አትሌቲክስ ዜናዎች

#ኢትዮዽያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል!

በፈረንሳይ ደ ሞንዴቪል ዛሬ በተካሄደው የቤት ውስጥ የ 1500ሜትር የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉዋል።
በውድድሩ አያል ዳኛቸው 4:11:00 በመሮጥ ቀዳሚ ስትሆን ፣ትግስት ከተማ ሁለተኛ ሲንቦ 3ኛ እንዲሁም ትዕግስ 4ኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።
በተመሳሳይ በፖላንድ ኦርለን ኮፐርኒከስ ዋንጫ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር በ3000ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል
በተጨማሪም በፖላንድ የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በ4:16,16 አሸንፋለች።