ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 26ኛ ሳምንትና የዲሲፕሊን ውሳኔዎች!

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 26ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ሁለቱ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 15 ጎሎች በ14 ተጫዎቾች ተቆጥረዋል።የጎሎቹ አገባብም 13 በጨዋታ ሁለት በፍፁም ቅጣት ምት ነው። በሳምንቱ 33 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋቾችና አንድ የቡድን አመራር ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 22 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋችና ቡድን አመራሮች ደረጃ በተላለፉ ውሳኔዎች 2 ተጫዋቾችና አንድ አሰልጣኝ ላይ ቅጣት ተላልፏል። መሀመድ ሙንታሪ(ሃዋሳ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ፥ ዳግም ንጉሴ(ሀዲያ ሆሳዕና) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከቱ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል፥ አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ(ኢትዮጵያ ቡና) በ26ኛ ሳምንት ጨዋታ
የጨዋታ ጊዜ ሆን ብሎ በማባከን ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን የቡድን አመራሩ
ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ
ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

በክለቦች ደረጃ በታዩ ሪፖርቶችም ወልቂጤ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለባቸው ከአምስት በላይ ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡