ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛው ሳምንትን የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ :-

 

 

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 16ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። በሳምንቱ 48 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሁለት ተጫዋቾች እና አንድ የቡድን አመራር ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።

 

 

 

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ መጋቢት 01 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ እና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ደንብ መሰረተ በተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ላይ በተላለፉ ውሳኔዎች – ሱራፌል ዳኛቸው(ፋሲል ከነማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል፣ ዘላለም ማቲዮስ(ወላይታ ድቻ) የክለቡ የቡድን መሪ ሲሆን የዳኛን ውሳኔ በመቃወም ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ አንድ ጨዋታ እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 6000 /ስድስት ሺ/ እንዲከፍል፣ አብነት ደምሴ(ኢትዮ ኤሌትሪክ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ የተመለከተ አንድ ጨዋታ እንዲታገድ በቃሉ ገነነ(ሃዋሳ ከተማ) በክለቡ አምስት የተለያዩ ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ በመመልከቱ አንድ ጨዋታ
እንዲታገድና የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦች ላይም በተመሳሳይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመሪያ እና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ደንብ መሰረት በተላለፉ ውሳኔዎች ኢትዮ ኤሌትሪክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሃዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የክለቦቻቸው አምስትና ከዛ በላይ ተጫዋቾች የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከታቸው የገንዘብ ቅጣት
ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ሲወሰን ሲዳማ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በአረንጓዴ ቲሴራ/መታወቂያ/ የተመዘገቡትን አራት /4/ ተጫዋቾች) ቀይሮ ስለማስገባቱ ከዳኞች ሪፖርት ተረጋግጦ በክለቡ ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈውበታል ።
በመሆኑም ሲዳማ ቡና ለፈፀመው ጥፋት በፕሪምየር ሊጉ የውድድር ደንብ መሰረት ምንም እንኳ ጨዋታው በድሬደዋ 2 ለ 0 አሸናፊነት ቢጠናቀቅም የዕለቱ ውጤት ተሰርዞ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆን ለክለቡ ዜሮ/0/ ነጥብና ሶስት/3/ የግብ ዕዳ እንዲሁም ለተጋጣሚው ድሬዳዋ ከተማ ሶስት/3/ ነጥብና ሶስት/3/ ተጨማሪ ግብ እንዲመዘገብ ፣ በዕለቱ የተመዘገቡት ጎል አግቢዎች እንዲሰረዙ ፣ በዕለቱ የተመዘገቡት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች እንዲፀኑና የቡድን መሪው አቶ ቾምቤ ገብረ ህይወት ለ6ወር እንዲታገዱና ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 25000 /ሃያ አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡