህ የመጡት ። ያ ደግሞ የሆነው እኛ በፈጠርነው ሳይሆን ጆን በፈጠረው ግንኙነት ነው”
ምናልባት አሁን ላይ ስንገልፀው እውን ይሆናል አልያም የሚል ጥርጣሬ ሊፈጥር ይችላል ። አቶ ዮሐንስ
የአላማችን  ሱፕርስታር የሆኑ ተጨዋቾችን ፍራንሲስኮ ቶቲ፣ ባካሪ ሳኛ  እና እነ ሳካን ጨምሮ በቀላሉ የሚያገኝ ሰው ነው።ካምፓኒውም በዛ ደረጃ የሚሰራ ነው።  እነዚህ ተጨዋቾች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ልምዶቻቸውን የሚያካፍሉበት መድረክ እንደሚሆን እናምናለን። ብዙ አይተን  እኛም ልባችንን የከፈትንለት ነው ውጤታማ  ስራ ይሰራል ብለን የምንጠብቀው ነው። ። በቢሮክራሲ የታጠረ እንዳይሆን ጥረት እናደርጋለን። ምንያክቱም እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ  ማበራታታ ነው ከእኛ የሚጠበቀው። እኛ በጣም ደስተኞች ነን አብረን በመስራታችን።   “

አቶ ባህሩ ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ   እስከ ምን ያህል ጊዜ ነው ? ለሚለው ሲገልፁ…

Undefined  ወይም” ስምምነታችን ከቃል ያለፈ የውል ስምምነት  ሳይሆን በጋራ አብሮ ለመስራት ነው ። ስለዚህ እዚህ ቦታ ይቆማል የሚል ስምምነት የለውም።  አብረን በጋራ እየሰራን ውጤታማ እንሆናለን ብዬ ነው የማስበው”
” ብለዋል

የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን  እንዴት ግኑኙነቱ እንደተፈጠረ  ሲቀጥሉ…

” ይህንን ግኑኙነት ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒን  ነው የፈጠረው የግንኙነት መስመር ዕውቅና በመስጠት  በጋራ በመሥራታችን እጅግ በጣም ዕድለኞች ነን።” በማለት ገልፀዋል

አቶ ዮሐንስ  ከፌዴሬሽኑ ጋር ያላቸውን ዓላማቸውን  በዚህ መልኩ ገልፀዋል….

“እግርኳስ ከጨዋታነቱ በዘለለ  በርካታ ፋይዳ አለው ።  የእኔ ዓላማቻን ታዋቂ የተጫዋቾችን  እና ብራንዶችን  እዚህ በማምጣት ታዳጊዎችን  እነሱን አይተው እንዲነሳሱ አመቻችቶ ለማሳደግ ነው። በተጨማሪም አሰልጣኞች እና ዳኞች እንዲሰለጥኑ  ግንኙነቶችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መፍጠር ነው። እኔ ከፌዴሬሽኖች ፣ ከሊጎች እና ከብራንዶች  ግኑኝነት  የመፍጠር ስራ ነው የእኔ ዓላማዬ “

ከጣሊያን እግር ኳስ ጋር አለ ስላሉት ቀጣይ ግኑኝነት አቶ ዮሐንስ ሲናገሩ  …..

” ከጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር እየሰራን ነው። ይኸው አሰልጣኞችን የማሰልጠን  እና ልምድ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ነው።  ምናልባት ደግሞ  ወደፊት የወዳጅነት ጨዋታ ከወጣቶች ጋር እንዲሁም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማድረግ ሥራ ነው  ይኖራል። ይህን በቅርቡ እናሳውቃለን ” ብለዋል።

የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ከሜዳ ግንባታ እና ከሌሎች የልማት ስራዎች ጋር በተገናኘ ለተጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። 

                  አቶ ዮሐንስ ዘውዱ