ዜናዎች

#የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አትላንታ አይጓዝም- ጨዋታም ተሰርዟል !

 

 

በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትላንት  ከጉያና ብሔራዊ ቡድንጋር የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ በሽመልስ በቀለ ሁለት ጎሎች ማሸነፉ ይታወሳል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከነገ በስቲያ ኦገስት 5 (ሐምሌ 29) ከአትላንታ ሮቨርስ ክለብ ጋር ሊያደርገው የነበረው ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ መሠረዙ ታውቋል። በዚህም ምክንያት እዛው ካለ ከለብ ካለ  ላውንደን  ዮናይትድ  ከተባለ የሶስተኛ ዲቪዚዮን ክለብ ጋር ቅዳሜ የሚጫወት ዬሆናል። ዋልያዎቹ  ከአትላንታ ሮቨርስ ከአራተኛ ዲቪዚዮን ጋር ሊጫወት የነበረ ቢሆንም አሁን ከሦስተኛ ዲቪዚዮን ጋር መሆኑ የተሻለ አጋጣሚ ይሆናል።  የቅዳሜው የወዳጅነት ጨዋታ   በነፃ የሚሆን ይሆናል። በትላንትናው ጨዋታ 2600  የሚጠጋ ተመልካች ትኬት ተሸጧል ።