አፍሪካ ዜናዎች

#የካፍ ሻምፕዮንስ ሊግ ጨዋታን ኢትዮዽያን ዳኞች ይመሩታል !

 

 

የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የፊታችን ማክሰኞ የታንዛንያው  ሲምባ ከ ዩጋንዳው ቫይፐርስ የሚያደርጉትን  ጨዋት በዋና ዳኝነት ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ  ሲመሩት በረዳትነት  ትግል ግዛው ፣ ሳሙኤል ታንጎ እንዲሁም አራተኛ  በላይ ታደሰ እንንዲሁም የጨዋታው ኦፊሰር ታንዛኒያዊው  ክሊፎርድ ንዲምቦ ይሆናሉ።

እንደሚታወሰው ባለፈው ሳምንት  በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የግብጹ አልአህሊና  ከደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስ ካይሮ ላይ ያደረጉትንና በ2 ለ 2 አቻ ውጤት የተጠናቀውን   ጨዋታኢትዮጲያዊያን ዳኞች በመሃል ዳኝነት አርቢትር በዓምላክ ተሰማ ፣ ረዳት ዳኝነቱን ትግል ግዛውና ተመስገን ሳሙኤል የመሩት ሲሆን በአራተኛነቱ ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ መዳኘታቸው ይታወሳል።

 

መረጃ
በቴሌግራም :-

https://t.me/Ethio_Kickoff

በኢንስታግራም ገጻችንን  :-
https://www.instagram.com/ethio_kick

🔛ድረ ገጻችንን  :-
https://ethio-kickoff.com